መንግስት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሬ አደረገ

03 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-በአዲሱ ጭማሪ መሰረት በከተማ ሚኒባስ ታክሲ 1ብር ከ 35 ሳንቲም የነበረው 1ብር ከ40 ሳንቲም፣ 2 ብር ከ70 ሳንቲም የነበረው 2 ብር ከ80 ሳንቲም ሆኗል፡፡

3 ብር ከ75 የነበረው 3 ብር ከ90 ሳንቲም፣ 3 ብር ከ90 የነበረው 4 ብር፣  5 ብር የነበረው 5 ብር ከ15 ሳንቲም ሆኗል፡፡

የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ታሪፍ እንዲሁ 1 ብር ከ45 የነበረው 1 ብር ከ50 ሳንቲም፣ 1 ብር ከ85 የነበረው 1ብር ከ90 ፣ 2ብር ከ45 የነበረው 2 ብር ከ50፣  2 ብር ከ75 የነበረው 2 ብር ከ80 ሆኗል፡፡

ጭማሪው በህዝቡ ኑሮ ላይ ተጨማሪ ጫና እንደሚፈጥር ታክሲ ተሳፋሪዎች ለዘጋቢያችን ገልጠዋል።