ቻይና ለቦይንግ ኩባንያ የካሳ ጥያቄ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2011) ቻይና ለቦይንግ ኩባንያ የካሳ ጥያቄ ማቅረቧ ተሰማ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የቦይንግ ምርት የሆኑ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን በሙሉ ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ያደረገችው ቻይና በዚህም ምክንያት የደረሰብኝን ኪሳራ ቦይንግ ኩባንያ ይክፈለኝ ስትል መጠየቋ ተሰምቷል።

ከቻይና ሌላ የቱርክና የዱባይ አየር መንገዶችም የካሳ ክፍያ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና ባለቤታቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ፈረንሳዊት ቦይንግ ኩባንያ 276 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍላቸው በመጠየቅ ክስ መመስረታቸው ታውቋል።