በሰሜን ሸዋና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን የጦር መሳሪያ ዝውውር ገደብ ተጣለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011) በኮማንድ ፓስት ስር በሚገኙት የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን የጦር መሳሪያ ዝውውር ገደብ መጣሉ ተገለጸ። ሕገ ወጥ የጦር የመሣሪያ ዝውውር በቅርቡ ለተከሰቱት የፀጥታ ችግሮች መንስኤ ናቸው ያለው ኮማንድ ፖስት  ከፌደራልና ከክልል ጸጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ ርምጃ እንደሚወሰድበት አስታውቋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአካባቢዎቹ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ዝውውር ይደረግ እንደነበረ የጠቀሱት የጸጥታ አካላት ...

Read More »

የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ስጋትና ውጥረት ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ/2011)የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ስጋትና ውጥረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ ተጀመረ፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ወደ ስብሰባው ሲገቡ ስልክ ይዞ መግባት ከመከልከሉ ሌላ ከፍተኛ ፍተሻ መደረጉ ታውቋል። ምክር ቤቱ ያለፉትን ወራት የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ አቅጣጫዎች ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በአራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች መካከል የዓላማና የርዕዮት አንድነት መላላት  በመኖሩ  እርስ ...

Read More »

የዊክሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በቁጥጥር ስር ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2011)በለንደን የኢኳዶር ኤምባሲ ለሰባት ዓመታት ተጠልሎ የነበረው የዊክሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በቁጥጥር ስር ዋለ። በምዕራባውያን መንግስታት በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው አሳንጅ ለኢኳዶር መንግስት ያቀረበው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ በእንግሊዝ ፖሊስ እጅ መውደቁን ቢቢሲ ዘግቧል። አሜሪካን አሳንጅ ተላልፎ እንዲሰጣት መጠየቋ የሚታወስ ነው። ጉዳዩን የለንደኑ ዌስት ሚኒስትር ፍርድ ቤት መመልከት መጀመሩ ታውቋል። የኢኳዶር መንግስት በስዊዲን ክስ የቀረበበትን ጁሊያን አሳንጅን ...

Read More »

የሱዳኑ ኦማር አልበሽር ከስልጣናቸው ወረዱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2011)የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣናቸው ተነሱ። እሳቸውን ጨምሮ ሶስት የሱዳን ገዢ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁም እስር ላይ መሆናቸውን ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። የ30 ዓመቱ የአልበሽር አገዛዝ ያከተመው ለወራት የዘለቀው ህዝባዊ አመጽ መቀጣጠሉን ተከትሎ ነው። የሱዳን ጦር ቤተመንግስቱን ጨምሮ ቁልፍ ቦታዎችን መቆጣጠሩም ታውቋል። አልበሽር ለፓርቲያቸው ምክትል የሊቀመንበርነቱን ቦታ መስጠታቸውን ቢያስታውቁም የሱዳን መንግስትን በቀጣይ የሚመራውን የሚወስኑት የጦር ...

Read More »

በከሚሴ ለተፈጸመው ጥቃት ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው ዳግም ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2011)በከሚሴ ለተፈጸመው ጥቃት ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው ዳግም ሊከሰት እንደሚችል ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ። የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት እንደዘገበው ከሰሞኑ የተነሳው ግጭት ወደ ስፍራው በገባው የፀጥታ ኃይልና በአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ ቢረጋጋም ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት እስካልተሰጠው ድረስ ከስጋት ነፃ መሆን እንደማይችሉ የከሚሴ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የጥቃቱ መነሻ በአሉባልታ ሰለባ የሆነው የወረዳው አመራር መሆኑን የሚገልጹት ነዋሪዎች አሁንም አመራሩ ህዝቡ ላይ ስጋት ደቅኖ ይገኛል ...

Read More »

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2011) በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ተገለጸ። ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በፍጥነት በመዛመት የፓርኩን ሰፊ ክፍል ማዳረሱ ታውቋል። የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ባለስልጣናት የፌደራል መንግስቱ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለማስመጣት መንግስት በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ቀደም ሲል ተከስቶ በነበረው ቃጠሎ ከ300 ሄክታር በላይ የፓርኩ ...

Read More »

ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለጸ። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሹመቱ የተሰጣቸው ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት በጡረታ እንደሆነ በተሰጣቸው ደብዳቤ ላይ መገለጹን ሪፖርተር ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኮሚሽነሩ በጡረታ እንዲገለሉ ማድረጋቸውን ከመገለጹ ውጪ ዝርዝር ምክንያት አልተሰጠም። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሃላፊ የኢትዮጵያ ...

Read More »

የጅማ ህክምና ማዕከል የጤና ሰራተኞች የስራ ማቆም አደረጉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011)በጅማ ዩኒቨርሲቲ የጅማ ህክምና ማዕከል የጤና ሰራተኞች የስራ ማቆም አደረጉ። ሰራተኞቹ የስራ ማቆም አድማውን የመቱት ባለፈው እሁድ ሌሊት በማዕከሉ ድንገተኛ ክፍል ባልታወቁ ሃይሎች ሁለት በልምምድ ላይ ያሉ ዶክተሮችን የግድያ ሙከራና በሌሎች ባለሙያዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ምንም ዓይነት የመከላከል ርምጃ አለመወሰዱን የጠቀሱት ሰራተኞቹ ለህይወታቸው ዋስትና ባለመኖሩ ስራቸውን ለማቆም መገደዳቸውን ገልጸዋል። ሰላምን ...

Read More »

በአማሮ ወረዳ ቡኒቲ ቀበሌ የአማራ ክልል ተወላጆች እየተፈናቀሉ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011)በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ቡኒቲ ቀበሌ የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አካባቢውን ለቀው እንዲፈናቀሉ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የተደረገው በቀበሌ አመራሮች ውሳኔ ነው። ባለፈው መስከረም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ከአካባቢው እንድንፈናቀል ተደርገናል የሚሉት ነዋሪዎቹ  አሁንም ጉማይዴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢው መስፈራቸውን ነው የሚናገሩት። ኢሳት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ደቡብ ክልል ስልክ ቢደውልም ሊሳካለት አልቻለም። የአማራ ክልል ...

Read More »

በአጣዬና ማጀቴ አካባቢ በተከሰተው የጸጥታ ችግር 27 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2011)በሰሜን ሸዋ አጣዬና ማጀቴ አካባቢ በተከሰተው የጸጥታ ችግር 27 ሰዎች መገደላቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ። ከተገደሉት መካከል ሦስቱ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ዋና አስተዳዳሪው አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ ለመንግታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል። አቶ ተፈራ ችግሩ የአማራ የኦሮሞ ህዝብ አጀንዳ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል። ከተገደሉት በተጨማሪ ከ20 በላይ ...

Read More »