24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ኪሊማንጃሮ በቁጥጥር ስር ዋሉ

03 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠዉ ገቡ ያላቸዉን 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ማድረጉን የኬንያ ኪሊማንጃሮ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉን የፖሊስ አዛዥ በመጥቀስ ዴይሊ ኒዉስ ባወጣዉ በዚሁ ዘገባ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች የተያዙት በታንዛኒያና በኬንያ ድንበር አካባቢ ታቬታ በተባለዉ ስፍራ ሲሆን የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገልጿል።

ፖሊስ በተጨማሪ ሕገወጥ ስደተኞቹን መንገድ እየመሩ ከድንበር ድንበር የሚያሸጋግሩ በኬንያ፤ በኢትዮጵያ፤ በሶማሊያ፤ በታንዛኒያና በአዉሮፓ ይህንኑ ተግባር እንደስራ ለረዢም አመታት የሚያከናዉኑ ግለሰቦች መኖራቸዉን በመግለፅ ፣ ስደተኞቹ ከደቡብ አፍሪቃ ህገወጥ የመጓጓዣ ሰነዶችን በመግዛት የተሻለ እድል ለማግኘት ወደ አዉሮፓ እንደሚጓዙ ገልጿል።