የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚያደርጉትን አድማ እንደቀጠሉ ነው

ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተዋል ይላል የደረሰን መረጃ። ተማሪዎቹ ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ እንዳላገኙ፣ ግቢያቸውን ለመልቀቅም ፈቃደኞች እንደልሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አካባቢውን ከቦ መቀመጡን ለማወቅ ተችሎአል።  የአወልያ ኮሌጅ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዛሬው እለት ለተለያዩ የእስልምና ተከታዮች የስልክ ጥሪ በማድረግ  ለዝሁር ጸሎት  እንዲቀላቀሏቸው ...

Read More »

አገር የመጠበቅ ግዳጅ ተጥሎበታል የተባለው መከላከያ ሚኒስቴር፤ በሆቴል ግንባታና ንግድ ውስጥ መሰማራቱ ተዘገበ

ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ፎርቹን ዘገባ፤መከላከያ ሚኒስቴር በትግራይ-መቀሌ ውስጥ በ165 ሚሊዮን ብር ወጪ  ለከፍተኛ የጦር መኮንኖች  መዝናኛ የሚሆን ባለ ሦስት ኮከብ ልዩ ሆቴል ለማስገንባት እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፤ ሆቴሉን በበላይነት ከመቆጣጠር ባሻገር የንግድ ስራውን የሚያካሂደውም ራሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ነው።  በኢትዮጵያ የመከላከያ ታሪክ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ፤ ንግድ ለማካሄድ ሆቴል ሲያስገነባ ፤ይህ የመጀመሪያው ነው። በመከላከያ ሚኒስቴር አማካይነት መቀሌ ...

Read More »

ሁለት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተገደሉ

ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሲራጂ እና ከማል የተባሉ ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞቱ። ተማሪዎቹ የተገደሉት በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት እስካሁን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ ውስጥ አዋቂዎች ፦”ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው”ማለታቸውን ፍኖተ -ነፃነት ዘግቧል። የሟቾቹ ተማሪዎቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከትናንት በስቲያ ተፈጽሟል። ስለጉዳዬ የ ዩኒቨርሲቲውን ሀላፊዎች ለማነጋገር የተደረገው ...

Read More »

የኑሮ ውድነቱ ፤ ለእግር ኳስ ውድድር መቋረጥ ምክንያት ሆነ

ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅዱስ ጊዮርጊስና በ አየር ሀይል ክለቦች መካከል ከትላንት በስቲያ በደብረዘይት ከተማ ሊከናወን የነበረው የእግር ኳስ ውድድር ፤ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ተመልካቹ  ማሰማት በጀመረው ተቃውሞ መባባስ ምክንያት ተቋረጠ። ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በስቴዲዮሙ የተገኘው ተመልካች የወቅቱን የኑሮ ውድነትና  በገዥው ፓርቲ እየተፈጸመ ያለውን የአፈና ድርጊት በዜማና በግጥም  መቃወም መጀመሩን የዘገበው ፍኖተ-ነፃነት፤ በዚህ መልክ የተጀመረው የተመልካች ተቃውሞ ውድድሩም ...

Read More »

በእኛ መታሰር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ዓለም ለማወቅ ችሎአል ሲሉ የስዊድን ጋዜጠኞች መናገራቸው ተሰማ

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእኛ መታሰር ዓለም  በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የፕሬስ ነጻነት አፈና ለማወቅ ችሎአል ሲሉ በእስር ላይ የሚገኙት የስዊድን ጋዜጠኞች መናገራቸው ተሰማ ሲኤን ኤን የማርቲን ሺቢየ እናት የሆኑትን ካሪን ሽብየን አነጋግሮ እንደዘገበው ማርቲን ሽብየና ጆን ፔርሰን የአለም ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የፕሬስ አፈና ለመረዳት በመቻሉ፣ ተልኮአቸው መና እንዳልቀረ ይረዳሉ። “ጋዜጠኞቹ ንጹሀን ...

Read More »

ከ200 ሺ ብር በላይ ከባንክ የሚወጣ ወይም የሚገባ ገንዘብን አስመልክቶ የተደነገገው አዲስ አዋጅ ተቃውሞና ትችት እየቀረበበት ነው

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት ፤ ከጥር 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከ200 ሺ ብር ወይም ከ10 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ከባንክ የሚወጣ ወይም የሚገባ  ገንዘብን አስመልክቶ ብሔራዊ ባንክ-ለፀረ-ሽብር ግብረ-ሀይል ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት  የደነገገው አዲስ አዋጅ  ተቃውሞና ትችት እየቀረበበት ነው። ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ   አንድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ  በመጥቀስ ሰንደቅ እንደዘገበው፤ መመሪያው ሥራ ላይ የዋለው ኅብተሰቡን  ስለ ...

Read More »

አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት “ፓርላማ” ብሎ በሚጠራው የገዥው ፓርቲ አባላት ስብስብ ውስጥ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ  ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ። በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ የሚወሰዱ ልጆችን የጤና ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል መመሪያ ለህፃናት ሀኪሞች ተዘጋጀ፡ በጉዲፈቻ የሚወሰዱ አዳዲስ ህፃናትን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ...

Read More »

በሳዉዲ መካ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ያለፈቃድ ከሚገባቸዉ ጊዜ በላይ ሲኖሩ የተገኙ 85 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ፡ የየመን እና የህንድን ፓስፖርት የያዙ  በሳዉዲ አረቢያ የሄዱበትን የሃጅና ኡምራ የፀሎት ጉዞ ካጠናቀቁ በሁዋላ ያለፈቃድ በመኖራቸዉ 85 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አረብ ኒዉስ ገለፀ። ግለሰቦቹ በህገ ወጥ መንገድ በኮንስትራክሽንና በሌሎች የጉልበት የስራ መስኮች የተሰማሩ እንደነበር ሌተና ኮሎኔል ሙሃመድ አል ሁሴን የመካ ፓስፖርት ፖሊስ ሃላፊ ገልፀዋል። በማእከላዊ ዞን ዉስጥ አጅያድ፤ ሬኦ፤ ካድዋ በተባሉት አካባቢዎች ...

Read More »

በጄኔራል ከማል ገልጁ የሚመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ፣ የሚደነቅ ነው ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:- የቀድሞው የኦፌዴን ሊቀመንበር እና አሁን የንቅናቄው የክብር ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለኢሳት እንደተናገሩት  በጄኔራል ከማል ገልቹ የተመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ በደስታ ነው የምከታተለው ብለዋል። “የኦሮሞ ህዝብ የሚሸሽ ወይም የሚገነጠል ህዝብ አይደለም” የሚሉት አቶ ቡልቻ፣ ሁሉም በዚህ ሀሳብ ዙሪያ ቢሰባሰብ ጤነኛ እንሆናለን ሲሉ አክለዋል ። አቶ ቡልቻ የጄኔራል ከማል ቡድን ከዚህ በፊት ሌላ ...

Read More »

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኤልያስ ክፍሌ ከጥፋት ነፃ ናቸው አሊያም ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ ዛሬ ሳይሰጥ ቀረ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ለፍርድ ቀጥሮት የነበረውን በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባልና ጋዜጠኞች ላይ ከጥፋት ነፃ ናቸው አሊያም ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ ዛሬ ሳይሰጥ ቀረ፡፡ የፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ...

Read More »