“ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩን ባያስተካክልም፤ ሕዝቡ መብቱን ለማስከበር መነሳቱ አይቀርም፡፡ ያኔ ተጠያቂ እኛና ሕዝቡ ሳንሆን፤ ራሱ ኢህአዴግ ነው የሚሆነው” ሲሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስጠነቀቁ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶክተር ነጋሶ ይህን ያሉት ሰሞኑን አንድነት ፓርቲን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ይመሩ ዘንድ በአብላጫ ድምጽ መመረጣቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው። “የሰጣችሁኝ ኃላፊነት ከባድ እንደሆነ ሁላችንም የምንገነዘበው ነው” ያሉት የቀድሞው የ አገሪቱ ፕሬዚዳንት፤ “በተለይም የፖለቲካ ምሕዳሩ ባልተስተካከለበት ሁኔታ አንድን ፓርቲ መምራት በጣም ከባድ ነው”ብለዋል። “ሆኖም ግን ፈቃደኝነቱ እንዲሁም የሚያስፈልገውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ በመሆን በቆራጥነት ...

Read More »

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ኃላፊዎች፤ የፌዴራል ፍርድ ቤት አያዘንም ማለታቸውን ሪፖርተር ዘገበ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመሠረተው የፍትሐ ብሔር ክስ- ማስረጃ እንዲልኩ ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሳቸው የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአውሳ ዞን መስተዳድርና የሚሌ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፦ ‹‹ክሱ መታየት ያለበት በክልላችን በመሆኑ ኃላፊዎችንም ሆነ የምርመራ መዝገቡን ለመላክ ፈቃደኛ አይደለንም›› ማለታቸውን ፌዴራል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስታወቋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ...

Read More »

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በገሊላ ወረዳ ሰሜን አሪ በሚባል ቦታ የመንግስት ፖሊሶች አንድ ሰው በመግደል ዝርፊያ መፈፀማቸው ተዘገበ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፖሊሶቹ ዝርፊያ ስለመፈፀማቸው ምስክርነት የሰጡ 18 የ አካባቢው ነዋሪዎችም እንዲታሰሩ ተደረገ። እንደ ፍኖተ-ነፃነት ዘገባ፤ ፖሊሶቹ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ.ም በግብርና ሙያ በሚተዳደርና አቶ ለጊዜ ወርቅማ በተባለ የገሊላ ወረዳ ነዋሪ ላይ ዝርፊያ ሲፈጽም ከፍተኛ የ አካል ጉዳት አድርሰውበታል። ከማሳው ቡና ለቅሞ ወደ ቤቱ እየሄደ ሳለ በወረዳው በሚገኙ የመንግሥት ፖሊሶች ዝርፊያና ከፍ ያለ ጉዳት የደረሰበት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቡና ገዥ የሆኑ አስር የውጭ አገር ኩባንያዎችና ማህበራት በብትን መልክ የሚቀርበውን የኢትዮጵያን ቡና እንደማይገዙ አሳወቁ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ቡና በብትን መልክ ብቻ ለማዕከላዊ ገበያ ይቅረብ” የሚለው መመሪያ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቡና ገዥ የሆኑ አስር የውጭ አገር ኩባንያዎችና ማህበራት በብትን መልክ የሚቀርበውን የኢትዮጵያን ቡና እንደማይገዙ አሳወቁ። ገዥ በማጣት አጣብቂኝ ውስጥ የወደቁትና መመሪያው እንዲቀየር ለንግድ ሚኒስቴር ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ የተደረገባቸው ቡና ላኪዎች፤ ለአቶ መለስ ዜናዊ አቤቱታ ለማሰማት እየተዘጋጁ ነው። የኢትዮጵያ ቡና ...

Read More »

የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲውን አመራሮች መረጠ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላለፉት ሁለት ቀናት  ጠቅላላ ጉባኤውን ካደረገ በሁዋላ፣ የፓርቲውን ሊቀመንበር፣ የብሄራዊ ምክር ቤት እና የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላትን መርጧል። የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን በሊቀመንበርነት የመረጠው ጉባኤ፣ ለብሄራዊ ምክር ቤት ከመረጣቸው 40 ሰዎች መካከል በእስር ላይ የሚገኘውን አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ፣ ዶ/ር ንጋት አስፋው፣ አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ተመስገን ...

