ኢትዮጵያ ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት ዘልቆ መግባቱን አመነች

ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የ ኢትዮጵያ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት፤በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት ገብቷል። የደቡባዊ ሶማሊያን አብዛኛውን ክፍል ከተቆጣጠሩት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ጋር እየተዋጉ የሚገኙትን የኬንያንና የሶማሊያን የሽግግር መንግስት ሰራዊት ለማገዝ  ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር እንደምትልክም፤ እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳልገባ ስታስተባብል መቆየቷ  ይታወሳል። እኚሁ የኢትዮጵያ ...

Read More »

የመንግስት ጭቆና ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ደርሶአል ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጠ

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ  የኢህአዴግ አገዛዝ ብሶት የወለደው ህዝብ እየፈጠረ መሆኑን  ጠቅሶ፣ ብሶት የወለደው ህዝብም  አምባገነኖችን ማስወገዱ አይቀሬ ነው ብሎአል። ፓርቲው   የኢትዮጵያ አምባገነኖች ከቱኒዚያው ቤን አሊ፣ ከሊቢያው ጋዳፊ፣ ከግብጹ ሙባረክ ሊመማር አለመቻላቸውን ከጳጉሜ 3 2003 ዓም ጀምሮ  የሰለማዊና ህጋዊ ፖለቲካ አራማጆችንና ነጻ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ከሶ ወደ ወህኒ ማውረዱን በመጥቀስ ...

Read More »

በስደት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ገለጡ

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርሰውን ጥቃት መቋቋም አንችልም በማለት ከአገራቸው ተሰደው በመምጣት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ኢትዮጵያውያንን ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ  ኢትዮጵያውን ገለጡ። ለስራቸው እንቅፋት ይፈጥራል በሚል ምክንያት ስማቸውን መግለጥ ያልፈለጉት ኢትዮጵያውያኑ እንዳሉት ፣ ገዢው ፓርቲ በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ የሚገኙትን ሁሉ በፎቶ እና በሌሎች ማስረጃዎች በማስደገፍ አይ ኤን ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ወረራ በረሃብ የተጎዳዉ የሶማሊያ ህዝብ ያለበትን ስቃይ እንደሚያባብሰዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰብኣዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረዉ አለርት ኔት ከናይሮቢ እንደገለፀዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣዉ የሰብኣዊ ሁኔታ ዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግስት ወረራ ፣ በረሃብ የተጎዳዉ የሶማሊያ ህዝብ ከመኖሪያዉ እንዲፈናቀልና ህይወት አድን የሆነዉን እርዳታ ትቶ እንዲሸሽ በማድረግ ያለበትን ስቃይ እንደሚያባብሰዉ ገልጿል። በሶማሊያ 4 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሲሆን 250 ሺህ ሰዎች ድርቅና የርስ በርስ ግጭት ባስከተሉት ረሃብ የተጎዳ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የካርታ ስራ ኤጀንሲ ብሄራዊ የካዳ-ስትራል ካርታ ለማዘጋጀት ለስራ ተቋራጮች ጨረታ አወጣ

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የካርታ ስራዉ የመሬት ይዞታ ድንበሮችን፤ ባለቤትነትና ምዝገባን የሚያካትት ሲሆን ጨረታዉን የሚያሸንፈዉ ድርጅት 23 ከተሞችን፤ የኦሮሚያ፡ የአማራ፤ የትግራይና የደቡብ ክልሎችን ጨምሮ እንዲሁም የቻርተር ከተማ ሆነዉ የተመዘገቡትን የአዲስ አበባንና የድሬዳዋ ከተሞችን በሚሸነሽን መልክ የአየር ፎቶግራፍ ያነሳል። ከአንድ አመት ጥቂት ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ ተመሳሳይ ስራ 50 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ገንዘብ በሚሆን ወጪ በአንድ የጀርመን የአየር የቅያስ ...

