በአዲስ አበባ ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011) በአዲስ አበባ ከተማ በ8 ቡድኖች ተደራጅተው በጦር መሳሪያ የተደገፈ ከባድ የወንጀል ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የነበሩ 48 ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውኝ የከተማዋ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ በተለይም በኮልፌ ቀራንዮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በየካ፣ ቦሌ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በቡራዩ፣ በሰበታና በሆለታ አካባቢ በሌሊት ዘረፋ እየተስፋፋ መምጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በውጭ ሀገር ዜጎች፣ በባለሀብቶችና በመንግስት ...

Read More »

የቡራዩ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011) በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ መያዙን የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ትናንት ሌሊት መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል  ። ይሕ በእንዲህ እንዳለም ከጋምቤላ ክልል ወደ አማራ ክልል በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ በፀጥታ አካላት ጥምረት በቑጥጥር ስር ውሏል። 105 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ነው። የቡራዩ ከተማ ...

Read More »

በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011) በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ከእነዚሁ አስቸኳይ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው መካከል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ናቸው ። ለዚሁ እርዳታ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገም ተገልጿል። የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሰታት ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከ51 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011) በአዲስ አበባ ዛሬ ከ51 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ። እጣ ከወጣባቸው ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች የ20/80 ቤቶች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው። ቤቶቹ በኦሮሚያ ክልል ስለሚገኙ ለአዲስ አበባ ነዋሮዎች ሊሰጥ አይገባም የሚሉ ብሄርተኞች በአካባቢው አደጋ እናደርሳለኝ እያሉ እየዛቱ መሆናቸውኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በኢትዮጵያ ባለፉት ...

Read More »

ልሳነ ግፉአን የህዝብና ቤት ቆጠራ መካሄዱን እቃወማለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011)በወልቃይት፣በጠገዴ፣በጠለምት፣በራያና አካባቢው የሚደረግን ማንኛውንም አይነት የህዝብና ቤት ቆጠራ አጥብቆ እንደሚቃወም የልሳነ ግፉአን ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የህዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም ጠይቋል። ወደዚህ ስራ ከመገባቱ በፊትም እንደሃገር የሚታዩ ችግሮችን መላው ህዝብ፣የለውጥ ሃይሉና የሚመለከታቸው አካለት ግልጽና የማያዳግም ርምጃ እንዲወስዱም ጥሪውን አቅርቧል። ልሳነ ግፉአን ድርጅት ባወጣው መግለጫው እንደ ሃገር እየታዩ ያሉና መፍትሄ ሊቀመጥላቸው ያልቻሉ ጉዳዮችን ...

Read More »

የሕግ አስከባሪ አካላት የጦር መሣሪያ ዓይነትን የሚወሰን ሕግ ተረቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011)ከመከላከያ ሠራዊቱ ውጪ የሆኑ ሕግ አስከባሪ አካላት መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ዓይነት የሚወሰን ሕግ ተረቀቀ ከ21 ዓመት በላይ የሆነ ጤነኛ ሰው ለግለሰብ የሚፈቀድ የጦር መሣሪያ ፈቃድ በማውጣት ሊታጠቅ ይችላል በረቂቅ ሕጉ በጦር መሣሪያ ንግድና በድለላ ለሚሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ይሰጣል። ከአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በስተቀር ሌሎች በክልል መንግሥታትና በፈዴራል መንግሥት የተደራጁ ሕግ አስከባሪ አካላት፣ መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ...

Read More »

የአማራ ክልል ምክር ቤት በጸጥታ ጉዳይ ላይ ሲመክር ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011)የአማራ ክልል ምክር ቤት  ከመደበኛ ጉባኤው በፊት  በጸጥታ ጉዳይ ላይ በማተኮር በዝግ ስብሰባ  ምክክር ሲያደርግ መዋሉ ተነገረ። ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጀምሮ እስከ የካቲት 29 ቀን 2011 እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል ። በዛሬው ስብሰባ ምክር ቤቱ በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርጓል ተብሏል። በተለይም ከትግራይ ክልል በኩል ባሉ ትንኮሳዎችና የጦርነት ስጋት በዚሁም የአማራ ...

Read More »

በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011) በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከ300 በላይ የስልክና የኢንተርኔት መስመሮች እንዲሁም በየዓመቱ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱን በተቋሙ አሰራር ላይ የተደረገ ጥናት አመለከተ። ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በነበረው በ100 ሚሊየን ብር ሲመዘበር ቆይቷል ማለት ነው። በምዝበራው ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 31 ግለሰቦች ላይም እገዳ ተጥሏል። የብሔራዊ ቤተ መንግስት የማያውቀው ከ300 በላይ የስልክና የኢንተርኔት መስመሮችን ጨምሮ ለግለሰቦች በሚውሉ ...

Read More »

ጠፍቶ የነበረው የኡበር ታክሲ አሽከርካሪ ሞቶ ተገኘ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011)በቅርቡ ኡበር ታክሲ በመንዳት ላይ እያለ ጠፍቶ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሙሰባ ባህሩ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኝና ዴልዌር በተባለ አካባቢ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። የ43 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ሙሰባ ባህሩ ባለፈው ጥር ወር የኡበር ታክሲ በምሽት በመንዳት ላይ እያለ ባልታወቀ ምክንያት ተሰውሮ መቆየቱን የዋሽንግተን ዲሲ ፖሊስ አስታውቆ ነበር። የሙሰባ ባህሩ አስከሬንን በማግኝት የተባበረው የዊል ሚንግተን ፖሊስ በኢትዮጵያዊው ሙሰባ ...

Read More »

የአጼ ቴዎድሮስ ጸጉር ለኢትዮጵያ ሊመለስ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011)የእንግሊዝ ሙዚየም  የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ለኢትዮጵያ ለመመለስ መስማማቱ ተገለጸ። ሙዚየሙ የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ለመመለስ ያሰበው በኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ነው ተብሏል። የአጼ ቴዎድሮስ ጸጉር ባለፈው ዓመት  በሙዚየሙ ውስጥ እና በድረገጽ ለዕይታ በመብቃቱ ብዙዎችን ኢትዮጵያውያን  አስቆጥቶ እንደነበር ይነገራል። አጼ ቴዎድሮስ ከ150 ዓመታት በፊት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1968 መቅደላ ላይ ለእንግሊዝ ወታደሮች እጅ አልሰጥም ብለው በጀግንነት መንፈስ ራሳቸውን መግደላቸው አይዘነጋም። ይህንን ...

Read More »