የግብፁ ፕሬዝዳንት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 4/2011)የግብፁ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ፡፡ ላለፉት ሁለት አመታት የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩት ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ ሊቀመንበርነታቸውን አስረክበዋል፡፡ አል ሲሲ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በመሆን እስከ ፈረንጆቹ 2020 ይቆያሉ ተብሏል፡፡ ፓል ካጋሜ ባደረጉት ንግግር ለአፍሪካ ሀገራት መንግስታት፣ ተቋማት እና ሌሎች አካላት በቆይታቸው ሲያደርጉላቸው ለነበረው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ አል ሲሲ በበኩላቸው በአፍሪካ የድርድር እና የመከላከል ...

Read More »

ሌተናል ኮለኔል ትርሲት ገብረመስቀል አረፉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 4/2011)የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባና የሶማሊያ ጋር በተደረገው ጦርነት ተሳታፊ የነበሩት ሌተናል ኮለኔል ትርሲት ገብረመስቀል ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በሌላም በኩል በአሜሪካ ሂዩስተን ከተማ ከኢሳት አስተባባሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ አብይ ግርማ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ለእረፍት ወደ አሜሪካ ብቅ ባሉበት በድንገት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ሌተናል ኮለኔል ትርሲት ገብረመስቀል በምርጫ 1997 ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲን በመወከል የአዲስ አበባ ...

Read More »

በደቡብ ጎንደር አንድ መስጊድ በእሳት ተቃጠለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 4/2011)በደቡብ ጎንደር ትላንት ምሽት በአንድ መስጊድ ላይ የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተሰማ። የእሳት አደጋው የደረሰው በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ጃራ ገዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የዘር ግጭትን ወደ ሃይማኖት ግጭት ለመቀየር የሚጥሩ ወገኖች ይሄን ችግር እንደፈጠሩትም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል። በቅርቡ በዚሁ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ከተማ ሁለት መስጊዶች መቃጠላቸውና በሶስተኛው መስጊድ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱና ...

Read More »

ሴራሊዮን አስገድዶ መድፈር ላይ የድንገተኛ ጊዜ መመሪያ አወጣች

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)ሴራሊዮን በሐገሯ በሴቶች ላይ የሚፈጽመው አስገድዶ መድፈር አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ የድንገተኛ ጊዜ መመሪያ ማውጣቷን አስታወቀች። ሴት በመድፈር የተጠረጠረና የተፈረደበት ሰው በእድሜ ልክ እስራት እንደሚቀጣም የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል። በሴራሊዮን በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እየጨመረና አሳሳቢ ሆኖ መገኘቱን በመግለጽ የድንገተኛ ጊዜ መመሪያ መውጣቱን ትላንት በርዕሰ መዲናዋ ፍሪታውን ያስታወቁት የሐገሪቱ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳባዩ መንግስት አደጋውን ለመቀነስ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጅ ተሻሽሎ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጅ ተሻሽሎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ተገለጸ፡፡ ማሻሻያው የሥራ አመራር ቦርዱ አባላትን ከ9 ወደ 5 ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ቦርዱ ለ3 የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሕጋዊ እውቅና መስጠቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች በትርፍ ጊዜያቸው ሳይሆን በቋሚነት ሙሉ ጊዜ እንደሚሰሩ እና በ5 ዓመታት ብቻ ተገድቦ የነበረው የሥራ ዘመናቸውም እንዲራዘም መደረጉን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ...

Read More »

አቶ አንዳርጉ ኢያሱ በርሔ ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት አገለሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱዳን ዴስክ ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ አንዳርጉ ኢያሱ በርሔ ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት ማግለላቸውን አስታወቁ። የራያ አካባቢ ተወላጅና የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ አንዳርጉ ኢያሱ ሕወሃት በራያ ሕዝብ ላይ የማይፈጽመው ኢሰብአዊ ድርጊት ራሳቸውን ከሕወሃት አባልነት ለማግለል ምክንያት እንደሆናቸው ገልጸዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ከለውጡ ጋር ከመተባበር ይልቅ ለውጡን ለመቀልበስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ከዚህ ድርጅት ጋር ...

Read More »

ኦብነግ ትጥቅ ፈታ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ዛሬ በይፋ ትጥቅ መፍታቱ ተገለጸ። ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሀገር የገባው ኦብነግ በሰላማዊ ትግሉ ለመቀጠል መዘጋጀቱን ሊቀመንበሩ አድሚራል መሃመድ ኡመር አስታውቀዋል። ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በተከናወነው ስነስርዓት የኦብነግ ሰራዊት ትጥቁን በመፍታት በክልሉ መንግስት ስር እንደሚሆን ተገልጿል። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሃመድ ኡመር የኦብነግ ትጥቅ መፍታት ለሶማሌ ክልል ሰላምና እድገት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል። ...

Read More »

ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሹመት ተሰጣቸው። ከንቲባው አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሐዋሳ ከተማና አከባቢዋ በአንዳንድ የሲዳማና የወላይታ ብሔረሰብ አባላት መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲጠፋና ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ እጃቸው አለበት በሚል ከሌሎች የከተማው አመራሮች ጋር ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል። አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ክስ እንደቀረበባቸው ቢታወቅም ለክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በምክትል  ...

Read More »

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ተወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 1/2011)የአማራ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት አወገዘ፡፡ በአካባቢው በተከሰተው ግጭቱ ሳቢያ መጠኑ ባልታወቀ ሁኔታ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። ሁለት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በተባለበት በዚሁ ግጭት ፋብሪካም ተቃጥሏል። 55 ከብቶችም ሞተዋል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር በይፋ አልተገለጸም። በርካታ ቤቶች ተቃጥለው ከ50 በላይ ...

Read More »

በሱዳን ወደ ወህኒ የተጋዙ ሰዎች እንዲፈቱ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2011)በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ኡመር አልበሽር ላይ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ወህኒ የተጋዙ ሰዎች እንዲፈቱና አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ የካርቱም ነዋሪዎች ጠየቁ። ዛሬ ሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም አደባባይ የወጡት በሲዎች የሚቆጠሩት የካርቱም ነዋሪዎች ጄኔራል አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ነጻነት፣ሰላምና ፍትህ የሚሉ መፈክሮችን ማስተጋባታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። “ወታደሮችህን በሙሉ አሰማራ መውደቅህ ግን አይቀርም”በማለት ለጄኔራል አልበሽር መልዕክት ያስተላልለፉት ...

Read More »