በአርዱፍ ታግተው የቆዩት ሁለት ጀርመናውያን ተለቀቁ

የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር(አርዱፍ) ታግተው የቆዩት ሁለት ጀርመናውያን ተለቀቁ። አርዱፍ ባወጣው መግለጫ፤ ሁለቱን ጀርመናውያን ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ለ አፋር ሽማግሌዎችና በኢትዮጵያ ለጀርመን ኤምባሲ ባለሥልጣናት ማስረከቡን አስታውቋል። ባለፈው ጥር ወር መግቢያ ላይ በአርዱፍ አማፅያንና በኢትዮጵያ መንግስት ታጣቂዎች መካከል  አፋር ውስጥ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የአርታሌ እሳተ ገሞራን ለመጎብኘት ወደ ሥፍራው ሲሄዱ የነበሩ አምስት የውጭ ቱሪስቶች ...

Read More »

ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን ዐረፉ

የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሰው ማለት፤ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ ዕለት” ሲሉ ይሰማሉ-ከሁኔታዎች ጋር ተለዋዋጭ በሆነው በሰው ልጆች ባህርይ- የስሜት ስብራት የደረሰባቸው ወገኖች። ይሁንና በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በአገራዊ ፖለቲካው ዙሪያ የጊዜና የሁኔታዎች ግፊት ከያዙት እውነታና አቋም የማያነቃንቋቸው ጥቂት የህሊና ሰዎች አልፎ አልፎም ቢሆን መከሰታቸው አልቀረም። ከነዚህ ፤ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆነው ከተገኙትና በሁኔታዎች ተጽዕኖ ካልተለወጡት መካከል፤  የኢትዮጵያ  ...

Read More »

በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚኖሩ አርሶአደሮች ከመንግስት ጋር ተፋጠዋል

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚኖሩ አርሶአደሮች ክልላችንን አናስደፍርም በማለት ከመንግስት ሀይሎች ጋር ተፋጠዋል ታዋቂውን እና ጥንታዊውን የወልድባ ገዳም ግቢ ለስኳር ምርት በሚል በዶዘር መታረስ መጀመሩን ተከትሎ በርካታ የመነኮሳቱ አጽም ሜዳ ላይ ተበትኖአል። የመንግስት ድርጊት ያበሳጫቸው መነኮሳቱ ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማቅረብ መልስ እናገኛለን ብለው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ጥያቄ ቢያቀርቡም “እናንተ እነማን ናችሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ደፍራችሁ ...

Read More »

የአማራ ክልል መምህራን ማህበር ሊቀ መንበርን ለመተካት ትናንት ምርጫ ተደረገ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመምህራንን ጥያቄ ያለምንም ፍርሀት ለመንግስት በማቅረባቸው፣ በመምህራን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት አቶ መንግስቱ አህመዴን ለመተካት ምርጫ ተካሂዷል ምርጫውን የሚያካሂዱት የየወረዳው የመምህራን ተወካዮች የዞን ተወካዮችን፣ የዞን ተወካዮች ደግሞ የክልል ተወካዮችን እንዲመርጡ ከተደረገ በሁዋላ ነው። የምርጫው ስርአት በስልጣን ላይ ላለው የመለስ አገዛዝ ለድርጅቱ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለመምረጥ ያስችለዋል። መምህራን በምርጫው ቀጥተኛ ተሳትፎ የማያደርጉ በመሆኑ፣ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግሥትና መጅሊስ እየፈጸመብን ያለው ደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው ይላሉ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥትና በማይወክለን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት /መጅሊስ/ በሃይማኖታችን ላይ እየተፈጸመብን ያለው ደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አስታወቁ፡፡ በአወሊያ መስኪድ አስተባባሪነት ሕዝበ ሙስሊሙን ወክለው ከመንግሥትና ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ጋር እንዲደራደሩ የተመረጡት 17 የኮሚቴ አባላት ውይይቱ ፍሬ አልባና ለመንግሥት ያቀረብነው መሠረታዊ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎች ሁሉ መና ቀርተዋል ብለዋል፡፡ በዛሬው እለት ...

Read More »

በማላዊ 70 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማላዊን ከታንዛኒያ በሚያዋስነዉ አካባቢ በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰዉ ገብተዋል የተባሉ 70 ኢትዮጵያዊያንና አንድ የሶማሊያ ዜጋ በፖሊስ ተይዘዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ኦል አፍሪካን ኒዉስ ገለፀ። ህገወጥ ስደተኞቹን ረድታችሁዋል ተብለዉ 3 የማላዊ ዜጎችም በእስር ላይ ይገኛሉ። በጢሻ ዉስጥ ተደብቀዉ የነበሩት ስደተኞች የተያዙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት መሆኑን የገለፁት የአካባቢዉ የፖሊስ አዛዥ ስደተኞቹ በተሸሸጉበት ስፍራ ...

Read More »

ኩፍኝ፣ መንጋጋ ቆልፍ እና ወባ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባወጣዉ ሪፖርት ባለፈዉ ሳምንት በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ዉስጥ እንዲሁም በአጎራባች የጋሞ ጎፋ ዞን እና በአማራ ክልል አዊ ዞን አንካሻ ወረዳ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዲባት ወረዳ በሽታዎቹ በአዲስ መከሰታቸዉን ገልጿል።  የተጠቀሱት ክልሎች የጤና ቢሮዎች ከአለም የጤና ድርጅት ባለሙያዎች ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ጥናት በማካሄድ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በኦስሎ ኖርዌይ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው የተደረገው የኖርዌይ መንግሥት የፖለቲካ ከለላ የጠየቁ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ከመለስ መንግስት ጋር ስምምነት መፈራራሙን በመቃወም ነው። ስምምነቱ የመኖሪያ ህጋዊ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውያን እስከ ማርች 15-2012 ድረስ አገር ለቀው ይወጣሉ።  ማርች ሁለት እና  5  በኦስሎ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሥርአቱን በመቃውም   አገራቸውን ...

Read More »

የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ውዝግብ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ በነዳጅ ሀብቷ በበለፀገችው በኮርዶፋን ግዛት ዙሪያ የፈጠሩትን  የይገባኛል ውዝግብ ለመፍታት፤ በኢትዮጵያ ሸምጋይነት አዲስ አበባ ውስጥ ድርድራቸውን ለመጀመር በተዘጋጁበት ጊዜ የአልበሽር መንግስት- ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት መዘጋጀቱ ተዘገበ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ልዑክ የሚዲያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ የሱዳን መንግስት ከደቡብ ሱዳን ጋር የፈጠረውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት በገለፀበት ማግስት ኬንያ፤ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ሰሞኑን ...

Read More »

አንዱአለም አራጌ የመግደል ሙከራ ተደረገበት

የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፈጠራ የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በአስከፊ እስርቤት ውስጥ ከሚማቅቁት መካከል የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አንዱአለም አራጌ በደረሰበት ድብደባ የተነሳ በደንብ መቆም እንደማይችልና ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታትም እንዳለበት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ የእስረኞችን የመከላከያ ማስረጃ ለማየት የተሰየመው ችሎት፣ የብይን ግልባጭ ለጠበቆቹ ባለመሰጠቱ ችሎቱን ለማስተላለፍ ተገዷል። አንዱአለም በድብደባው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የማረሚያ ...

Read More »