የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጅ ተሻሽሎ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጅ ተሻሽሎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ተገለጸ፡፡ ማሻሻያው የሥራ አመራር ቦርዱ አባላትን ከ9 ወደ 5 ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ቦርዱ ለ3 የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሕጋዊ እውቅና መስጠቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች በትርፍ ጊዜያቸው ሳይሆን በቋሚነት ሙሉ ጊዜ እንደሚሰሩ እና በ5 ዓመታት ብቻ ተገድቦ የነበረው የሥራ ዘመናቸውም እንዲራዘም መደረጉን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ...

Read More »

አቶ አንዳርጉ ኢያሱ በርሔ ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት አገለሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱዳን ዴስክ ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ አንዳርጉ ኢያሱ በርሔ ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት ማግለላቸውን አስታወቁ። የራያ አካባቢ ተወላጅና የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ አንዳርጉ ኢያሱ ሕወሃት በራያ ሕዝብ ላይ የማይፈጽመው ኢሰብአዊ ድርጊት ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት ለማግለል ምክንያት እንደሆናቸው ገልጸዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ከለውጡ ጋር ከመተባበር ይልቅ ለውጡን ለመቀልበስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ከዚህ ድርጅት ጋር ...

Read More »

ኦብነግ ትጥቅ ፈታ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ዛሬ በይፋ ትጥቅ መፍታቱ ተገለጸ። ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሀገር የገባው ኦብነግ በሰላማዊ ትግሉ ለመቀጠል መዘጋጀቱን ሊቀመንበሩ አድሚራል መሃመድ ኡመር አስታውቀዋል። ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በተከናወነው ስነስርዓት የኦብነግ ሰራዊት ትጥቁን በመፍታት በክልሉ መንግስት ስር እንደሚሆን ተገልጿል። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሃመድ ኡመር የኦብነግ ትጥቅ መፍታት ለሶማሌ ክልል ሰላምና እድገት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል። ...

Read More »

ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሹመት ተሰጣቸው። ከንቲባው አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሐዋሳ ከተማና አከባቢዋ በአንዳንድ የሲዳማና የወላይታ ብሔረሰብ አባላት መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲጠፋና ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ እጃቸው አለበት በሚል ከሌሎች የከተማው አመራሮች ጋር ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል። አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ክስ እንደቀረበባቸው ቢታወቅም ለክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በምክትል  ...

Read More »

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ተወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የአማራ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት አወገዘ፡፡ በአካባቢው በተከሰተው ግጭቱ ሳቢያ መጠኑ ባልታወቀ ሁኔታ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። ሁለት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በተባለበት በዚሁ ግጭት ፋብሪካም ተቃጥሏል። 55 ከብቶችም ሞተዋል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር በይፋ አልተገለጸም። በርካታ ቤቶች ተቃጥለው ከ50 በላይ ...

Read More »

በሱዳን ወደ ወህኒ የተጋዙ ሰዎች እንዲፈቱ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2011)በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ኡመር አልበሽር ላይ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ወህኒ የተጋዙ ሰዎች እንዲፈቱና አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ የካርቱም ነዋሪዎች ጠየቁ። ዛሬ ሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም አደባባይ የወጡት በሲዎች የሚቆጠሩት የካርቱም ነዋሪዎች ጄኔራል አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ነጻነት፣ሰላምና ፍትህ የሚሉ መፈክሮችን ማስተጋባታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። “ወታደሮችህን በሙሉ አሰማራ መውደቅህ ግን አይቀርም”በማለት ለጄኔራል አልበሽር መልዕክት ያስተላልለፉት ...

Read More »

የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን የጥናትና ምርምር ማዕከል ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2011)በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ስም የጥናትና ምርምር ማዕከል ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ። አምቦ ዩኒቨርስቲ ሎሬት ጸጋዬን በአርአያነት የሚያሳይና ለትውልድ ተምሳሌት በሚሆን መልኩ ማዕከሉን ለማቋቋም በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ማዕከሉ የሚቋቋመው በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን የትወልድ ስፍራ መሆኑም ተገልጿል። በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የስነ ፅሁፍ ስራዎች ላይ ምርምር ማድረግ እና እንደ ሎሬት ፀጋዬ ያሉ ምሁራንን ለማፍራት የሚያስችል ማዕከል ይሆናል ተብሏል። በስነጽሁፍ ስራቸው ሁሌም ...

Read More »

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2011)የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የ12 አባላቱን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አስታወቀ። እነዚህ አባላት በክልሉ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሌብነት ወንጀሎች እጃቸው እንዳለበት ተገልጿል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳያቸውን አጣርቶ ለክስ ይፈልጋቸዋል የተባሉት 12ቱ የምክር ቤት አባላት በአብዲ ዒሌ አስተዳዳር ዘመን ከፍተኛ አመራር እንደነበሩ የሶማሌ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል። የቀድሞ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትም ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳባቸው አመራሮች መካከል ይገኙበታል። ...

Read More »

በአማራ ክልል ጭልጋ ወረዳ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2011)በአማራ ክልል ጭልጋ ወረዳ ባለፉት ሁለት ቀናት ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። ከአይከል እስከጓንግ ባለው መስመር ሁለት ቀበሌዎች መውደማቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ለኢሳት እንደገለጹት ሰሞኑን ባገረሸ ጥቃት በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ሰዎች ተገድለዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተሰደዋል። አፈናና ዝርፊያም በስፋት እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት እየሰራ ቢሆንም በውክልና የሚደረግ ...

Read More »

ሎረን ባግቦ ከወህኒ ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2011)በአለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰው በወህኒ የቆዩት የአይቮሪኮስቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሎረን ባግቦ ከወህኒ መውጣታቸው ተሰማ። ሎረን ባግቦ ከእስር ቤት ከወጡ በኋላም ወደ ቤልጂየም መጓዛቸው ታውቋል። በቁም እስረኝነት በቤልጂየም እንዲቆዩ ከኔዘርላንድ ሔግ ወህኒ ቤት ዛሬ የተለቀቁት ሎረን ባግቦ ፓስፖርታቸውንም እንዲያስረክቡ ቅድመ ሁኔታ ተጥሎባቸዋል። የአይቮሪኮስት መሪ በነበሩበት ወቅት ፈጸሙት በተባለው ወንጀል ጉዳያቸው በአለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ...

Read More »