በሞያሌ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 5/2011)በሞያሌ ግጭት ተቀሰቀሰ። ባለፉት ሶስት ቀናት በተደረገ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ያዝ ለቀቅ ሲያደርግ የነበረው ግጭት ከእሁድ ጀምሮ ተጠናክሮ እየተካሄደ መሆኑን የሶማሌ ክልል የፕሬዝዳንቱ የህግ አማካሪ ለኢሳት ገልጸዋል። የህግ አማካሪው አቶ ጀማል ዲሪዬ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ ስለሚችል የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች አስቸኳይ መፍትሄ ማፈላለግ አለባቸው ብለዋል። በግጭቱ 17 ሰዎች መቁሰላቸውንም አቶ ጀማል ገልጸዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ኢሳት ያነጋገራቸው ...

Read More »

የቡና ቱሪዝም ቀንን ለማክበር የወጡት መግለጫዎች አይወክሉኝም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 30/2011) የዘንድሮው የቡና ቱሪዝም ቀንን ለማክበር የወጡት መግለጫዎች አይወክሉኝም ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ዓለም ዓቀፍ የቡና ፕሮግራም በቡና መገኛ ምድር በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን በዓል አስመልክቶ በሳምንቱ መጀመሪያ በተሰራጨው መግለጪያ የቡና መገኛ ጂማ ነው የሚለው አገላለጽ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዛሬ እንዳስታወቀው ከመስሪያ ...

Read More »

የኤርትራው ፕሬዝዳንት በጎንደር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 30/2011) የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። በተመሳሳይ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አብዱላሂም በተመሳሳይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ሶስቱ መሪዎች ጎንደር የተለያዩ ስፍራዎችን ጎብኝተው ከሰዓት በኋላ ባህርዳር ደርሰዋል። የኢትዮጵያ፣የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች በአስመራ የጀመሩትን የሶስትዮሽ ውይይት በበህርዳር ከተማ ለመቀጠል መግባታቸው ተመልክቷዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂን ጎንደር ላይ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ከምክትል ...

Read More »

በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ የጅምላ መቃብር ተገኘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 30/2011) በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ወሰን ላይ የጅምላ መቃብር መገኘቱ ተገለጸ። ፖሊስ እንዳስታወቀው የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ ታማኝ በሆነው የልዩ ሃይል ተፈጸሟል በተባለ ግድያ የ200 ሰዎች አስክሬን በአንድ ጉድጓድ የተቀበረበት የጅምላ መቃብር ተገኝቷል። ግድያው የተፈጸመው በሁለቱ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ወቅት እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ ተጨማሪ የጅምላ መቃብር ለማግኘት ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። አቶ አብዲ ዒሌ በስልጣን ...

Read More »

ከፍተኛ የጦር አዛዦች ተሰናበቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 30/2011) በሰራዊቱ ውስጥ የተጀመረውን የለውጥ ርምጃ ለማጠናከር በርካታ ጄነራሎችን ጨምሮ ከ160 በላይ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ከሰራዊቱ መሰናበታችውን የቅርብ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ጎንደር ከተማ ላይ ትናንት በሰጡት መግለጫ ባለፉት 7 ወራት ከተሰሩ ስራዎች ትርጉም ያለውና መሰረት የረገጠ ስራ የተሰራው በሰራዊቱ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል። የሰራዊቱን አመራር ለማሰባጠር በተወሰደው ርምጃ የተነሱት ወታደራዊ ሃላፊዎች በፈቃደኝነት እንደለቀቁም ገልጸዋል። ባለፉት ...

Read More »

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሰባት ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። ወይዘሪት ብርቱካን አዲስ አበባ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ወይዘሪት ብርቱካን በመንግስት ጥሪ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ እንደሚመደቡም ለማወቅ ተችሏል። ዳኛ ናቸው። ፖለቲከኛም እንዲሁ። በሁለቱም መስኮች የገዘፈ ስም የያዙ፣ ዋጋም የከፈሉባቸው፣በብዙዎች ዘንድ ጥንካሬአቸውና መስዋዕትነታቸው በአርያነት ...

Read More »

ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጣቢያ ልትገነባ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጣቢያ ልትገነባ መሆኗን አስታወቀች። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ምክትል ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ዋና ሃላፊ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በቀይባህርና ህንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ የባህር ሃይል ሰፈር ልትገነባ በዝግጅት ላይ ናት። በአፍሪካ ትልቅና ጠንካራ የባህር ሃይል የነበራት ኢትዮጵያ የህወሃት አገዛዝ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ባህር ሃይሏ መፍረሱ የሚታወስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ...

Read More »

በኦነግ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011)በኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በመንግስት በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። እየታዩ ያሉት ችግሮችም ከዚሁ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን በማመልከትም ጦርነት የሚባል ነገር አሁን የለም ሲሉም አስረድተዋል። ጄኔራል ብርሃኑ እንዳሉትም በቅርቡ ወደ ቤተመንግስት ተጉዘው የነበሩት ወታደሮች  ቤተመንግስቱን ለመበጥበጥና ካገኙም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመግደል አልመው ነበር። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ምክትል ኤታማዦር ሹምና ...

Read More »

የራያዎች አንገብጋቢ ጥያቄ የማንነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የራያዎች ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄ የማንነት እንጂ የልማት አይደለም ሲል የራያ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል ዛሬ በአላማጣ ከተማ  በጠሩት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን ተከትሎ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጸው ማንነቴን መልሱልኝ ያለን ህዝብ በልማት የተስፋ ቃላት ለማዘናጋት መሞከር ከንቱ ድካም ነው ብሏል። ብዙ ከማውራት ብዙ መስራት በሚል መሪ ቃል በዶክተር ...

Read More »

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከስልጣናቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 29/2011) የሀረሪ ክልልን ለ12 ዓመታት ያስተዳደሩት አቶ ሙራድ አብዱላሂ ከስልጣናቸው ተነሱ። በምትካቸው አቶ ኦሪዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው መሾማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሀረሪ ገዢ ፓርቲ ሃብሊ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብን ተከትሎ ከስልጣናቸው የተነሱት አቶ ሙራድ ቤተሰባዊ አስተዳደር በማስፈንና ደጋፊዎቻቸውን በዙሪያቸው በማሰባሰብ ሲወነጀሉ ቆይተዋል። አቶ ሙራድ ከሃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም ለተተኪያቸው አቶ ኦሪዲን ስልጣን ...

Read More »