ሁለት ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች በቦርድ ሊቀመንበርነት ተሰየሙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2011) ለኢትዮጵያ ግዙፍ መንግስታዊ የፋይናንስ ተቋማት ሁለት ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች በቦርድ ሊቀመንበርነት ተሰየሙ። ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተባበሩት መንግስታት የሚሰሩት ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመረጡ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ሪጅናል ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ መመረጣቸው ታውቋል። የመንግስት የገንዘብ ተቋማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዳይሬክተር እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ በማክሮ ኢኮኖሚስትነት ሲያገለግሉ ቆይተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የተቀላቀሉት ዶክተር ...

Read More »

በኢሳና አፋር ብሄረሰቦች ግጭት 8 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2011) በኢሳና አፋር ብሄረሰቦች መካከል የተከሰተው ግጭት ቀጥሎ በዛሬው ዕለት 8 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። ከአዲስ አበባ እስከጅቡቲ በተዘረጋው መንገድ ላይ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የሁለቱ ወገኖች ግጭት ሲካሄድባቸው እንደዋለ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ገዳማይቱ ላይ በተካሄደ ግጭት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ከሮማ በተሰኘች መንደር የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። ከሰኞ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የአፋርና የኢሳዎች ግጭት ወደ ሰላሳ የሚጠጋ ሰው መገደሉን ...

Read More »

ድንበር ተሻግረው የገቡ ሃይሎች 22 ኢትዮጵያውያንን ገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2011)በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር የተሻገረ የታጠቀ የውጭ ሃይል ጥቃት ከፍቶ 22 ኢትዮጵያውያንን ገደለ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የድንበር ከተማ ገሃንዳሌ ላይ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 50 ሰዎች ቆስለዋል። ትላንት ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ወረራ በፈጸመው የውጭ ሃይል ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የገሃንዳሌ ነዋሪዎች አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ቢኖርም ዜጎችን ከጥቃት መከላከል እንዳልቻለ ግን ተገልጿል። እንደወትሮው የጎሳ ...

Read More »

በአሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ሕይወቱ አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) በአሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ስደተኛ ትላንት ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ። በፈረንጆቹ የገና በአል ሕይወቱ ያለፈው የ8 አመቱ ታዳጊ የጓቲማላው ተወላጅ ፍሊፕ ጎሜዝ በዚህ ወር በአሜሪካ ወህኒ ቤት ሕይወታቸው ያለፈውን ታዳጊዎች ቁጥር ወደ 2 ከፍ አድርጎታል። የታዳጊውን ሕልፈት ተከትሎ የአሜሪካ የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሰራሩን በመከለስ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል። ሆስፒታል ቆይቶ ሲመለስ ህመሙ የተባባሰበት የ8 አመቱ ታዳጊ ...

Read More »

አመፅና የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን ያወድማል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ17/2011) አመፅና የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን ስለሚያወድም በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ አይደለም ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ገለጸ። የንቅናቄው ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅቱ ከአመፅ ነፃ በሆነ በሰላማዊ መንገድ መታገልን ብቻ የሚጠይቅ ነው ብለዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመፅ እና ትጥቅን መሰረት ያደረገ ትግል ኢትዮጵያን ወደ ውድመት ከመምራት በስተቀር ሌላ ጥቅም የለውም ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል። ንቅናቄው ይሕንኑ በመረዳቱም ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአፍሪካ አህጉር ታሪክ የሰሩ ተባሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) እየተገባደድ ባለው 2018 በአፍሪካ አህጉር ታሪክን ከሰሩ ሰዎች የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ። ጋናዊቷ ጋዜጠኛ ኤልዛቤት ኦህኒ ዛሬ ቢቢሲ ላይ ባቀረበችው ዘገባ ዶክተር አብይ አህመድ ጸሃይን በምዕራብ የማውጣት ያህል አይቻልም የተባለውን በአጭር ጊዜ ከውነዋል በማለት ምስክርነቷን ሰጥታለች። በለየለት አምባገነን ስርዓት የምትተቻቸውንና ከኤርትራ ጋር በፍጹም ጠላትነት ውስጥ የቆየችውን ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሌላ ...

Read More »

በወልቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ የሚመስል ነገር ተሰርቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ በወለቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት የማወጅ ያህል ነው ሲሉ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለኢሳት ተናገሩ። ጥያቄያችን የረጅም ዓመታት ጥያቄ ነው ያሉት  ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ህጉን ተከትለን የማንነት ጥያቄያችንን ካቀረብን  ከሶስት ዓመታት በላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም ወይዘሮ ኬሪያ የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ ...

Read More »

በኢሳና አፋር ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት 18 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) በኢሳና አፋር ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት 18 ሰዎች መገደላቸው ተገደሉ። ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱ ወገኖች ተካሄደ በተባለውና በመሳሪያ በታገዘው  ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ የገዋኔና አዋሽ አካባቢ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ የኢትዮጵያ መንግስት የአፋር ንጹሃንን ህይወት እንዲታደግ በሚል መግለጫ አውጥቷል። አርዱፍ በግጭቱ ከኢሳዎች ጀርባ የጅቡቲ መንግስት የመሳሪያ ድጋፍ ያደርጋል ሲል ከሷል። ግጭቱ ...

Read More »

በኢንዶኔዥያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 አሻቀበ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)ኢንዶኔዥያን በመታው አውሎ ንፋስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ሲያሻቅብ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1ሺህ መብለጡ ታወቀ። በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም። በእሳተጎመራና በመሬት መደርመስ ጭምር የተዘጋው አውሎ ነፋስ የሙዚቃ ኮንሰርት በማሳየት ላይ የነበሩ ሙዚቀኞችን ጭምር ከመድረክ ጠርጎ ሲሄድ ታይቷል፣ ህንጻዎችም ፈራርሰዋል። 265 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ የሚኖርባትና 17ሺህ ያህል ደሴቶች የሚገኙባት ኢንዶኔዢያ በሳምንቱ መጨረሻ በገጠማት አደጋ ዋነኛው ...

Read More »

አቶ ፍጹም አረጋ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 15/2011)በአሜሪካ ዋሽንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ በቆዩት በአቶ ካሳ ተክለብርሃን ምትክ አቶ ፍጹም አረጋ መሾማቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። እንዲሁም ለ27 ዓመታት በሕዉሃት ሰዎች ብቻ በርስትነት ተይዞ በቆየው ቻይና ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋ በአምባሳደርነት መሾማቸውም ተመልክቷል። በአጠቃላይ 59 ያህል ዲፕሎማቶች በተለያዩ ሃገሮች የተመደቡ ሲሆን የእነዚህ ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል። ቀደም ሲል ከተመደቡት 59 ሰዎች ውስጥ በሰብዓዊ መብት ...

Read More »