በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011) በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ።

በወረዳው ምንነቱ ያልታወቀ የጦር ካምፕ መገኘቱ የፈጠረው ስጋትን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ስድስት ታጣቂዎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በጋምቤላ ልዩ ሃይልና በካምፑ በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ለጊዜው ጋብ ቢልም በአካባቢው ህዝብ ላይ ስጋት መደቀኑን የአኝዋክ ሬዲዮ አዘጋጅ አግዋ ጊሎ ለኢሳት ገልጿል።