በምዕራብ ጉጂ 33 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀመሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011)በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ መመለሳቸው ተነገረ። በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑንም የምዕራብ ጉጂ  ዋና አስተዳዳሪ መግለጻቸው ተዘግቧል። ይሕ በእንዲህ እንዳለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በንፁሃን ዜጎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ 60 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ስጋቶችንም ያዘለ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011)በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ተስፋን ይዞ የመምጣቱን ያህል በተቃራኒው ስጋቶችንም ያዘለ እንደሆነ በአፅንኦት መገምገሙን የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ኢሕአዴግ በመግለጫው እንዳለው ለዉጡ አሁንም ህዝባዊ መሰረት ይዞ በኢህአዴግ እየተመራ ያለ ቢሆንም በፀረ ለውጥ አስተሳሰብ አራማጆች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት እየፈጠሩ ናቸው። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ላለፉት 3 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በድርጅቱ ውስጥም ሆነ በለዉጡ ...

Read More »

ኦነግ የአየር ድብደባ ተፈጽሞብኛል አለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) በምዕራብ ኦሮሚያ ምንም አይነት የአየር ድብደባ አለተፈጸመም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ያወጣውን መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አስተባበለ። በቄለም ወለጋ ዞን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲል ኦነግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትናንትናው ዕለት  በቃል-አቀባዩ ብልለኒ ስዩም በኩል በምዕራብ ኦሮሚያ ጦሩ ያካሄደዉን የአየር ድብደባ  የለም በሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር። ይህም ሆኖ ግን የኦሮሞ ...

Read More »

መንግስት ወደ ማይፈለገው ወታደራዊ ርምጃ እየተገፋፉ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) በሕዝብ መካከል ተሰግስገው ግጭቶችና ትንኮሳዎች በየአካባቢው ለማቀጣጠል ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ አንዳንድ አካላት መንግስት ወደ ማይፈለገው ወታደራዊ ርምጃ እየገፋፉት ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስቲሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ትላንት የት ነበርን ዛሬስ ወዴት እየሄድን ነው በሚል ርዕስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ባስተላለፈው መልዕክት እዚህም እዚያም ከለውጡ ጋር አብረው የማይሄዱ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው ብሏል። እነዚህ ጊዜያዊ ችግሮች ግን የለውጡን ሂደት ...

Read More »

የከተራ በዓል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) የከተራ በዓል ዛሬ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ። ታቦታትም ከአድባራት ወተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደየ ጥምቀተ ባህሩ ተወስደዋል፡፡ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጥምቀተ ባህር ከደረሱ በኋላም አዳራቸውን በዚያው አድርገው በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከናውነዋል። የከተራ በአሉ በደመቀና በአሰደሳች ሁኔታ እንዲከበር ወጣቶች አካባቢዎቻቸውን በማጽዳት አርአያነት ያለው ተግባር አከናውነዋል። በዓሉ ...

Read More »

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰ ግጭት 900 ያህል ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ በምርጫ ዋዜማ በተቀሰቀሰ ግጭት 900 ያህል ሰዎች በሶስት ቀናት መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮ ትላንት እንዳስታወቀው በሰሜን ምዕራብ ኮንጎ በሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭትና በተከተለው እልቂት ሳቢያ በአካባቢው የሚደረገው ምርጫ እንዲራዘም ምክንያት ሆኗል። ባኑና ባቲንዲ በተባሉ ጎሳዎች መካከል በ4 ቀበሌዎች ውስጥ በተከተለው ግጭት 900 ያህል ሰዎች ከመገደላቸው በተጨማሪ ...

Read More »

በኢትዮጵያ 36 ሚሊየን ህጻናት በከፋ ድህነት እየተሰቃዩ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011)በኢትዮጵያ እድሜአቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 36 ሚሊየን ህጻናት በከፋ ድህነት እንደሚሰቃዩ ተገለጸ። በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣንና በዩኒሴፍ ትብብር በተዘጋጀ አንድ ጥናት ላይ እንደተመለከተው ከ41ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ህጻናት 88በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ የድህነት መለኪያዎች አደጋ ውስጥ ናቸው። ጥናቱ በዘጠኝ የድህነት ማሳያ መስፈርቶች ውስጥ ቢያንስ በሶስቱ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንዳሉ የሚጠቁም እንደሆነ አመላክቷል። በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ የወደፊት የኢኮኖሚ ብልጽግናና የማህበራዊ ...

Read More »

የአድዋን ድል ኢትዮጵያውያን በየተሰማሩበት መስክ መድገም አለባቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011)የአድዋን ድል ኢትዮጵያውያን በየተሰማሩበት መስክ መድገም እንዳለባቸው አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ገለጸች። አትሌት ደራርቱ  የአድዋን ድል ለመዘከር በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ መዘጋጀቷንም አስታውቃለች። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከአድዋ ድል መታሰቢያ አንድ ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ላይ አትሌት ደራርቱ የምትሳተፍ ሲሆን 500 ሜትሩን ያለጫማ ለመሮጥ ወስናለች። የዚሁ ውድድር አምባሳደር ተደርጋ ...

Read More »

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል ነው ተባለ

          (ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011) በቀደሞው የደህንነት ሃላፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የስልጣን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል እንደነበር ተገለጸ።           የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንደገለጹት እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ላይ ማጣራት እየተካሄደና ርምጃም እየተወሰደ መሆኑም ታውቋል።           በዚህም በሶስት ሺ ዜጎች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ተመልክቷል።           ከሀገር መውጣትና ወደ ሀገር መግባት ...

Read More »

የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር ዋለች

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011) የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር መዋሏን የቴሌቭዥን ጣቢያው አስታወቀ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርምጃውን አውግዟል። ዕሁድ ዕለት በሴንት ሉዊስ ከተማ ሴንት ሉዊስ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለችው የ59 ዓመቷ አሜሪካዊት ማርዚ ሐሺሚ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም። በትውልድ አሜሪካዊት የሆነችውና ዕምነቷን ወደ እስልምና ከመቀየሯ በፊት ሜላት ፍራንክሊን በመባል የምትታወቀው ማርዚ ሐሺሚ ለአራት መንግስታዊ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች በእንግሊዘኛ ...

Read More »