በሃና ማሪያም አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/ 2010) በአዲስ አበባ በተለምዶ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ገለጹ። ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ድንገት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃችውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል የስራ ማቆም አድማ ከመቱ አራተኛ ቀናቸውን ያስቆጠሩት የቦሌ ለሚ የኢንንዱስትሪ ዞን ሰራተኞች በፌደራል ፖሊስ ሲዋከቡ መዋላቸው ተገልጿል ። አዲስ አበባ ሃና ማርያም በዳግም ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/ 2010) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉ ተገለጸ። በመተከል ሁለት የአማራ ተወላጆች በጫካ ተገድለው መገኘታቸውን የኢሳት ወኪል ከስፍራው ካደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ክልል መንግስት ከጥቃት ሸሽተው በቅርቡ ወደ ባህርዳር የተሰደዱ የአማራ ተወላጆችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ጥረት እያደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት ግድያው መቀጠሉ ተነግሯል። ባለፈው ህዳር ወር የጀመረው ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። ከቀዬ መንደራቸው በማንነታቸው ...

Read More »

በሶማሌ ክልል 11 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010) በሶማሌ ክልል በቀጠለው ተቃውሞ በፊቅ ዞን በሁለት ከተሞች 11 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ኢሳት የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል። ቡሳ እና ለጋሂዳ በተባሉ ከተሞች ግድያውን የፈጸሙት የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል። ልዩ ሃይሉ ከየከተሞቹ እንዲወጣ ከፌደራል መንግስት ትዕዛዝ መሰጠቱን የሚጠቅሱት የኢሳት ምንጮች በህወሃት ጄነራሎች የሚደገፈው የክልሉ ፕሬዝዳንት ትዕዛዙን ተግባራዊ ለማድረግ እንዳልፈለገ ገልጸዋል። አንደኛ ወሩን እየደፈነ ያለው ...

Read More »

የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 58 ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010) ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ናዛወሯን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 58 ደረሰ። በተቃውሞው ጉዳት የደረሰባቸው ፍልስጤማውያን ቁጥርም 2ሺ 700 ደርሷል። በተቃውሞው ሳቢያ ተጨማሪ  ዕልቂት እናዳይፈጠር ስጋት ደቅኗል። ፍልስጤማውያን ምስራቃዊው የኢየሩሳሌም ክፍል የነገዋ የፍልስጤም ሃገራቸው ርዕሰ ከተማ እንደሚሆን በመናገር  ላይ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት በኢየሩሳሌም  መከፈቱ ለግጭቱ መከሰት ምክንያት ሆኗል። አሜሪካ በሁለቱ ...

Read More »

የኢንደስትሪያል ዞን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010)በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ዞን በሚገኙ ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መምታታቸው ተገለጸ። አድማ በመምታታቸው ከመንግስት በኩል ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው ነው። በሌላ በኩል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ደሞዝ ሳይከፈላቸው ከአንድ ወር በላይ እንደሆናቸው ተገልጿል ። አዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ዞን ባለፉት ሶስት ቀናት ባልተለመደ መልኩ ውጥረት ታይቶበታል። በርከት ያሉ በውጭ ባለሀብቶች የሚንቀሳቀሱ ፋብሪካዎች ከወትሮው ተግባራቸው ...

Read More »

በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ክፍያ ከስራው ክብደት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በመግለጽ የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል። ሰራተኞቹ በስራቸው መጠን የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ ሊያገኙ አልቻሉም። በገዢው ፓርቲ በኩልም የሰራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኝነት ባለመኖሩ ሰራተኞች ...

Read More »

በጠምባሮ ዞን 10 መምህራን ቆስለው ሆስፒታል ሲገቡ በርካቶች ደግሞ ታሰሩ

በጠምባሮ ዞን 10 መምህራን ቆስለው ሆስፒታል ሲገቡ በርካቶች ደግሞ ታሰሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሚገኙ መምህራን ለልማት በሚል ያለፍላጎታቸው ከወር ደሞዛቸው ላይ መቆረጡን በመቃወማቸው 10 መምህራን በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ሲገቡ፣ 20 መምህራን ደግሞ የለምንም ጥያቄ ተስረዋል። በዚህም የተነሳ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል። መምህራኑ ከዚህ በፊት ለአባይ ግድብ በሚል የወር ...

Read More »

ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 7/2010)የልብ ቀዶ ሕክምና ባለሙያው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር ተለቀቁ። የ66 አመት እድሜ ያላቸው ስዊዲናዊውው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከ5 አመታት እስር በኋላ ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ወጥተዋል። በቅሊንጦ ቃጠሎ በግድያ ወንጀል ተከሰው ከነበሩት 38 ሰዎች ክሳቸው እንዲነሳ ሲወሰን አራቱ በነጻ ተለቀው ቀሪዎቹ ደግሞ የፍርድ ሂደታቸው እንዲቀጥል መባሉ ይታወሳል። በእነመቶ አለቃ ማስረሻ ስጤ መዝገብ አግባው ሰጠኝን ጨምሮ 62 ሰዎች ...

Read More »

በባለስልጣናት የውጭ አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር አብይ ተናገሩ

በባለስልጣናት የውጭ አካውንቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር አብይ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በውጭ አገራት ባንኮች የባንክ ሂሳብ ደብተር ያላቸው ባለስልጣናት ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። የካቢኔ ስብሰባቸውን ከአርብ ወደ ቅዳሜ እንደተለወጠና ጊዜን በስራ ሰዓት በስብሰባ ማባከን እንደሚያስቀር ተናግረዋል። ባለስልጣናት አሰራራቸውን ...

Read More »

ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ

ዶ/ር ፍቀሩ ማሩና ጨምሮ የተወሰኑ እሰረኞች ተፈቱ (ኢሳት ዜና ግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ክሳቸው የተነሳላቸው የህክምና ባለሙያውን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ፣ አቶ አግባው ሰጠኝ፣ አቶ ሲሳይ ባቱ፣ ፋሲል አለማየሁ እና አቶ ከመደ ጨመዳ ከእስር ቤት ወጥተዋል። በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ ከ38 ተከሳሾች መካከል በነፍስ ይከላከሉ ከተባሉት አራት ...

Read More »