በአላማጣ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ አይከፈላችሁም ተባሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በአላማጣ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የምከፍለው ደሞዝ የለኝም ሲል የትግራይ ክልላዊ መንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ። የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ በጀት እንዲሰጠን ስለጠየቅን እስከዛው ድረስ የምከፍለሰ በጀት የለኝም ሲሉ የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ተወላጆቹ የክልሉ መንግስት እየወሰደ ያለው ርምጃ አግባብነት የሌለውና እኛን ለማጥቃት ሆን ብሎ ያቀደው ነው ሲሉ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።    

Read More »

የጋምቤላ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ ሳይደረግ ቀረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በጋምቤላ ተወላጆች ዛሬ ተጠርቶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሳይደረግ መቅረቱ ተገለጸ። በሁለት ከተሞች ተጠርቶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሳይካሄድ የቀረው አልተፈቀደም በሚል ምክንያት መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰልፈኞች ገና ከመጀመራቸው በፖሊስ እንዲበተኑ መደረጉ ታውቋል። በጋምቤላ ፍቃድ ተከልክሏል ለሌላ ጊዜ ጠይቁ በሚል የከተማው አስተዳደር ምላሽ መስጠቱን ነው የኢሳት ምንጮች የገለጹት። በቅርቡ በፓርላማ የጸደቀውን የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ በመቃወም ...

Read More »

በቴፒ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011) በቴፒ ጋብ ብሎ የነበረው ቀውስ ዳግም ማገርሸቱ ተሰማ። የሰው ህይወት የጥፋበት ግጭት ዛሬ መቀስቀሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኮንሶ ከአስተዳደር መዋቅር ጋር የተያያዘው ውጥረትም ሰሞኑን መባባሱን ለማወቅ ተችሏል። ለውጥ አደናቃፊ የሆኑ የደቡብ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናት አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይከሳሉ። በሌላ በኩል የክርስትና እምነት ተከታይ በሆኑ የጅጅጋ ነዋሪዎች ላይ ሰሞኑን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ጊዜያዊ የሰዓት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጥቃት ማድረሱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)የኢትዮጵያ አየር ሃይል በሶማሊያ የአልሻባብ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ገለጸ። 44 ደቂቃ በዘለቀው ጥቃት የአልሻባብ አመራሮችን ጨምሮ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎች መገደላቸውንም የኢትዮጵያ አየር ሃይል ለመንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። ከሶማሊያ ባይድዋ ግዛት በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቡርሃይቤ በተባለው የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥቃቱ መሰንዘሩንም መረዳት ተችሏል። ባላፈው ሳምንት መጨረሻ ጥር 16/2011 የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች በፈጸሙት ...

Read More »

በጅቡቲ ሁለት ጀልባዎች ተገልብጠው 28 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች ተገልብጠው 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 የሚበልጡት የገቡበት አለመታወቁን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዓለም አቀፉን የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤምን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ጀልባዎቹ ጉዞ በጀመሩ በ30 ደቂቃ ውስጥ በገጠማቸው ወጀብ ሲሆን ጎዶሪያ በተባለው የጅቡቲ ግዛት አደጋው መከሰቱም ተመልክቷል። የአካባቢው ነዋሪዎችን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻውን ሊያሰፋ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰሜን አሜሪካ የበረራ መዳረሻውን ሊያሰፋ መሆኑን አስታወቀ። አየር መንገዱ ወደ ሒውስተን አዲስ በረራ በመጀመር ወደ አፍሪካ የሚበሩትን መንገደኞች ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ መስመር እንደሚዘረጋም ታውቋል። ከኢትዮጵያ በየቀኑ በመብረር በሳምንት 7 ጊዜ ወደ ዋሽንግተን የሚያደርገውን ምልልስም 3 በረራዎችን በመጨመር ወደ 10 ማሳደጉንም ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደገለጹት ተቋማቸው በሰሜን አሜሪካ የሚያደርገውን ...

Read More »

አቶ አብዲ ኢሌ ክስ ተመሰረተባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ባለፈው ሰኔና ሐምሌ በክልሉ ግጭት እንዲነሳ በማድረግ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው። እንዲሁም ሴቶች እንዲደፈሩና ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ፣ በሃይማኖት ተቋማት ላይም ጥቃት እንዲፈጸም ማድረጋቸውንም አቃቤ ሕግ ገልጿል። ከወራት በፊት በቁጥጥር ስር ውለው በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት የሚገኙት አቶ አብዲ መሐመድ ክስ የተመሰረተባቸው ከሌሎች 46 ግለሰቦች ጋር ...

Read More »

የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አዋጅን በመቃወም ነገ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2011)በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የጸደቀውን የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አዋጅን በመቃወም በነገው ዕለት በሁለት ከተሞች ሰልፍ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ። የጋምቤላ ክልልን ነዋሪዎች ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው በሚል ተቃውሞ የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባና ጋምቤላ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪ አቶ ፔን ኡጁሉ ለኢሳት እንደገለጹት ከክልሉ ነዋሪዎች ቁጥር በላይ ለሆኑት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የተሰጠው መብት የኢትዮጵያውያኑን መብትና ...

Read More »

ታንዛኒያ ሕጻናት የሰውነት ክፍሎቻቸው ተሰርቀው መሞታቸው ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2011)ታንዛኒያ ውስጥ ታግተው የተወሰዱ 10 ሕጻናት የሰውነት ክፍሎቻቸው ተሰርቀው ሞተው መገኘታቸው ተዘገበ። የአሜሪካው ኬብል ኔትወርክ ሲ ኤን ኤን የታንዛኒያ ምክትል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩን አነጋግሮ ባጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው ሕጻናቱ የታገቱት ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ሲሆን ጥርሶቻቸውን ጨምሮ የሰውነት ክፍሎቻቸው ተወስዶ አስከሬናቸው ተገኝቷል። የታንዛኒያ ምክትል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፋውስቲን ንድጉሊ ድርጊቱን ከጠንቋዮች ጋር አያይዘውታል። መዳኒት አዋቂ ነን ባዮች ከዚህ ቀደም ...

Read More »

የእስራኤል ፖሊስ አንድ ኢትዮጵያዊን ወጣትን መግደሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2011)የእስራኤል ፖሊስ አንድ የአዕምሮ ሕመም ያለበትን ኢትዮጵያዊ በመግደሉ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን አስነሳ። የሁዴ ቢያድጌ የተባለው የ24 ዓመት ወጣት ኢትዮጵያዊ ከቤቱ ወጥቶ ሲሄድ ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ይደውላሉ። ቤተሰቦቹ ፖሊስ የጠሩበት ምክንያት ልጃቸው አደጋ እንዳይደርስበት እንዲታደግላቸው እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል። ይሁንና ፖሊስ ከተጠራ በኋላ የአዕምሮ ህመምተኛው ጩቤ ይዟል በማለት ተኩሰው እንደገደሉት ለማወቅ ተችሏል። የአዕምሮ ሕመምተኛው ኢትዮጵያዊ እገዛ ሊደረግለት ሲገባ በፖሊስ በመገደሉ ...

Read More »