በኦነግ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011)በኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በመንግስት በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። እየታዩ ያሉት ችግሮችም ከዚሁ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን በማመልከትም ጦርነት የሚባል ነገር አሁን የለም ሲሉም አስረድተዋል። ጄኔራል ብርሃኑ እንዳሉትም በቅርቡ ወደ ቤተመንግስት ተጉዘው የነበሩት ወታደሮች  ቤተመንግስቱን ለመበጥበጥና ካገኙም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመግደል አልመው ነበር። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ምክትል ኤታማዦር ሹምና ...

Read More »

የራያዎች አንገብጋቢ ጥያቄ የማንነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የራያዎች ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄ የማንነት እንጂ የልማት አይደለም ሲል የራያ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል ዛሬ በአላማጣ ከተማ  በጠሩት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን ተከትሎ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጸው ማንነቴን መልሱልኝ ያለን ህዝብ በልማት የተስፋ ቃላት ለማዘናጋት መሞከር ከንቱ ድካም ነው ብሏል። ብዙ ከማውራት ብዙ መስራት በሚል መሪ ቃል በዶክተር ...

Read More »

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከስልጣናቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የሀረሪ ክልልን ለ12 ዓመታት ያስተዳደሩት አቶ ሙራድ አብዱላሂ ከስልጣናቸው ተነሱ። በምትካቸው አቶ ኦሪዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሀረሪ ገዢ ፓርቲ ሃብሊ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብን ተከትሎ ከስልጣናቸው የተነሱት አቶ ሙራድ ቤተሰባዊ አስተዳደር በማስፈንና ደጋፊዎቻቸውን በዙሪያቸው በማሰባሰብ ሲወነጀሉ ቆይተዋል። አቶ ሙራድ ከሃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም ለተተኪያቸው አቶ ኦሪዲን ስልጣን ...

Read More »

በአፋር ፖሊስ የሃይል ርምጃ መውሰዱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011)በአፋር ዛሬ በተካሄደ ህዝባዊ ተቃውሞ ፖሊስ የሃይል ርምጃ መውሰዱ ተገለጸ። በአዳር ወረዳ ኤልውሃ በተሰኘች ከተማ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን የክልሉ ልዩ ሃይል በወሰደው ርምጃ በርካታ ሰዎች በስለት ተወግተውና ተደብድበው ሆስፒታል መግባታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አንድ የሀገር ሽማግሌን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ኤልውሃ ከተማ ነዋሪዎች የታሰሩት በአስቸኳይ ካልተፈቱና ስለት ተጠቅመው ጉዳት ያደረሱ ፖሊሶች ለህግ ካልቀረቡ ተቃውሞውን ...

Read More »

ትውልደ ኤርትራዊና ትውልደ ሶማሊያዊ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ሆነው ተመረጡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011) በአሜሪካ በተካሄደው የአማካይ ዘመን ምርጫ ትውልደ ኤርትራዊና ትውልደ ሶማሊያዊ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ሆነው ተመረጡ። ለ435 የአሜሪካ ምክር ቤት ወንበር ትውልደ ሶማሊያዊዋ ኢላን ኦማር በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሙስሊም የኮንግረስ አባልም ሆነዋል። የ34 አመቱ ዮሴፍ ንጉሴ በኤርትራ ውስጥ በሚካሄደው ጦርነት ሳቢያ ቤተሰቦቹ ወደ አሜሪካ ከተሰደዱ በኋላ በኮሎራዶ ግዛት መወለዱን በሕይወት ታሪኩ ላይ ተመልክቷል። ከኮሎራዶ ግዛት ለኮንግረስ ከተመረጡ አባላት አንዱ ...

Read More »

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ወደ ጎንደር ከተማ ሊሄዱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011) የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የፊታችን አርብ ጎንደር ከተማ ይገባሉ ተባለ። ፕሬዝዳንቱ በአማራ ክልል በሚያደርጉት ጉብኝት የክልሉን ርዕሰ ከተማ ባህርዳርን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎችም ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተመልክቷል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፊታችን አርብ ጎንደር ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የአማራ ክልል ባለስልጣናት አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው ተመልክቷል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት በጠላትነት የቆዩበት ምዕራፍ ባለፈው ሰኔ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአስመራ ጉብኝት ፍጻሜ ...

Read More »

በሕገወጥ መንገድ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011)ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ በሶስት ወራት ውስጥ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ብዛት ከ1 ሺ 500 በላይ መብለጡን ፖሊስ ገለጸ። የጦር መሳሪያዎቹም በአብዛኛው ቱርክ ሰራሾች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በብዛት የሚገባውም በሱዳን በኩል እንደሆነ ተመልክቷል። በፌደራል ፖሊስ የተደራጁ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ከተማ ደባልቄ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት እስከ መስከረም መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት 1 ሺ 560 ሕገ ወጥ ...

Read More »

በሕዝቦች ትግል የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስ መጠበቅ አለብን ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011) በሕዝቦች ትግል የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስ የተገኘውን ተስፋ፥ ነፃነት እና ሰላም መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገለጸ፡፡ ክልላዊ መንግስቱ በምዕራብ ጐንደር ዞን የተፈጠረውን ግጭት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በነጋዴ ባህር አካባቢ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የ4 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዚህ መነሻ በተፈጠረ ግጭት በዞኑ መተማ እና ሽንፋ አካባቢዎች ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ህይወትም መጥፋቱ ...

Read More »

ዓለም አቀፉ የቡና ቱሪዝም ፕሮግራም ተቃውሞ አስነሳ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011) የቡና መገኛ ጂማ ነው በሚል በቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን የሚከበረው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የቡና ቱሪዝም ፕሮግራም ተቃውሞ አስነሳ። ዛሬ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አውግዟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመተባባር የዘንድሮውን የቡና ቱሪዝም ለማክበር በከፋ የተያዘው ፕሮግራም ተሰርዞ በጂማ እንዲሆን መደረጉ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭና ታሪክን የሚቀማ ...

Read More »

በአፋር ተቃውሞ ሲደረግ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 28/2011) በአፋር የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲደረግ ዋለ። አሳይታ፣ አዳአር፣ በራሂሌ፣ ገላኢሉ፣ ዳሎል፣ ገዋኔና ኮነባ በተሰኙ የአፋር ከተሞች በተደረገው ተቃውሞ የክልሉን መንግስት የሚመራው ገዢ ፓርቲ ለህዝብ ስልጣኑን እንዲያስረክብ ተጠይቋል። ሁለተኛ ወሩን እያጠናቀቀ ያለው የአፋር ተቃውሞ ፌደራል መንግስቱ በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ የክልሉ ህዝብ ከተደቀነበት አደጋ እንዲታደገው ጥሪ ቀርቧል። የአፋር ህዝብ ፓርቲ ለኢሳት እንደገለጸው የፌደራሉ መንግስት በቶሎ ምላሽ ካልሰጠ በአፋር ከፍተኛ ...

Read More »