በጎንደርና ባህርዳር ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በሶስት አመት ይጠናቀቃል

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት11/2011)በአማራ ክልል ጎንደርና ባህርዳር ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በ1መቶ ሚሊየን ብር ለመገንባት የሚንቀሳቀሰው ወንፈል ተራድኦ ተቋማቱን በሶስት አመታት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል ገባ። በአሜሪካን ሃገር የተቋቋመውና በክልሉ ተወላጆች ኢትዮጵያውይን የተመሰረተው ድርጅት ግንባታውን የሚያከናውነው ከአማራ ልማት ማህበር ከዩኒቨርስቲዎች ጥምረት ፎረምና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ነው። የወንፈል ተራድኦ ስራ አስፈጻሚ አባላት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ለግንባታው ከሚውለው ...

Read More »

ግሎባል አሊያንስ ከጎንደር ለተፈናቀሉ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ረዳ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 11/2011)ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር መለገሱን ግሎባል አልያንስ አስታወቀ። አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን ግሎባል አሊያንስ የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ከ3 ሺ በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉትም የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ። እናም በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ...

Read More »

በጎንደር የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የሚከልከል መመሪያ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2011)በጎንደር በተወሰኑ አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የሚከልከል መመሪያ በአማራ ክልል ይፋ ተደረገ። መመሪያውን ለማስፈጸም ከመከላከያ ሰራዊት ፥ከክልሉ ፖሊስና የጸጥታ ሐይሎች የተወጣጣ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ዘላለም  ልጅአለም ከኢሳት ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ አስታወቋል። ይህ ጸጥታን በጥምር ወታደራዊ እዝ የማስከበሩ ስራ በመመሪያ መልክ የወጣ እንጂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመሆኑንም አቶ ዘላለም ገልጸዋል። በምዕራብ እና ...

Read More »

አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተፈቀደ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011)የኢትዮ ቴሌኮም የኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ የነበሩትና በሌብነት የተጠረጠሩት አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤት ፈቀደ። ፍርድ ቤቱ አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ፈቅዶላቸዋል። ፖሊስ በወሳኔው ላይ ይግባኝ ስለመጠየቁ የተገለጸ ነገር የለም። አቶ ኢሳያስ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ይፈቱ አይፈቱ የታወቀ ነገር የለም። መርማሪ ፖሊስ  በኢትዮ-ቴሌኮም ኃላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ...

Read More »

በምዕራብ ጎንደር 138 ግለሰቦች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011)በምዕራብ ጎንደር ዞን ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ 138 ግለሰቦች በሕይወት ማጥፋትና በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው መታሰራቸው ተነገረ። በግጭቱ ሳቢያ 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር አስታውቋል ። በምዕራብ ጎንደር  ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶችና መሳሪያዎች  መያዛቸውም ተነግሯል። በምዕራብ ጎንደር ዞን ካለው ግጭት ጋር ...

Read More »

ኢሳት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2011)በኢትዮጵያ ለተካሄደው ለውጥ ኢሳት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና እንደሚገባው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ገለጹ። የኢሳት የጋዜጠኞች ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ካሳሁንን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውለታል። የኢሳትን ጋዜጠኞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ካሳሁን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የኢሳትን ጋዜጠኞች ሲቀበሉ የሚዲያ ተቋሙ የኢትዮጵያ ...

Read More »

በኢትዮ-አሜሪካ ለተቋቋሙ የንግድ ሰጪ ተቋማት ድጋፍ ይደረጋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011)የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያውያንና በኢትዮ-አሜሪካ ለተቋቋሙ የንግድ ሰጪ ተቋማት ድጋፉን እንደሚያደርግ አስታወቀ። የንግድ ምክር ቤቱ አባል ለሆኑ ተቋማት በማንኛውም መንግስታዊና ሕጋዊ በሆኑ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የንግድ ማህበረሰቡን ወክሎ የአባላቱን ጥቅም እንደሚያስከብርም ምክር ቤቱ ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ በይፋ መመስረቱ በተገለጸበት መድረክ ላይ ምክር ቤቱ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ድጋፉን እንደሚያደርግ ተገልጿል። የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት ምስረታ ላይ የተገኙት ...

Read More »

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011) የኢትዮ-ቴሌኮም የቀድሞው የኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው በአዲስ የሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ። አቶ ኢሳያስ ዳኘው በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ በዋስ እንዲፈቱ በጠቅላይ ፍርድቤት ተወስኖላቸው እንደነበር ታውቋል። የሜቴክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩትና በእስር ላይ የሚገኙት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ፖሊስና አቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ...

Read More »

የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ካምፕ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት/2011)በትጥቅ ትግል ላይ በጫካ የነበሩ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ ገቡ። ሕዝቡና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ቅንጅታዊ ሥራ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የኦነግ ሰራዊት አባላት ሀገራዊ ለውጡን ለመደገፍ ቁርጠኛ በመሆን ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባታቸው ታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ሰራዊት አባላት ጦላይን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል በተዘጋጁ የተለያዩ ካምፖች በመግባት ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸው ተነግሯል። እነዚህ ወደ ካምፕ የገቡት አባላት ...

Read More »

የኢሳት ባልደረቦች ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሊቪዥንና ሬዲዮ ኢሳት ባልደረቦች ከአምስተርዳም፣ለንደንና ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ አሸኛኘት ተደረገላቸው። ከዋሽንግተን ዲሲ የተነሱት የኢሳት ባልደረቦች ከዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ሲነሱ በኢትዮጵያውያን አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። አሸኛኘቱን በስፍራው ተገኝቶ ሲዘግብ የነበረውም ምናላቸው ስማቸው ስለ አሸኛኘቱ መረጃውን ሊያደርሰን እዚህ ስቱዲዮ ይገኛል።  

Read More »
gittigidiyor indirim kuponuполучить кредит онлайн на карту