የኢሳትን ወደ ዓየር መመለስ በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣

ኀዳር 23፣ 2003 ዓም በጋራ ጥረት የኢሳትን ህልውናን ማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ነጻን ሚዛናዊ የመገናኛ ብዙሀን ተቋም መሆኑን፣ በኢዲቶሪያል ፖሊሲው ያስቀመጠው ብቻ ሳይሆን፣ ሥራ ከጀመረበት ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በተግባር ያረጋገጠው ጉዳይ ነው። ለዚህም ጠንካራ መረጃዎቹ በየጊዜው ያስተላለፋቸውና ዛሬም እያስተላለፋቸው ያሉት ፕሮግራሞቹ ናቸው። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ሥር በሆኑባቸው ሐገራት ሊኖረው የሚችለው ...

Read More »

ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ስርጭት ለሦስተኛ ጊዜ ተቋረጠ።

ሐምሌ 19 ቀን 2002 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) በኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአውሮፓ አገሮች የሚያሰራጨው የቴሌቪዥን አገልግሎት ከ ሀምሌ 19 ቀን 2002 ዓም ጀምሮ ለሦስተኛ ጊዜ ተቋርጦአል። በተመሳሳይ ጊዜም በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተላለፈው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሥርጭትም ከአገልግሎት ውጭ ሆኖአል። ሥርጭቱ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዲቋረጥ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን በእጃችን የሚገኙ ማስረጃዎች አረጋግጠውልናል። ከ ሐምሌ 19 ቀን 2002 በፊት የኢሳት ስርጭት ባልተቋረጠ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ መታፈኑን ስለመግለጽ

ግንቦት 21/ 2002 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ ምንጩን በዉል ለማወቅ አዳጋች በሆነ ሞገድ /electronic interference/ በመጠቃቱ የስርጭት አገልግሎቱን ከአለፉት ሦስት ቀናት ጀምሮ ለተመልካቹ ለማድረስ አለመቻሉ ይታወቃል ። የአገልግሎት ሰጪው ድርጅት ባደረገው የቅድመ ማጣሪያ ስራም የሚከተሉትን እውነታዎች ለማረጋገጥ ተችሏል፣ አገልግሎቱን የሚሰጠዉ ኩባንያ ችግሩን ለመፍታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደረገ ከቆየ በሁዋላ የኢሳት ስርጭት ምንጩ በውል ካለታወቀ አካባቢ በሚሰራጭ ሞገድ ኢላማ ተደርጎ እየተጠቃ ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን አማካሪ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 20 2002 ዓም ጉዳዩ፡ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዠን ስርጭት መቋረጥን ይመለከታል የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ላለፉት 24 ሰዓታት በአየር ላይ አለመዋሉ ይታወቃል። የስርጭቱ መቋረጥ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን በሺዎች የሚቆጠሩ የስልክና የኢሜል መልእክቶችን ልከውልናል። ለተሰጠው የሞራል ማበረታቺያ፣ የበጎ ምኞት መግለጫ ና ድጋፍ ተመልካቾቻችንንና ደጋፊዎቻችንን ማመስገን እንወዳለን። የኢሳት አማካሪ ቦርድ ለተመልካቾቻችንና ለደጋፊዎቻችን የሚከተሉትን መልእክቶች ማስተላለፍ ይፈልጋል፣ አገልግሎቱ የተቋረጠው ኢሳት በወሰዳቸው ወይም የኢሳት ሰራተኞች ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣

ሚያዚያ 22 ቀን 2002 ዓም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቀደም ሲል የሥርጭት አገልግሎቱን በኤፕሪል ወር መጨረሻ  እንደሚጀምር ይፋ አድርጎ ነበር። የቴሌቪዥን አገልግሎቱ በኤፕሪል ወር መጨረሻ ሥርጭቱን ለመጀመር ዕቅድ ሲያወጣ በጊዜው ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ ነበር። የመጀመሪያው፣ ሥርጭቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ማናቸውም ዓይነት የራሱ ውስጣዊ ዝግጅቶች ማጠናቀቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው፣ ፕሮግራሞቹን ለማስተላለፍ የሚያስችለው ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረግ የሁኔታ ማመቻቸት ነበር። የመጀመሪያውን ዝግጅት በያዘው ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት፣ የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ ሊጀምር ነው።

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት የተለያዩ፣ የዜና፣ የውይይት፣ ጥናታዊ፣ የመዝናኛ ፣ የስፖርት ፕሮግራሞቹን፣ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ ሌሎች የአለም ክፍሎች በኤፕሪል መጭረሻ ማሰራጨት ይጀምራል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን አገልግሎት ያቋቋምን አካላት ኢትዮጵያ ሀገራችን እና ህዝቧ አሁን ለሚገኙበት እጅግ አስቸጋሪ እና ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ እንዲደርሱ ከአደረጓቸው በርካታ ምክንያቶች አንዱ እና ...

Read More »