በምዕራብ ጎንደር 138 ግለሰቦች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011)በምዕራብ ጎንደር ዞን ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ 138 ግለሰቦች በሕይወት ማጥፋትና በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው መታሰራቸው ተነገረ። በግጭቱ ሳቢያ 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር አስታውቋል ። በምዕራብ ጎንደር  ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶችና መሳሪያዎች  መያዛቸውም ተነግሯል። በምዕራብ ጎንደር ዞን ካለው ግጭት ጋር ...

Read More »

ኢሳት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2011)በኢትዮጵያ ለተካሄደው ለውጥ ኢሳት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና እንደሚገባው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ገለጹ። የኢሳት የጋዜጠኞች ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ካሳሁንን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውለታል። የኢሳትን ጋዜጠኞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ካሳሁን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የኢሳትን ጋዜጠኞች ሲቀበሉ የሚዲያ ተቋሙ የኢትዮጵያ ...

Read More »

በኢትዮ-አሜሪካ ለተቋቋሙ የንግድ ሰጪ ተቋማት ድጋፍ ይደረጋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011)የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያውያንና በኢትዮ-አሜሪካ ለተቋቋሙ የንግድ ሰጪ ተቋማት ድጋፉን እንደሚያደርግ አስታወቀ። የንግድ ምክር ቤቱ አባል ለሆኑ ተቋማት በማንኛውም መንግስታዊና ሕጋዊ በሆኑ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የንግድ ማህበረሰቡን ወክሎ የአባላቱን ጥቅም እንደሚያስከብርም ምክር ቤቱ ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ በይፋ መመስረቱ በተገለጸበት መድረክ ላይ ምክር ቤቱ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ድጋፉን እንደሚያደርግ ተገልጿል። የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት ምስረታ ላይ የተገኙት ...

Read More »

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011) የኢትዮ-ቴሌኮም የቀድሞው የኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው በአዲስ የሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ። አቶ ኢሳያስ ዳኘው በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ በዋስ እንዲፈቱ በጠቅላይ ፍርድቤት ተወስኖላቸው እንደነበር ታውቋል። የሜቴክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩትና በእስር ላይ የሚገኙት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ፖሊስና አቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ...

Read More »

የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ካምፕ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት/2011)በትጥቅ ትግል ላይ በጫካ የነበሩ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ ገቡ። ሕዝቡና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ቅንጅታዊ ሥራ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የኦነግ ሰራዊት አባላት ሀገራዊ ለውጡን ለመደገፍ ቁርጠኛ በመሆን ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መግባታቸው ታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ሰራዊት አባላት ጦላይን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል በተዘጋጁ የተለያዩ ካምፖች በመግባት ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸው ተነግሯል። እነዚህ ወደ ካምፕ የገቡት አባላት ...

Read More »

የኢሳት ባልደረቦች ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሊቪዥንና ሬዲዮ ኢሳት ባልደረቦች ከአምስተርዳም፣ለንደንና ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ አሸኛኘት ተደረገላቸው። ከዋሽንግተን ዲሲ የተነሱት የኢሳት ባልደረቦች ከዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ሲነሱ በኢትዮጵያውያን አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። አሸኛኘቱን በስፍራው ተገኝቶ ሲዘግብ የነበረውም ምናላቸው ስማቸው ስለ አሸኛኘቱ መረጃውን ሊያደርሰን እዚህ ስቱዲዮ ይገኛል።  

Read More »

በአማራ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 90ሺ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2011)በአማራ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎ ቁጥር 90ሺ ያህል መድረሱን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ። ተፈናቃዮቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ከመምጣታቸውና ያረፉበትም ቦታ የተለያየ መሆኑ ደግሞ የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ብለዋል የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አሰማህኝ አስረስ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ። ለተፈናቃዮቹ የክልሉና የፌደራል መንግስት በጋራ ድጋፍ ቢያደርጉም በቂ ሊሆን አልቻለም ብለዋል። ስለዚህ ተጨማሪ እርዳታ ...

Read More »

በሱዳን ጭንብል ያጠለቁ የጸጥታ ሃይሎች ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ሲያሰቃዩ የሚያሳይ ምስል ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2011) በሱዳን ጭንብል ያጠለቁ የጸጥታ ሃይሎች አልበሽር ከስልጣን ይውረዱ በሚል ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን ሲያባርሩ፣ሲደበድቡና ወደ ሚስጥራዊ የማሰሪያ ስፍራ እየጎተቱ ሲወስዱ ያሚያሳይ ምስል ይፋ ሆነ። ቢቢሲ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽሙት የጸጥታ ሃይሎች ድርጊቱን የሚፈጽሙት ታርጋ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች ነው። እንደ መረጃው ከሆነ ሰልፈኞቹን ለመያዝና ወደ ሚስጥራዊ የማሰሪያ ስፍራዎች ለመውሰድ ሚስጥራዊ የደህንነት ሰዎች ተመድበዋል። በሱዳን ወራትን ባስቆጠረው ተቃውሞ በሰልፈኞቹ ...

Read More »

የኢሳት ጋዜጠኞች ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2011)የኢትዮጵያ ሳተለይት ቴሌቪዥንና ሬድዮ ኢሳት ጋዜጠኞች ነገ ሐሙስ የካቲት 7/ 2011 ከተለያዩ የዓለም ክፍል በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ተገለጸ።   የጋዜጠኞቹን የአዲስ አበባ ጉዞ አስመልክቶም በአዲስ አበባ የሚገኘው የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ በእቴጌ ጣይቱ ሆቴል መግለጫ ሰቷል። የአስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ሺበሺ መግለጫውን አስመልክቶ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጨለማው ዘመን ብርሃን የነበረ፣ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ውለታ የዋለ ነው ...

Read More »

አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት ተመደቡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2011)የሕወሓቱ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት መመደባቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ። አቶ አስመላሽ ከኢሕአዴግና ከሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው በተጨማሪ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር በመሆን ሲሰሩ ቆይተዋል። በቅርቡ ተካሂዶ ከነበረው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በኋላ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት እንዲያገለግሉ ተመድበዋል። አቶ አስመላሽ ላለፉት በርካታ ዓመታት በፓርላማ በመንግሥት ...

Read More »