ዩ ኤስ አይ ዲ የሚያቀርበውን ድጋፍ ማቋረጡን አስታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011) የአሜሪካው የሰብዓዊ እርዳታ ተቋም ዩ ኤስ አይ ዲ በጌዲዮና ጉጂ አካባቢዎች ባገረሸው ውጥረት ምክንያት ለተፈናቃዮች የሚያቀርበውን ድጋፍ ማቋረጡን አስታወቀ። ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶድርጅቱ የሚሰጠውን ድጋፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን ያስታወቀው የድርጅቱ ዳይሬክተር በአካባቢዎቹ ቆየተው ከተመለሱ በኋላ ነው። ፋይል  የዩኤስ አይዲ ዳይሬክተር ሌስሊ ሪድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጌዲዮና ጉጂ አካባቢዎች ዳግም የተፈጠረው አለመረጋጋት የድርጅቱን እንቅስቃሴ ...

Read More »

በቤንሻንጉል የአማራ ተወላጆች በመስጊድ ውስጥ ተጠልለዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011) ቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሼ ዞን ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች በምስራቅ ወለጋ መስጊድ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገለጸ። ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይየሚገኙት እነዚህ ተፈናቃዮች መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉቴ ከተማ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ የተሰባሰቡት ተፈናቃዮች ቁጥር በየዕለቱ በመጨመሩ ከፍተኛ ችግር እንደደረሰባቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ባለፈው ሳምንት ከካማሼ ዞን ያሶ ወረዳ የተፈናቀሉ 600 ...

Read More »

የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት ገብቶናል አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 3/2011)የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የከተማዋ ጸጥታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ስጋት ገብቶናል ሲሉ ገለጹ። ኤጄቶ በሚል የሚንቀሳቀሱ የሲዳማወጣቶች ስም የተደራጁ ሃይሎች የአካባቢውን ነዋሪ እያዋከቡ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ያነጋገረውና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የኤጄቶ አባል አንዳንድ የሲዳማን ወጣቶች መልካም ስም ለማጉደፍ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ተናግሯል። ሰሞኑን በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 5 የሲዳማ ወጣቶችን ሃዘን ከመግለጽ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአመራር ለውጥ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ– ታህሳስ 2/2011)በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአመራር ለውጥ መደረጉ ተገለጸ። ንግድ ባንኩ በጀመረው የአሰራር ለውጥ አራት አዳዲስ ምክትልፕሬዝዳንቶች ተሹመዋል።           ከተሾሙት አራት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሁለቱ ከግል የንግድ ባንኮች የመጡ ናቸው ተብሏል። ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ከመንግስት የፋይናንስ ተቋማት የመጡ መሆናቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነባር የአመራር አባላት ከተነሱ በኋላ የሃላፊነት ክፍተት ተፈጥሮ ቆይቷል። በተለይም የአራት ዘርፎች ሃላፊዎች ከቦታቸው ከተነሱ በኋላ ...

Read More »

የአዴት ከተማ ነዋሪዎች ባህር ዳር ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 2/2011) በምዕራብ ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ ነዋሪዎች ያልተለወጠው አመራር በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቅ በመጠየቅ ለአቤቱታ ባህር ዳር ገቡ። በወረዳው ባልተለወጡ የአስተዳደር አካላት እየተፈፀመ ያለውን ሙስናና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም እንዲሁም  አመራሮቹ ለህግ እንዲቀርቡ  የአዴት ነዋሪዎች ጠይቀዋል። ከአዴት ከተማ 42 ኪ.ሜ ርቀት ተጉዘው በ3 አውቶብሶች ባህርዳር የገቡት የአካባቢው ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በተደራጀ ሁኔታ ...

Read More »

ከተሿሚ ዲፕሎማቶች ውስጥ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ተገኙ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 2/2011)በቅርቡ ከ50 ለሚበልጡ ዲፕሎማቶችተሰጠ ከተባለው ሹመት ጋር ተያይዞ ዝርዝሩ ይፋ ሳይሆን የቀረው ከተሿሚዎቹ ውስጥ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች በመገኘታቸው እንደሆነ የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ገለጹ። ለአዲሱ ሹመት ታጭተው ከነበሩት ውስጥ አንዱ በሳምንቱ መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።           የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 58 ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች መመደቡን በገለጹበት ወቅት ከዝርዝሩ ውስጥ የተጠቀሱት አቶ መአሾ ኪዳኔ በሳምንቱ መጨረሻ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በብሔራዊ መረጃና ...

Read More »

ለተፈናቃዮች የእርዳታ እህል ማቅረብ አልተቻለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 2/2011) በቤንሻንጉል ጉምዝና አዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቃዮች የእርዳታ እህል ማቅረብ አለመቻሉን የብሔራዊ የአደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ፋይል በሌላ በኩል በአካባቢዎቹ ለወራት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆምና ታጣቂዎችን መሳሪያ ለማስፈታት የፌደራል መንግስት ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ማስገባቱ ታውቋል። የብሔራዊ የአደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ለተረጂዎች እርዳታ ለማጓጓዝ የሄዱ ተሽከርካሪዎች ...

Read More »

በደቡብ ክልል ቡርጂ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 2/2011)በደቡብ ክልል ቡርጂ አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ።           በግጭቱም በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳትመድረሱ ነው የታወቀው። ፋይል           ከኦሮሚያ ክልል ጋር ይዋሰናል በተባለው በምዕራብ ጉጂ አካባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ አለመብረዱን ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።           ግጭቱ በዋናነት የቡርጂ ብሔረሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል ነዋሪዎች ።           በደቡብ ክልል ቡርጂ አካባባቢ ግጭቱ በዋናነት መቀስቀስ የጀመረው በ2010 መስከረም ላይ ...

Read More »

ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን የተሳሳተ ዘገባ አረመ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011)የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ። የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ የዘር ግጭት የሚጭር ቪድዮ አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 28/2011) የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፖለቲካ አላማቸው ሲሉ ሕዝብን ወደ ራሳቸው ፍላጎት ለማምጣት ሌሎችን በጠላትነት የሚፈርጁ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም ሲል ታዋቂው የትንተና መጽሔት ፎሪን ፖሊሲ ዘገበ። አንዳንድ በስም የጠቀሳቸው ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ሕዝበኛ ሲሉ ቢያነሷቸውም ዶክተር አብይ አሕመድ እንደ አሜሪካው ትራምፕም ሆነ እንደ ቱርኩ ኤርዶጋን ብራሳቸው ዙሪያ ሰዎችን ለማሰልፍ ተቀናቃኛቸውን በጠላትነት የሚፈርጁ ...

Read More »