በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መደበቅ ችግር እየፈጠረ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011)በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መደበቅና እንዳይያዙ ከለላ መስጠት በአሰራሩ ላይ ችግር እየፈጠረበት መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ገለጸ። ወንጀሎችን ከተደበቁበት ለማውጣትና ለህግ ለማቅረብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድጋፍ እንዲሰጥ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ጠይቀዋል። የተወካዮች ምክርቤት የጠቅላይ አቃቤህግ የ5 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ...

Read More »

በአርሲ ነጌሌ ከ30 በላይ ሱቆች ታሸጉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2011) በአርሲ ነጌሌ ከ30 በላይ ሱቆች እንዲታሸጉ የከተማው አስተዳደር ውሳኔ አስተላለፈ። ባለሱቆቹ ህጋዊ መሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ቢያቀርቡም የከተማው አስተዳደር ሱቆቹ ለሌሎች የሚሰጥ በመሆኑ በአስቸኳይ ለቃችሁ ውጡ ተብለዋል። ላለፉት ስድስት ወራት በከተማው አስተዳደርና በወጣቶች ከፍተኛ ጫና ሲደረግባቸው የነበሩት ባለሱቆቹ ለ20 ዓመታት በህጋዊነት ሲሰሩባቸው የነበሩት ሱቆች ከእሁድ ጀምሮ ታሽገውባቸዋል። የከተማዋ ሌሎች ነጋዴዎችም በማንነታችን የተነሳ የከተማው አስተዳደር የሚያደርግብን ጫና በመጨመሩ ከተማዋን ...

Read More »

ግብጽ በአሸባሪዎች ላይ ጥቃት ከፈተች

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 22/2011) በግብጽ በሳምንቱ መጨረሻ በአንድ የቱሪስት አውቶቡስ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ግብጽ በአሸባሪዎች ላይ ጥቃት መክፈቷን ገለጸች። በዚህም ጥቃት 40 ያህል መገደላቸውንም ይፋ አድርጋለች። ባለፈው አርብ ጊዛ በተባለው የግብጽ የቱሪስት መናሃሪያ በመንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ በአንድ የቱሪስቶች መጓጓዣ ላይ ባደረሰው ጉዳት ሶስት የቬትናም ዜጎች ተገድለዋል። እንዲሁም አንድ ግብጻዊ አስጎብኚም በተመሳሳይ ሕይወቱ አልፏል። ለዚህ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደ ወገን ...

Read More »

ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተፈናቀሉ የአማራ ተማሪዎች ሊመለሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 22/2011) በኦሮሚያ ክልል ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተፈናቀሉ የአማራ ተማሪዎች ሁኔታዎች ሲመቻቹ ወደ ትምህርታቸው እንደሚመለሱ የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ጥር 1 እና 2 ተማሪዎችን ለመመለስ እቅድ መያዙም ታውቋል በቡሌ ሆራ  እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ዩኒቨርሲቲው  በሴኔቱ ስምምነት ለጥቂት ቀናት እንዲዘጋ ተወስኗል ፡፡ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ  ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረ የሰላም እጦት ምክንያት ወደ የመጡበት አካባቢ ተመልሰዋል፡፡ ...

Read More »

በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ውስጥ አደገኛ መርዝ አለ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 22/2011)በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ውስጥ አደገኛ መርዝ መኖሩን የተቋሙ ሰራተኞች የነበሩ እስረኞች ገለጹ። ይህንኑ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ያሳወቀ ሲሆን የመርዙ አይነትና አደገኝነት በባለሙያ እየተመረመረ መሆኑም ተመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የኦነግና የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትን ማሰርና ማሰቃየት  ህጋዊ አሰራር ስለነበር ልንጠይቅ አይገባም ሲሉ ታሳሪ የደህንነት አባላት መናገራቸውን ሪፖርተር በዘገባው አስፍራሯል። በሌላም በኩል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ...

