በሞያሌ ከ80ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2011) በሞያሌ ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ እንደአዲስ ባገረሸው ግጭት ከ80ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። በግጭቱ የተፈናቀሉት አብዛኞቹነዋሪዎች በአቅራቢያ ባሉ ወረዳዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ነው ለማወቅ የተቻለው። አንደኛ ሳምንቱን የደፈነው ግጭት ከትላንት ጀምሮ ጋብ ያለ ቢመስልም የተኩስ ድምጽ በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች እንዳለ ተገልጿል።           በሞያሌ ከህክምና መስጪያ ማዕከላት ውጪ የከተማዋ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መቆሙንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የቦረና ዞን የመንግስት ...

Read More »

አሜሪካ በደቡብ ሱዳን በሶስት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) አሜሪካ በደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸውን አስገብተዋል ያለቻቸውን የእስራኤል የጦር ጄኔራል ጨምሮ በሶስት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች። ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች መሆናቸውምታውቋል። በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባትና ቀውሱን በማባባስ በሃገሪቱ ለተከሰተው ለ400 ሺህ ሰዎች ዕልቂት አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉትን እስራኤላዊ ጡረተኛ ጄኔራል እስራኤል ዚቭ ሶስት ኩባንያዎች ላይም የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ መጣሉን ኢየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። እስራኤል ...

Read More »

በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ የተገኙ አዳዲስ መረጃዎች ይፋ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/ 2011) መርማሪ ፖሊስ በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ የተገኙ አዳዲስ ተሳትፎዎችን ይፋ አደረገ። በቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ በምርመራ ወቅት ያገኛቸውን አዲስ የወንጀል ተሳትፎዎች ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። መርማሪ ፖሊስ እንደገለጸው ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ከሕዳሴው ግድብ እና ከልዩ ልዩ ዓለምአቀፍና የሀገር ውስጥ ተቋማት ጋር ያደረጓቸው ውሎች እንዲሁም የተከፈሉ ገንዘቦች ...

Read More »

ሶስት ሃገራት የዲሞክራሲ ርምጃ አሳይተዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 09/2011) በዓለማችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት ሃገራት በ2018 የዲሞክራሲ ርምጃ ማሳየታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ። ለዲሞክራሲ እጅግ ፈታኝና አደገኛበሆነውና አምባገነኖች ይበልጥ አፋኝ ሆነው በወጡበት በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ እጅግ አስደናቂ ሁኔታ ተከስቷል ስትል በዋሽንግተንፖስት ላይ ጽሁፏን ያቀረበችው ፍረዳ ጊቲስ በትግራይ የበላይነት ስር የቆየው ዘረፋና ስርዓት በዚህ ዓመት ማብቃቱን አመልክታለች። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ በሚኖሩ ...

Read More »

በጉራጌ ዞን የየወረዳ አስተዳዳሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በጉራጌ ዞን ማረቆና መስቃን ወረዳዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት የየወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች እጅ አለበት በሚል በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገለጸ። በክልል ደረጃ በደኢህዴን ውስጥየሚገኙና የግጭቱ ዋና አቀናባሪዎችን ያልነካ እስር ችግሩን አይፈታውም ሲሉ ነዋሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው። የደቡብ ክልል ፖሊስ የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪን አቶ በለጠ ደራሮንና የመስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታህ ሸምሱን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባሳወቀበት መግለጫው ግጭቱን በመቀስቀስና በማባባስ ...

Read More »

በሞያሌ በትንሹ 12 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በሞያሌ በሚገኘው የበቀለ ሞላ ሆቴል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 12 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ጥቃቱ የተፈጸመው የቦረና ኦሮሞና የሶማሌ ገሪ ብሄረሰብተወካዮች ከፌደራል መንግስቱ ሰራዊት አመራሮች ጋር ውይይት እያደረጉ በነበረ ጊዜ መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ የተሰኘ የዜና ምንጭእማኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በጥቃቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሳተፋቸውም ተገልጿል። በሞያሌ ሳምንቱን በደፈነውና እንደአዲስ ባገረሸው ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። የሞያሌው ግጭት መነሻው ...

Read More »

በኢየሩሳሌም ጎለጎታ የሃይማኖት አባቶች ተደበደቡ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በኢየሩሳሌም ጎለጎታ ግቢ ውስጥበሃይማኖት አባቶች ላይ ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ። በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ በሚካሄድ ስብስባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት አባቶቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ መፈጸሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ብጹእ አቡነ እምባቆምን ጨምሮ ሶስት አባቶች በተፈጸመባቸው ድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ድብደባውን የፈጸሙት የህወሀት ደጋፊ የሆኑ ሶስት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ሲሆኑ በእስራዔል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ...

Read More »

ሕገ-መንግስትን መጣስ ዛሬ የተጀመረ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) በኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ-መንግስት መጣስም ሆነ በክልሎች ጣልቃ መግባት ዛሬ የተጀመረ አይደለም ሲሉ ሌተናል ጀኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ገለጹ። ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች የፖለቲካስልጣኑን በበላይነት ይዘው ሕገ-መንግስቱን እየጣሱ ሕግ ሳይገዛቸው የቆዩበት ሁኔታ ዛሬ ለተከሰተው ችግር አስተዋጽኦ ማድረጉንምጄኔራሉ አመልክተዋል። የሕዉሃት ነባር ታጋይ እና በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን እስከ ግንቦት ወር 1993 የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም የነበሩት ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ...

Read More »

በኮንጎ ዴሞክራቲክ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከፍተኛ ውጥረት አነገሰ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011)በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመጪው ዕሁድ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሃገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት መፍጠሩ ተሰማ። አሜሪካ ዜጎቿ ከርዕሰ መዲናዋኪንሻሳና ሌሎች ከተሞች ለቀው እንዲወጡ ያሳሰበች ሲሆን ብሪታኒያ ዜጎቿ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዳይገቡ ማስጠንቀቂያሰጥታለች። ላለፉት 17 ዓመታት በመሪነት የቆዩትን ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላን ለመተካት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከፊታችን እሁድ ታህሳስ 23 የሚካሄደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተቀናቃኝ ወገኖች ጥሪ አቅርቧል። ...

Read More »

ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ያቀኑት ወታደሮች ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 8/2011) ወደ ቤተ መንግስት ያለፈቃድ ካቀኑ ወታደሮች ውስጥ 66ቱ ላይ የተላለፈባቸው ዝርዝር ቅጣት ይፋ ሆነ። ከነትጥቃቸው ያለፈቃድ ወደ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ካመሩት 200 የሰራዊት አባላት መካከል 66ቱ ላይ ከ5 እስከ 14 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ፋይል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ከ500 ሰው በላይ በተገኘበት ግልጽ ችሎት  መታየቱ ታውቋል። በውሳኔው መሰረት አንድ ተከሳሽ በ14 ዓመት ጽኑ ...

Read More »