የኢሳት 7ኛ አመት በኮሎምቦስ ኦሃዩ ተከበረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 19/2010)የኢሳት 7ኛ አመት በኮሎምቦስ ኦሃዩ በድምቀት ተከበረ። በበአሉ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልና የኢሳት ድርሻ በሚል ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ቅዳሜ ህዳር 25/2017 በኦሃዩ በተከበረው የኢሳት 7ኛ አመት ላይ ከኦሃዩና አካባቢዋ፣ከሴንሴናቲ፣ከዴይተን፣ክሊቭላንድና ኢንዲያና ግዛት የመጡ የኢሳት ደጋፊዎች ተሳትፈዋል። በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ኮመዲያን ክበበው ገዳና የኢሳት ባልደረባው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሲሆኑ ኮመዲያን ክበበው ገዳ ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር። ...

Read More »

ሰላም ባስ ገራዥ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር19/2010)በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ገራዥ ላት ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። አቃቢ ህግ ግለሰቦቹ ድርጊቱን የፈጸሙት በአርበኞች ግንቦት ሰባት ትዕዛዝ ነው ሲልም አመልክቷል። አርብ ሕዳር 15/2010 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች አንተነህ ፋንታሁን፣ኤርሚያስ አለባቸው፣አንድነት ፋንታሁን፣ፍስሃ እያዩና ብርሃኑ ሞገስ የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ተመልክቷል። እኒዚህ በክሱ ላይ የተዘረዘሩት ...

Read More »

የሮበርት ሙጋቤ የልደት ቀን ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር ታወጀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010) በዚምባቡዌ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የልደት ቀን ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር ታወጀ። ባለፈው ሳምንት ስልጣኑን የተረከቡት ኤመርሰን ናንጋግዋ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከዚምባቡዌ መስራች መሪዎች አንዱ በመሆናቸው ክብር ይገባቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን እንዲወርዱ በተደረገ ድርድር 10 ሚሊየን ዶላር የጡረታ ጉርሻ እንደተፈቀደላቸው ዘገባዎች ያሳያሉ። ባለፈው ሳምንት በጦር ሃይሉና በአስታራቂዎች ግፊትና ድርድር የስልጣን መልቀቂያቸውን አስገብተው ወደ ...

Read More »

የዮናታን ተስፋዬ ክስ ከሽብርተኝነት ክስ ወደ መደበኛ ወንጀል ተቀየረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ ተከሶበት የነበረው የሽብር ተግባር ክስ ተሰረዘለት። ክሱ ወደ መደበኛ ወንጀል የተቀየረው የፍርድ ሂደት የዮናታን የእስር ቤት ቆይታንም ከ6 አመት ወደ 3 አመት ዝቅ እንዲል አድርጎታል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ዳኛ ዘርአይ ወልደሰንበት ከችሎት እንዲነሱላቸው ለፍርድ ቤት ያቀረቡትን አቤቱታ በፅሁፍ ማስገባታቸው ታውቋል። በታህሳስ 2008 ነበር በኦሮሚያ ...

Read More »

በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ በኢትዮጵያና በቱርክ መሃል ጦርነት እጭራለሁ አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ተስፋኪሮስ ሃይሉ ገብረማርያም በኢትዮጵያና በቱርክ መሃል ጦርነት እጭራለሁ ሲሉ ማስፈራራታቸው ተገለጸ። አታሼው ይህን ያሉት በስካር መኪና ሲያሽከረክሩ አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ በፖሊስ በመጠየቃቸው ነው። በቱርክ አንካራ ቅዳሜ ለሌት አደጋውን ያደርሱት አቶ ተስፋኪሮስ ሁለት ተሽከርካሪዎችን የገጩ ሲሆን አንድ ሰው ማቁሰላቸውም ታውቋል። በሎሳንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች ቆይተዋል። ...

Read More »

በታላቁ ሩጫ ኮከብ የሌለበት ባንዲራ በፖሊስ ሲቀማ ዋለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)በታላቁ ሩጫ ውድድር ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ የያዙ ኢትዮጵያውያን በፖሊስ ሲነጠቁ መዋላቸውን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የቴዲ አፍሮን ምስልና “ኢትዮጵያ” የተሰኘውን የዜማውን አርማ የያዘ ካኒቴራ የለበሱ ወጣቶችም ከታላቁ ሩጫ ውድድር እንዲወጡ ተደርገዋል። የሼህ መሀመድ አላሙዲ አድናቂዎች “አይዞህ አባቴ”የሚልና የእሳቸውን ፎቶ ለጥፈው ሲሮጡ ግን ከውድድሩ እንዲታገዱ አልተደረጉም። በታላቁ ሩጫ ላይ 44ሺህ ተሳታፊዎች ለውድድሩ ድምቀት ሰጥተውት ነበር። በዚህ ውድድር ላይም ...

Read More »

በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ንጹሃን ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይም ርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ እንደገና ግጭት ማገርሸቱን መንግስት በሳምንቱ መጨረሻ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዲስ ባገረሸው ግጭት ባለፈው ሳምንት ብቻ 20 ሰዎች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከህወሃት ስራ አስፈጻሚ አባልነት ታገዱ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)ከሁለት ወራት በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤትን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን አገደ። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፓርቲውን ሊቀመንበርና ሌላ አንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ማድረጉን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊቀመንበርነትን ላለፉት አምስት አመታት የያዙት አቶ ...

Read More »

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ጋብ ብሎ የነበረው በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ። በሞያሌ አቅራቢያ ቦርቦር በተባለው አካባቢ በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ከሁለቱ ወገኖች 27 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የህወሃት ልዩ ኮማንዶ በአካባቢው ከገባ በኋላ ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች በግድያው ላይ የኮማንዶ ሃይሉ በቀጥታ መሳተፉንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል በአርሲ ነገሌ የመንግስት ካድሬዎች አቀናብረውታል በተባለ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

በግብጽ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 235 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)በግብጽ ሳይናይ ግዛት በአንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 235 ሰዎች ሲገደሉ 130 ሰዎች ቆስለዋል። የሟቾቹም ሆነ በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀንም አውጀዋል። እስካሁንም ለጥቃቱ በይፋ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ። በግብጽ ሳይናይ ግዛት ዛሬ በአንድ መስጊድ ላይ በደረሰው የሽብር ጥቃት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ...

Read More »