Read More »

በሱዳን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ጋዜጠኞችም ተቀላቀሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2011) በሱዳን የተቀሰቀሰውና ካሳምንት በላይ የቀጠለውን ተቃውሞ ጋዜጠኞችም መቀላቀላቸው ተሰማ። የሱዳን መንግስት የተቃውሞ እንቅስቃሴውን እንዳንዘግብ ጫና እያደረገብን ነው ያሉ ጋዜጠኞች ከሃሙስ ጀምሮ አድማ ሲመቱ አንዳንድ የውጭ ሃገር ዘጋቢዎች ከሃገር እንዲወጡ ታዘዋል። የሱዳን መንግስት ዓመጹን የእስራኤልን መንግስት እጅ አለበት በማለት በይፋ መግለጫ ሰቷል። የሱዳን ጋዜጠኞት ኔትወርክ (SJN) ትናንት ሃሙስ እንዳስታወቀው መንግስት የጋዜጠኞችን ስራ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም የሶስት ቀናት ...

Read More »

የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጪው ሚያዚያ ሊካሄድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2011)በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት የነበረው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጪው ሚያዚያ ሊካሄድ መሆኑን ኤጀንሲው አስታወቀ። የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የሕዝብና የቤት ቆጠራን ለማካሄድ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊየን ብር እስካሁን ድረስ ወጭ ተደርጓል። የሕዝብና የቤት ቆጠራው በሕገ መንግስቱ መሰረት በየ10 አመቱ መካሄድ ቢኖርበትም በኢትዮጵያ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት መካሄድ ከነበረበት ጊዜ ሁለት አመት አልፎታል። የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የሕዝብና የቤት ቆጠራውን ባለፈው ...

Read More »

አባ ገዳዎች ወደ ወለጋ ሊሄዱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2011)የኦሮሞ አባ ገዳዎች ወደ ወለጋ ሊሄዱ መሆኑ ተገለጸ። በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የተከሰተውንና በርካታ ሰዎች ለተገደሉበት ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ አባገዳዎቹ በመጪው ሳምንት እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል። ግጭቱ በሚካሄድባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ካሉ የህበረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት መፍትሄ ለማግኘት እንደሚጥሩም ተገልጿል። በወለጋ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የጸጥታ ስጋት ፈጥሯ ሲል መንግስት እየከሰሰ ነው። ኦነግም ራሴን ለመከላከል ርምጃ ወስዳለሁ ብሏል። ለወራት በዘለቀው የሰላም ...

Read More »

ብጹዕ አቡነ መልከጸዲቅ እሑድ አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2011)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ የነበሩት ብጹዕ አቡነ መልከጸዲቅ እሑድ አዲስ አበባ ይገባሉ። ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በስደት የቆዩት ብጹዕ አቡነ መልከጸዲቅ ከጤና ጋር በተያያዘ ከፓትርያሪክ አቡነ መርቆርዮስ ጋር ለመመለስ አለመቻላቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በሐምሌ ወር 2010 በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ዕርቅ ሲያደርጉ ከካሊፎርኒያ ወደ ዋሽንግተን የመጡትና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ...

Read More »

በሱዳን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2011)በሱዳን በዳቦና በነዳጅ ዋጋ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ፕሬዝንዳቱ ከስልጣን ይውረዱ የሚል ጥያቄን ይዞ መቀጠሉ ተሰማ። የሱዳን የህክምና ባለሙያዎች ተቃውሞውን በመቀላቀል የስራ አድማ የመቱ ሲሆን የህክምና ተማሪዎችም ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። በዋና መዲናዋ ካርቱም በትላንትናው ዕለት በተካሄደው ተቃውሞ 9 ሰዎች መጎዳታቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በምስራቃዊው የሱዳን ግዛት በገዳሪፍ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩት ተማሪዎች ትናንት ረቡዕ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ዩኒቨርስቲውን ...

Read More »