በኦሮሚያ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማን ተከትሎ ከወዲሁ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 16/2009)በኦሮሚያ ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ የሚካሄደው በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች ከወዲሁ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ተሰማ። የአውቶቡስ መናሃሪያዎች የነገውን የስራ ማቆም አድማ በመቱ አውቶብሶች ተጨናንቀዋል። አድማውን አብዛኛው የኦሮሚያ አካባቢ ተግባራዊ እንደሚሆንም ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። በወጣቶች የተጠራውን አድማ በመቀላቀል በርካታ ከተሞች ጥሪውን እየተቀበሉ ነው። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል የተከለሰው የቁቤ መጽሀፍ ተግባራዊ እንዳይደረግ ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል። ...

Read More »

በአዲስ አበባ የጤፍ ዋጋ መወደዱ ሕብረተሰቡን በእጅጉ እያማረረ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 16/2009) በአዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጤፍ ዋጋ መወደዱ ሕብረተሰቡን በእጅጉ እያማረረ መሆኑ ተገለጸ። በተለይም የሕዝብ የገቢ አቅም እያሽቆለቆለ ባለበት ሁኔታ የጤፍ ዋጋ መወደዱ የቤተሰብ መናጋት እየፈጠረ መሆኑን በሀገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች ገልጸዋል። በአዲስ አበባ በተያዘው ክረምት የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከ3 ሺ ብር በላይ መሆኑ ታውቋል። መስከረም በየነ በልደታ አካባቢ የምትኖር የአራት ሕጻናት እናት ናት።የቤት እመቤት የሆነችውን ...

Read More »

እግድ በተጣለባቸው የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው ገንዘብ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 16/2009) ከሌብነት ጋር በተያያዘ እግድ በተጣለባቸው የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ ውስጥ የተገኘው ገንዘብ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በቢሊየን ብር የኮንስትራክሽን ስራዎችን በሚያንቀሳቅሱት በነዚህ ኩባንያዎች የባንክ አካውንት ውስጥ የተገኘው ከፍተኛው ገንዘብ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በታች እንደሆነም ተመልክቷል። ከ50 የሚበልጡ ዝቅተኛና መካከለኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ በፍርድ ቤት እግድ የወጣባቸው ከ200 የሚበልጡ ...

Read More »

ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 16/2009) ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማስገደድ ወይንም በማስወገድ በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ሕዝብን ያማከለ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ ሕልውና ከምንጊዜውም በላይ በፈተና ውስጥ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅትም የተቃውሞ ሃይሎችም መተባበር እንደሚገባቸው አመልክቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ከነሐሴ 12 እስከ 14/2009 በዩኤስ አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ከተማ ባካሄደው 4ኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ባወጣው ...

Read More »

በባህርዳር ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች በመታሰር ላይ መሆናቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 15/2009)በባህርዳር ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች በመታሰር ላይ መሆናቸው ታወቀ። በተለያዩ ክፍለከተሞች በሚገኙ የቀበሌ እስር ቤቶች ከ500 በላይ ነጋዴዎች ታስረው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የባህርዳር ፖሊስ ቦምብ ያፈነዱትን ይዣለሁ በማለት የጀመረው የቪዲዮ ቀረጻ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ በክልሉና በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚቀርብ ታውቋል። በሌላ በኩል በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ጥብቅ ፍተሻ ሲደርግ ውሏል። በባህርዳር ነዋሪው የሌሊት ጥበቃ ሮንድ በፈረቃ እንዲደርሰው ሊደረግ ...

Read More »

በአሜሪካ ታላቅ የተባለ የጸሐይ ግርዶሽ ተከሰተ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 15/2009)በአሜሪካ ታላቅ የተባለ የጸሐይ ግርዶሽ ተከሰተ። ጸሐይ ሙሉ በሙሉ በጨረቃ የተሸፈነችበት ግርዶሽ በተለይ በአሜሪካ ምእራብ ዳርቻ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ለመመልከት ታድለዋል። በአሜሪካ ኦሪጎን፣በደቡብ ካራሎይና ቻርልስተን የጸሀይ ግርዶሹን ሙሉ በሙሉ ለመመልከት ብቻ በሚሊየን የሚቆጠሩ ጉብኚዎች መገኘታቸውን የአለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሜሪላንድ በሚገኘው የሕዋ አየር ሁኔታ ምርምር ጣቢያ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ጥላዬ ታደሰ እንደገለጹት ጨረቃ በምድርና ጸሃይ መካከል ሙሉ በሙሉ ...

Read More »

በኦሮሚያ ወጣቶች የተጠራውን ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 15/2009) በኦሮሚያ ወጣቶች የተጠራውን ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አለምአቀፍ ድጋፍ ቡድን ጥሪ አቀረበ። ከነገ በስቲያ እሮብ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚቆየውና በመላው ኦሮሚያ የተጠራው አድማ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የግብር ጫናን በመቃወምና በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በልዩ ፖሊስ የተጨፈጨፉ ሰዎችን ለማስታወስ ነው። የኦፌኮ አለምአቀፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ ኔጌሳ ኦዶ በተለይ ለኢሳት ...

Read More »

የጋምቤላ ክልል ለብሔረሰቦች በዓል የተበደረውን 346ሚሊየን ብር ከዓመታዊ በጀቱ እየከፈለ መሆኑ ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 15/2009)የጋምቤላ ክልል ባለፈው ዓመት ለተከበረው የብሔረሰቦች በዓል የተበደረውን 346ሚሊየን ብር ከዓመታዊ በጀቱ እየቀነሰ መክፈል መጀመሩ ታወቀ። የመንግስት ልሳን አዲስ ዘመን ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ባለስልጣንን አነጋግሮ እንደዘገበው ለ10ኛው የብሄረሰቦች በዓል ከፌደራል መንግስት የተበደረውን ብር በየዓመቱ ከሚሰጠው በጀት እየቀነሰ ተመላሽ ማድረግ ጀምሯል። የዘንድሮው የብሔረሰቦች ቀን በአፋር ክልል ሰመራ የሚከበር ሲሆን ለበዓሉ ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮች 1.6 ቢሊየን ብር መመደቡ ተገልጿል። ብሩ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውጤታማ አለመሆናቸው አንድ ጥናት አመለከተ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 15/2009)በኢትዮጵያ የታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውጤታማ አለመሆናቸውን በአቶ አባይ ጸሃዬ የሚመራው ተቋም ያጠናው ጥናት አመለከተ። በፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል የተካሄደው ጥናት በስኳር፣በቤቶች ግንባታ፣በመንገድና ትላልቅ የመስኖ ፕሮጀክቶች የታቀዱ ስራዎች መውደቃቸውንና ከፍተኛ የህዝብ ንብረቶች ዝርፊያና ውድመት ማስከተላቸውን በኢሳት እጅ የገባውና በባለ 327 ገጹ ሪፖርት አመልክቷል። ከነዚህ ካልተሳኩ ፕሮጀክቶች ጋርም ተያይዞ 77 ቢሊየን ብር አላግባብ መባከኑን ጥናቱ አመልክቷል። የመንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች ...

Read More »

በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች በህቡዕ በመንቀሳቀስ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡእ ጀምሮ ለ5ቀናት የሚቆይ አድማ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በሌላ በኩል በአማራ ክልል በተለይም ባህርዳርን ጨምሮ በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ሌላ ዙር አድማና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊደረግ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ለነሃሴ 10 ተራዝሞ በነበረው የግብር ...

Read More »