በአፋር ገዋኔ የህዝብ ቁጣን ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2011) በአፋር ገዋኔ በመከላከያ የተገደለው ወጣት ጉዳይ የህዝብ ቁጣን መቀስቀሱ ተሰማ። ሰልፈኞቹ የመከላከያ ሃይሉ ከገዋኔ ይውጣልን፣ገዳዮች ለህግ ይቅረቡልን፣ኮንትሮባንዲስቶች በህግ ይጠየቁልን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ማሰማታቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። የአፋር ወጣቶች ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ አመራር በሶስት ወራት ውስጥ እንዲሰራ የተቀመጠለትን የቤት ስራ አልሰራም በሚል በተለያዩ ወረዳዎች ህዝባዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር ...

Read More »

ኤርትራ የቱርክ መንግስትን አሳሰበች

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2011) በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል የተደረሰውን የሰላም ስምምነትና አወንታዊ እርምጃዎችን ለማደናቀፍ ቱርክ ከምታደርገው እንቅስቃሴ እንድትቆጠብ ኤርትራ አሳሰበች። የኤርትራ ሙስሊም ሊግ የሚል ድርጅት በመፍጠርም ሉዋላዊነቴን የሚጋፋ ድርጊት ቱርክ ፈጽማብናለች  ስትልም ኤርትራ ክስ አቅርባለች። ኳታርና ሱዳን ደግሞ በተባባሪነት ከሚያካሂዱት ድርጊት እንዲታቀቡም  የኤርትራ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወታው መግለጫ አሳስቧል። በኤርትራ በኩል የቀረበውን ክስ በተመለከተ ስማቸው ከተጠቀሱት ሀገራት የተሰጠ ማስተባቢያም ሆነ ማረጋገጫ ...

Read More »

የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2011) በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከአብራሪዎች ውጭ በሆነ ችግር መሆኑን የምርመራው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት አመለከተ። የምርመራ ቡድኑ ባወጣው የመጀመሪያ የምርመራ ሪፖርት  የአውሮፕላኑ አብራሪዎች በአምራቹ ቦይንግም ሆነ በአሜሪካ የፌዴራል አቪዬሽን ባለሥልጣን የተቀመጡ መስፈርቶችን ያሟሉ እንደነበሩ አረጋግጧል። የመርማሪ ቡድኑ በአውሮፕላን አደጋው ቅድመ ሪፖርቱ አራት ነጥቦችን ያካተተ ሁለት የደህንነት ምክረ ሐሳቦችንም አቅርቧል፡፡ የምርመራ ቡድኑ ...

Read More »

የፋኦ ሪፖርት ከ113 ሚሊየን በላይ ህዝብ በከፋ ረሃብ መጠቃቱን አስታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ከ113 ሚሊየን በላይ ህዝብ በከፋ ረሃብ መጠቃቱን አንድ ሪፖርት አመለከተ። በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ አማካኝነት ይፋ በሆነው ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው 53 ሀገራት በከፋ የረሃብ አደጋ ተመተዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ስምንቱ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባቸው በመባል መጠቀሳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በስምንት የዓለም ሀገራት ከ72 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የረሃብ አደጋ የገጠማቸው በሚል ተመዝግበዋል። ከ2017 ...

Read More »

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ክስ በደህንነት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት እንዳይፈጸም ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011) የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት አቶ ድንቁ ደያስ በ11.3 ሚሊዮን ብር የቼክ ማታለል ወንጀል ተከሰው ታስረው እንዲቀርቡና ከሀገር እንዳይወጡ የፍርድ ቤት ቤት ትዛዝ ቢወጣባቸውም በደህንነት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት ተፈጻሚ አለመሆኑን ምንጮች ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል ከትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙት አቶ ድንቁ ደያስ ከገር እንዳይወጡ የፍርድ ቤት ትዛዝ ቢውጣባቸውም ውጭ ሐገር እንደሚመላለሱ ያገኘነው መረጃ  ያመለክታል። ...

