በሶማሌ ክልል 46 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ ሊደረጉ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2011) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ 46 ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ከእነዚህም 6ቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። የተቀሩት 40ዎቹ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ተሸሽገው እንደሚገኙም አስታውቋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ላይ የተሳተፉና በቀጥታ ትዕዛዝ የሰጡት የሶማሌ ክልል የቀድሞ አመራሮች ላይ የተጀመረው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጸው አቃቤ ህግ ...

Read More »

በድሬዳዋ ሕዝባዊ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2011)በድሬዳዋ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉ ተሰማ። የተጠራቀመውን ብሶትና በደል ለመግለጽ አደባባይ የወጣው የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የከተማው መዋቅር ነዋሪውን ባይተዋር ያደረገ፣ መብትና ጥቅሙን የገፈፈ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀዋል። ህዝቡ ንብረት ከማውደምና ከማቃጠል ተቆጥቦ ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲገልጽም ጥሪ ተደርጓል። የተቃውሞ ትዕይንቱ ላይ የከተማው ከንቲባ ከስልጣን እንዲወርዱ ...

Read More »

የማዕከላዊ አፍሪካ ስፖርት ሚኒስትር ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተሰጡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011)የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊካ ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት ፓትሪክ ኤድዋርድ ናጊሶና ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ተሰጡ። የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ባለስልጣን እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮን ፌዴሪሽን አባል የነበሩትን ተጠርጣሪ ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሳልፋ የሰጠችው ፈረንሳይ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል። ግለሰቡ ባለፈው ወር ፓሪስ ላይ መያዛቸው ይታወሳል ። ፓትሪስ ኤድዋርድ ናጊሶና የተባሉት የማዕከላዊ አፍሪካ የስፖርት ባለስልጣን ከወር በፊት ...

Read More »

የሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ውዝግብ እየተቆጣጠርኩ ነው አለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011)የሶማሌ ክልል መንግስት ሰሞኑን የተፈጠረውን ውዝግብ በመቆጠጣር ላይ መሆኑን አስታወቀ። የክልሉን ፕሬዝዳንት ከስልጣን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴንም ማስቆሙን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአቶ ሙስጠፋ ኡመር የሚመራውን የክልሉን መንግስት በማወክና ከስልጣን በማውረድ የቀድሞውን አገዛዝ ለመመለስ የታቀደውን ሴራ በማቀናጀት አራት የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊና የደህንነት አዛዦች እንደሚገኙበት የሶማሌ ክልል ፕሬዛዳንት አማካሪ ለኢሳት ገልጸዋል። ሙከራው ቢከሽፍም ተጨማሪ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። አቶ አህመድ ሽዴ ...

Read More »

በአፋርና ኢሳዎች መካከል ዕርቅ ለማውረድ የሰላም ውይይት ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011) በአፋርና ኢሳዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆምና ዕርቅ ለማውረድ በአዲስ አበባ የሰላም ውይይት መካሄዱ ተገለጸ። በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት የተካሄደው ውይይት ላይ የሁለቱም ወገኖች የሃገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ሽማግሌዎቹ በሰላም ችግሩን ለመፍታት መስማማታቸውም ተገልጿል። የሰላም ውይይቱ ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት እንዳይሆን ስጋታቸውን የሚገልጹ ወገኖች መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸው ...

Read More »

በድሬዳዋ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011)በድሬዳዋ ከተማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። በተቃውሞው የተገደለ ሰው ባይኖርም በርካታ ሰዎች በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሰኞ ታቦት ወደ ቤተክርስቲያን በሚያመራበት ጊዜ በተወሰኑ አካላት ድንጋይ መወርወሩን ተከትሎ በቁጣ ለተቃውሞ የወጣው ህዝብ የተጠራቀመ ብስሶቱን በማሰማት ላይ እንደሆነም ተገልጿል። ነዋሪውን ያገለለው የድሬዳዋ ከተማ መዋቅር እንዲፈርስ በህዝቡ ተጠይቋል። ተቃውሞ ወደ አመጽ የተቀየረው የከተማው ከንቲባ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከ500 የሚበልጡ የሶሪያ ስደተኞች አሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2011)በኢትዮጵያ ከ500 የሚበልጡ የሶሪያ ስደተኞች እንደሚገኙ ተገለጸ። እ ኤ አ ከ2011 ጀምሮ በጦርነት ከምትታመሰው ሃገር ሶሪያ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች በልመና እና በመለስተኛ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል። የኢትዮጵያ የስደተኞችና የዜግነት ጉዳይ መምሪያ ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለአልጀዚራ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ደሃ ሃገር ብትሆንም ከ20 ከሚበልጡ ሃገራት ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል። ከሐምሌ መጨረሻ እስከ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2011)በኢትዮጵያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መደረጉንና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሲዊዘርላንድ ዳቮስ በሚካሄደው የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ ዛሬ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የዲሞክራሲ ምህዳሩ መስፋቱን በዚህም የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ሰላማዊ ትግል መጀመራቸውን ገልጸዋል። የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል የግል ዘርፉን ማስፋት የሚቻልበት ምቹ ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2011)አቶ በረከት ስምኦን በቁጥጥር ስር ዋሉ። የአማራ ክልል የጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዳስታወቀው አቶ በረከት ስምኦን የታሰሩት በሌብነት ተጠርጥረው ነው። የብአዴን አመራር አባል  የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳም በተመሳሳይ ሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸውንና ወደ ባህርዳር መወሰዳቸው ታውቋል። አቶ በረከት ስምኦንን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን የከበቡ የአማራ ክልል ፖሊሶች ወደ ባህርዳር  እንደወሰዷቸውም ታውቋል። ባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ...

Read More »

ኦነግ የአመራር እና የአባላቱ እስራት እንዲቆም ጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2011) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር  (ኦነግ) በአመራር እና በአባላቱ የተጀመረው እስራት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ፡፡ ኦነግ  በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው መግለጫ የኦነግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑትን አቶ ጀቢሳ ገቢሳ ጨምሮ የኦነግ አመራሮች እና አባላት አርብ ዕለት መታሰራቸውን ይፋ አድርጎል፡፡ ቀደም ብሎ ኮለኔል ገመቹ አያና እንደታሰሩበትም  አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና በመንግስት መካከል የተፈጠረውን  ውዝግብ ...

Read More »