ታዋቂው የማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ የቀብር ስነስርአት ተፈፀመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)በኦሮምኛ ሙዚቃ ታዋቂው የማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ  የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈፀመ። የአርቲስቱ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሲፈጸም ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አድናቂዎቻቸው ተገኝተዋል። አንጋፋው የኦሮምኛ ማሲንቆ ተጫዋች ለገሠ አብዲ በ1927 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ያያ ቃጫማ በተባለ ስፍራ ነው የተወለዱት። በኦሮምኛ የሙዚቃ አድማጮች የማሲንቆው ንጉስ ተብለው የሚጠሩት ለገሰ አብዲ በሀገር ፍቅር፥ በብሄራዊ ቴአትር፣ በአዲስ አበባ ከተማ ...

Read More »

በህገወጥ መንገድ የገባና 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እቃ ተያዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011) የደህንነት ካሜራዎችን ጨምሮ ለዲፕሎማቲክ አገልግሎት በሚል ሰበብ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እቃ መያዙ ተነገረ። የገቢዎች ሚኒስቴር  እንዳስታወቀው በሁለት ስማቸው ባልተጠቀሰ ኤምባሲዎች እና በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ስም በህገወጥ መንገድ ለዲፕሎማቲክ አገልግሎት በሚል የገቡ እቃዎች ተይዘዋል። እቃዎቹ ታሽገው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ሲገቡ መያዛቸውን እና እስካሁንም የአንደኛው ኤምባሲ  እቃ ብቻ ...

Read More »

ኦብነግ ከመንግስት ጋር ተስማማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ሃገር ቤት ገብቶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግስት ጋር መስማማቱ ተገለጸ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባርና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት ላይ የደረሱት በኤርትራ አስመራ መሆኑም ተመልክቷል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና በኦብነጉ ሊቀመንበር አድሚራል ሙሐመድ ኡመር ኡስማን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኦብነግ መሪዎች በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በ1983 የሽግግሩ መንግስት መስራች የነበረውና ...

Read More »

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ አዲስ አበባ ገባ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከሁለት አመታት ስደት በኋላ ትላንት አዲስ አበባ ገባ። ከጸጥታ ጋር በተያያዘ እንደሆነ በታመነ መልኩ ሕዝባዊ አቀባበል አልተደረገለትም። ወደ ሃገር የመመለሻ ጊዜው ጭምር ሲለዋወጥበት የቆየው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የመንግስት ባለስልጣናት፣ቤተሰቦቹ እንዲሁም አትሌቶች ተቀብለውታል። በብራዚል ሪዮ ኦሎምፒክ በነሐሴ ወር 2008 በማራቶን ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ...

Read More »

የአቶ ጌታቸው አሰፋ ሃብት እንዲታገድና የዝውውር መብታቸው እንዲገደብ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011) የቀድሞ የደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሃብታቸው እንዲታገድና የዝውውር መብታቸው እንዲገደብ አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ ማን ጠየቁ። የኮሎራዶው ኮንግረስ ማን ማይክ ኮፍ ማን የኤች አር 128 የውሳኔ ሀሳብን ጠቅሰው በአቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ለሁለት የአሜሪካ ሚኒስትሮች የጻፉትን ደብዳቤ ዛሬ አስገብተዋል። ኮንግረስ ማን ኮፍ ማን አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡና በውጭ ያላቸው ሃብት እንዲታገድ ...

Read More »

በባህርዳር የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)በባህርዳር የነዳጅ እጥረት ተከሰተ። ከባህርዳር በተጨማሪ በዙሪያዋ ባሉ ከተሞችም በነዳጅ ማደያዎች ቤንዚን በመጥፋቱ ህዝቡ ችግር ላይ መውደቁን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ላለፉት ሶስት ቀናት ማደያዎች ነዳጅ ማቅረብ ባለመቻላቸው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች በጥቁር ገበያ ከመደበኛው ዋጋ በእጥፍ እየተሸጠ መሆኑንም ገልጸዋል። የነዳጅ እጥረቱን በተመለከተ በክልሉ መንግስት በኩል የተሰጠ ማብራሪያ ባለመኖሩ የችግሩን መንስዔ ለማወቅ እንዳልተቻለ ተመልክቷል። በባህርዳር ከተማ ጨምሮ ...

Read More »

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011)       በውጭና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጀመሩ። በየአመቱ በጥቅምትና በግንቦት ወር የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከ25 አመታት በላይ ለሁለት ተከፍሎ ሲካሄድ ቆይቷል። ዛሬ ሰኞ የካቲት 12/2011 አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሃገራዊ ሁኔታ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ...

Read More »

በራያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 12/2011) በራያ አላማጣ በትላንትናው ዕለት የተገደሉ አምስት ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ። በቆቦ፣ ዋጃና ጥሙጋ በተቃውሞ የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት በመከላከያ ሰራዊት በኩል የተወሰደውን ርምጃን ተከትሎ ግጭት መፈጠሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በትላንቱ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ተጨማሪ የክልሉ ልዩ ሃይል ወደ አለማጣ ገብቷል። በቆቦም ተቃውሞ ተካሂዷል። የትግራይ ክልል መንግስት የተገደሉት ሰዎች ሶስት መሆናቸውን አስታውቋል። ለሟቾች ...

Read More »

በአላማጣ ከተማ የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ።

በአላማጣ ከተማ የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ በሄደ ቁጥር የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት የሚወስዱት እርምጃም በመጠናከሩ ትናንት 5 ሰዎችን ገድለው በርካታ ሰዎችን አቁስለዋል። የራያን የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አግዘው ህዳሩ እርሳቸው ባላቸው መረጃ 9 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ...

Read More »

የላሊበላን ጥንታዊ ገዳማት ከተደቀነባቸው አደጋ ለመታደግ መንግስት ፈጣን እና ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

የላሊበላን ጥንታዊ ገዳማት ከተደቀነባቸው አደጋ ለመታደግ መንግስት ፈጣን እና ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ/ም )የላሊበላ ገዳማት አስተዳዳሪና የከተማዉ ከንቲባ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ላሊበላ በተጋረጠበት አደጋ ዙሪያ ተወያይታዋል፡፡ ከዉይይቱ በኋላ የልዑካን ቡድኑ አባላት ለመገናኛ ብዙኀን እንዳሉት ላሊበላን የመታደግ እንቅስቃሴ በያዝነው ጥቅምት ወር ይጀመራል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ...

Read More »