Read More »

በአማራ ክልል የታሰሩት ዳኛ ጉዳይ ዳኞችን ሥጋት ውስጥ መክተቱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/ 2011) በአማራ ክልል በፖሊስ ላይ የቅጣት ውሳኔ በመስጠታቸው የታሰሩት ዳኛ ጉዳይ ዳኞችን ሥጋት ውስጥ መክተቱ ተነገረ። በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አንድ የፖሊስ አባል በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ በሰጡት ውሳኔ ምክንያት መታሰራቸው፣ ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ዳኞችን ሥጋት ውስጥ መጣሉ ተገልጿል። የታሰሩት ዳኛ አቶ ምሥጋናው ባቡር ይባላሉ። አቶ ምስጋናው የሞጣ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ...

Read More »

በአፋር ገዋኔ አንድ ወጣት ተገደለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011) በአፋር ገዋኔ አንድ ወጣት በመከላከያ ሃይል መገደሉ ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በመከላከያ ሃይሉ የተገደለው ወጣት ፍየሎችን በመጠበቅ ላይ የነበረ ነው። የመከላከያ ሃይሉ ጥቃት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የነበሩት ወጣቶች ላይ ሊሰነዝር ያሰበውን ጥቃት ነው በዚህ ወጣት ላይ የፈጸመው ይላሉ። ለሚመለከተው አካል አቤት ብንልም የሚሰማን አካል አላገኘንም ብለዋል። በገዋኔ የመከላከያ ሃይሉ ፈጸመ የተባለውን ጥቃት አላውቅም ያሉት የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ...

Read More »

አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ የዋስትና መብት ይከበርልን ሲሉ ጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011)አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ፍርድ ቤት የፈቀደልን የዋስትና መብት ይከበርልን ሲሉ ጠየቁ። በባህርዳር ከተማ ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት የቀድሞ የኢህ አዴግና የብ አዴን ከፍተኛ አመራሮች ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲያሰናብታቸውም ጠይቀዋል። በሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ባለፈው ሳምንት በፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው። ዛሬ ባህርዳር ላይ ለተሰየመው ችሎች ጥያቄአቸውን ያቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ የአማራ ...

Read More »

በቢሾፍቱ የተከሰተው የውሃ ችግር ነዋሪዎችን ለከፋ ችግር መዳረጉ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011)በቢሾፍቱ የተከሰተው የውሃ ችግር ለከፋ ችግር ዳርጎናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢሳት ገለጹ። በተለያዩ ቀበሌዎች ተከሰተ የተባለው የውሃ ችግር አንድ ወር እንዳለፈውም ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ የውሃ መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ውሃ ያለበትን አካባቢ ፈልጎ ማግኘትና ለውሃ መጫኛና መቅጃ የሚያወጡት ወጪ እንዳማረራቸውም ይናገራሉ። ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል አቤት ማለታቸውንና ከሚመለከተው አካል በትዕግስት ጠብቁ ከሚባለው ምላሽ ውጪ ምንም መፍትሄ አለመገኘቱንም ይናገራሉ። ኢሳትም ...

Read More »

በአፋር በተለያዩ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011) በአፋር የተሾመው አዲሱ አስተዳደር ምንም ለውጥ አላመጣልንም በሚል በተለያዩ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ ተሰማ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት የወጣቱ ጥያቄ ለውጥ ይምጣ በአዲስ አመራር ኣነመራ የሚል ነበር። ለዚህም ወጣቱ ለአዲሱ አስተዳደር የ100 ቀናት ጊዜን ሰጥቶ በመጠባበቅ ላይ ነበር ይላሉ ነዋሪዎቹ ። ይሄ ደግሞ ወጣቱን ለቁጣ አነሳስቶታል ብለዋል። በተለያዩ ወረዳዎች ላይ በአንድ ጊዜ ተደርጓል የተባለው ሰልፍ ምክር ቤት እስከ ...

Read More »