በሃገራት መካከል ያለው ትብብርና አንድነት አደጋ ላይ ወድቋል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በሃገራት መካከል ያለው ትብብርና አንድነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ገለጹ። ዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ በመካሄድ ላይ ባለው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደገለጹት ስርዓትና ደንብ ያስያዘውና ህዝቦች ተቀራርበው ለጋራ ዓላማ እንዲሰሩ ሲያደርግ የነበረው አንድነት እየተሸረሸረ ነው። ይህ አንድነት በጣም በሚያስፈልገን ወቅት አደጋ ላይ መውደቁ አሳሳቢ ነው ሲሉ ዋና ጸሃፊው ስጋታቸውን ገልጸዋል። ጽንፍ የያዙ ...

Read More »

የአየር ትራፊክ ሰራተኞች ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ። ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲወጡ ትላንት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን አቃቢ ሕግ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እጠይቃለሁ ማለቱ ተመልክቷል። በሃገሪቱ ላይ የ70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ኪሳራ አድርሰዋል በሚል ተጠርጥረው የአየር ትራፊክ ተቆጣጠሪ ሰራተኞች በ20ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ትላንት ነው። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የአየር ትራፊክ ሰራተኞች ...

Read More »

ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከተከሰተው አልመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ። የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ወቅት አስተባባሪ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች የታሰሩት በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በታፈሱበት ወቅት እንደነበርም ይታወሳል። ሁለቱ ወጣቶች ዛሬ ከወህኒ ወጥተው ቤተሰባቸውን መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።    

Read More »

ይህ ቀን እንዲመጣ መስዋዕትነት ለከፈሉ ዜጎች እውቅና ሊሰጥ ይገባል

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011)በጨቋኙ መንግስት እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች ቁም ስቅላቸውን ላዩ ጋዜጠኞች ፣ የመብት ተሟጋቾች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይህ ቀን እንዲመጣ ለከፈሉት መስዋዕትነት ታላቅ ክብር እና እውቅና እንደሚገባቸው አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ገለጸ፡፡ አክቲቪስት ታማኝ በየነ በኢትዮጵያ ሆቴል በሽብርተኝነት ስም በእስር ለተንገላቱ ወገኖቹ የምስጋና እና የምሳ ገብዣ አድርጓል  

Read More »

የአማራ ክልል ለብአዴን ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የአማራ ክልል ለብአዴን ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። በባህርዳር ከ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄዱት አቶ ደመቀ ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተባብረን ሀገርን ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅም ሳንጠቀም በትነን ቆይተናል ሲሉ ከ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስቱና የፌደራል ስርአቱ እየተጣሰ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በኢትዮጵያ ሕገ መንግስቱና ፌደራል ስርአቱ እየተጣሰ መሆኑን ሕዝቡ ተገንዝቧል ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። የሕወሃት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ዛሬ የተጀመረውን የሕወሃት ጉባኤ በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትምክህተኛው ሃይል ስርአቱን ለማፍረስና ወደ ኋላ ለመመለስ እየተንቀሳቀሱ ነው ሲሉም ከሰዋል። 27 አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሁሉ ጨለማ ነው ብሎ መናገሩም ሆነ ሁሉንም ነገር ከሕወሃት ጋር ማያያዙም ...

Read More »

የደመራ በአል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የዘንድሮው የደመራና የመስቀል በአል የሚከበረው ሰይጣን ድል በተነሳበትና ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድነት በመጡበት ወቅት ነው ሲሉ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ ገለጹ። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ይህንን መልዕክት ያስተላልፉት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው የደመራ በአል ላይ ነው። በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ በአል በስፍራው ለታደሙ ምዕመናንና እንግዶች መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ መፈጠሩንና ሁለቱም ...

Read More »

ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ ክስ ተመሰረተባቸው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 15/2011) ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ የኬንያ ፖርላማ አባል ሆነዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው። የፓርላማ አባሏ ወንበራቸውን ተነጥቀው በምትካቸው ሌላ ሰው እንዲመረጥም ጥሪ ቀርቧል። የመርሳን ቤት አውራጃን ወክለው የኬንያ ፓርላማ አባል የሆኑት ሶፍያ ሼክ ኡደን ከኬንያ ባሻገር የኢትዮጵያና የአሜሪካ ዜግነት ይዘዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። የመርሳ ቤት አውራጃ ነዋሪ የሆኑት ያያ መሃመድ ሃሰን ለኬንያ ከፍተኛው ፍ/ቤት በትናንትናው ዕለት ክስ አቅርበዋል። የቀረበባቸው ...

Read More »

የግብጽ ወታደራዊ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 15/2011) የግብጽ ወታደራዊ ልዑካን በመጪው ጥቅምት ወር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚወጡ ተገለጸ። የግብጽ ወታደራዊ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ ምንን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም በጥቅምት ወር መጀመሪያ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተመልክቷል። በግብጽ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚ ፎረም ዳይሬክተር የሆኑት ግብጻዊው አደል አልአዳዊ በቲውተር ገጻቸው ዕሁድ ዕለት ባሰራጩት መረጃ ውይይቱ ጠቃሚ እንደሚሆንም አመልክቷል። ግብጻውያኑ ወታደራዊ ልዑካን በቁጥር ምን ያህል እንደሚሆኑና በማን ...

Read More »

የድሬዳዋ ፖሊስ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የድሬዳዋ ፖሊስ ለ13 ሰዎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ግጭትና መንስኤ በመመርመር ውጤቱን ይፋ አደረገ። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ ሐምሌ 29 /2010 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት በ3 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የ13 ንፁሀን ዜጎች ህይወት ማለፋንና በ42 ቤቶች ላይ ቃጠሎና ዝርፊያ መካሔዱን ገልጿል። ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ 4 ግለሰቦች በቤት ቃጠሎ፣ 21 ግለሰቦች ደግሞ በቀጥታ በግድያው መሳተፋቸው ...

Read More »