Read More »

ሱዳንና ኢትዮጵያ የሁለቱ አገራት ተቃዋሚዎችን በየአገሮቻቸው ላለማስተናገድና አሳልፎ ለመስጠትም ተስማሙ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው አገራቱ በየአገሮቻቸው ያሉ አማጽያንን ለማስወጣትና አሳልፎ ለመስጠት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የሁለቱ አገራት የድንበር ጉዳይ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተገኙት የሲናር ክፍለሀገር ገዢ የሆኑት አህመድ አባስ ፣ ሁለቱ አገሮች በድንበር አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን አሳልፈው ለመስጠት መስማማታቸውን አረጋግጠዋል። የመለስ መንግስት የሱዳንን መንግስት ላለማበሳጨት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑን የዘገበው ሱዳን ትሪቢዩን፣ በቅርቡ ...

Read More »

በዳንግላ ወረዳ አንድ በግንቦት7 አባልነት የተጠረጠረ መምህር ታፍኖ ተወሰደ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በዳንግላ ወረዳ ነዋሪ የሆነው መምህር ምህረት በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ የተወሰደው ከሳምንት በፊት ነው። የኢሳት የአማራ ክልል ዘጋቢ እንደገለጠው ማንነታቸው ያልታወቁ ራሳቸውን የደህንነት ሰራተኞች አድርገው ያስተዋወቁ ሲቪል የለበሱ ሰዎች መምህሩን ከክፍል አስወጥተው ወደ አልታወቀ ስፍራ ወስደውታል። መምህሩ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የማእከላዊ እስር ቤት ሳይወሰድ እንዳልቀረ ግምቶች መኖራቸውንም ገልጧል። በክልሉ መንግስትን ...

Read More »

መንግስት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሬ አደረገ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲሱ ጭማሪ መሰረት በከተማ ሚኒባስ ታክሲ 1ብር ከ 35 ሳንቲም የነበረው 1ብር ከ40 ሳንቲም፣ 2 ብር ከ70 ሳንቲም የነበረው 2 ብር ከ80 ሳንቲም ሆኗል፡፡ 3 ብር ከ75 የነበረው 3 ብር ከ90 ሳንቲም፣ 3 ብር ከ90 የነበረው 4 ብር፣  5 ብር የነበረው 5 ብር ከ15 ሳንቲም ሆኗል፡፡ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ታሪፍ እንዲሁ 1 ብር ከ45 ...

Read More »

24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ኪሊማንጃሮ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠዉ ገቡ ያላቸዉን 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ማድረጉን የኬንያ ኪሊማንጃሮ ክልል ፖሊስ አስታወቀ። የክልሉን የፖሊስ አዛዥ በመጥቀስ ዴይሊ ኒዉስ ባወጣዉ በዚሁ ዘገባ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች የተያዙት በታንዛኒያና በኬንያ ድንበር አካባቢ ታቬታ በተባለዉ ስፍራ ሲሆን የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገልጿል። ፖሊስ በተጨማሪ ሕገወጥ ስደተኞቹን መንገድ እየመሩ ከድንበር ድንበር ...

Read More »

ከቃል ኪዳኑ ታቦት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ ሴራ እየተጠነሰሰ ነው

ታህሳስ 02 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እግዚአብሄር ለሙሴ ጽፎ የሰጠው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ቦታ ለሺ አመታት አለምን አነጋግሯል፣ የበርካታ የታሪክ ተመራማሪዎችን ቀልብ ስቦ ቆይቷል፤፡ ታዋቂው ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ግርሀም ሀንኮክ ከአመታት በፊት ” ዘ ሳይን ኤንድ ዘ ሲል” በሚለው መጽሀፋቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ የሚጠቁም መጽሀፍ አሳትመዋል። በመጽሀፋቸውም የካቶሊክ እና የአይሁድ እምነት ተከታዮች አውሮፓውያን ታቦቱን ፍለጋ ...

Read More »