Read More »

የመምህር የኔሰው ገብሬ ሞትን ተከትሎ አንድ ወጣት በአካባቢው ባለስልጣናት ፊት እራሱን በገመድ አንቆ ለመግደል ሞከረ

ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህዳር 12 ቀን 2011 ዓም የዳውሮ ዋና ከተማ በሆነው ተርጫ ከተማ የሚኖረው ወጣት እራሱን በገመድ አንቆ ለመግደል የሞከረው፣ የአካባቢው ባለስልጣናት በፈጠሩበት የአስተዳደር በደል ነው። ለአመቻች መምህርነት  ስራ ለመቀጠር አመልክቶ ምልመላውን አልፎ የነበረው ወጣት፣ ወደ ስልጠና ለመሄድ  ሲዘጋጅ የወረዳው ባለስልጣናት  ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ተጠባባቂነት ቦታ ማውረዳቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በድህነት ይኖር የነበረው ወጣት፣ “ለምን ...

Read More »

በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲካኞች እና ጋዜጠኞች በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ ህዳር 14 ቀን 2004 ዓም ከቀኑ በ9 ሰአት በዋለው ችሎት ላይ ሁሉም እስረኞች እጆቻቸው በካቴና ታስሮ በፍርድ ቤቱ ተገኝተዋል። የፍርድ ቤቱን ሄደት ለመከታተል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቢገኙም፣ ፖሊሶች ግን 20 ሰዎችን ብቻ እንደሚያስገቡ በመግለጣቸው አብዛኛው ህዝብ ሁኔታውን በውጭ ሆኖ ለመከታተል ተገዶአል። ፍርድ ቤቱ ከአንደኛውና ከአራተኛው ክሶች በስተቀር ሌሎች ክሶች መሰረተ ቢስ ናቸው፣ አንደኛውና ...

Read More »

የአፋሩ ሀንፍሬ አሊ ሚራ፤ በበዓለ-ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው መንፀባረቁን ተዘገበ

ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 26 ቀን በሞት በተለዩት አባታቸው በቢትወደድ ሱልጣን አሊሚራ ምትክ፤ ሰሞኑን  እጅግ በደመቀ በዓል የሱልጣንነት ማዕረግ የተጎናፀፉት ሀንፍሬ አሊ ሚራ፤ በበዓለ-ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው መንፀባረቁን ሪፖርተር ዘገበ። “የአፋር ህዝብ ልብ፤ከመንግስት?ወይስ ከሱልጣን?” በሚል ርዕስ ጋዜጣው እንደዘገበው፤ የሀንፍሬ አሊሚራህን የሱልጣን ሲመት ለማክበር በኤርትራና በጅቡቲ የሚገኙትን ጨምሮ በአራቱም ማዕዘን የሚገኙ አፋሮች ...

Read More »

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች የክስ ቻርጅ ዛሬ ጠዋት ቀርቦ ተነበበ

ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ  ዜጎች የክስ ቻርጅ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት ቀርቦ ተነበበ፡፡ ከጠዋቱ 3፡40 ሰዓት ላይ በካቴና ታስረው ወደ ችሎት የቀረቡት በሀገር ውስጥ የሚገኙት ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 8  ያሉት ተከሳሾች ብቻ ...

Read More »

በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ተጠሪ የሆኑት ጆኒ ካርሰን፣ ኢትዮጵያ ሶማሊያን ዳግም መውረሯ ትክክል አይደለም አሉ

ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለስልጣኑ ይህን ቃል የሰጡት ማክላቺ ለተባለው ጋዜጣ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከአራት አመት በፊት ሶማሊያን በመውረር ለሁለት አመታት ያክል በአገሪቱ ውስጥ ብትቆይም፣ በመጨረሻ አልሸባብን  መፍጠር በስተቀር ያመጣቸው ውጤት እንደሌለ ካርሰን ተናግረዋል። ካርሰን በሶማሊያ ሰላም ለማምጣት ማንኛውም እንቅስቃሴ በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ በኩል መካሄድ እንዳለበት በመግለጥ የኢትዮጵያን እንቅስቃሴ በእጅጉ ነቅፈዋል። የመለስ መንግስት በድጋሜ ሶማሊያን ለመውረር ለምን እንደፈለገ ግልጽ ...

Read More »