በአውሮፓ የሚኖሩ ሙስሊሞች መንግስት አህባሽ የተባለውን የእስልምና አስተምህሮ ለማስፋፋት እቅድ ዘርግቶ መንቀሳቀሱን አወገዙ

ኢሳት ዜና:-1 ሺ 4 መቶ 33ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል  በብራሰልስ፣  ቤልጂም በተከበረበት ወቅት የሉቅማን ኢትዮጵያዊያን ቤልጄማውያን ሙስሊሞች ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት  አብዩ ያሲን  መንግስት በፖሊሲ ደረጃ ቀርጾ  አህባሽ የተባለውን የእስልምና አስተምህሮ ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን  የጽሁፍና የንግግር ማስረጃዎችን በማቅረብ ለተሳታፊው አስረድተዋል። ከዚህ ቀደም በአለማያ ከተሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ መንግስት በሰንዳፋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ውስጥ 200 የሚሆኑ የአህባሽ አሰልጣኞችን እያሰለጠ መሆኑን ...

Read More »

አርቲስትና የመብት ተሟጋች ደበበ እሸቱ አርብ እለት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብቻውን በዝግ ችሎት ቀረበ

ዳኛ ታሪኳ ተበጀ  በሚያስችሉት  አንደኛ  ወንጀል  ዝግ  ችሎት  ላይ  ማንኛውም  የተከሳሽ ቤተሰብ፣ ጋዜጠኛ፣ የመብት ተሟጋችና ታዛቢዎች እንዲገቡ አልተፈቀደም፡፡ ከተከሳሾቹ  ቀደም  ብለው  ፍርድ  ቤቱን የከበቡት  ፌዴራል  ፖሊሶች  በችሎቱ  አቅራቢያ ማንኛውም  ሰው  እንዳይጠጋ  የከለከሉ  ሲሆን ሦስት ጋዜጠኛች ብቻ የፖሊሶችን ከለላ በትግል አልፈው  የፍርድ ቤቱ  መዝገብ  አመላላሽ  ጋር በመድረስ “እኛ ጋዜጠኞች  ነን ፖሊሶች ከልክለውን ነው፣ እባክሽን ዳኟዋ ጋር ሂጂና እንድንገባ እንድትፈቅድልን ጠይቂልን”  በማለት መታወቂያቸውን ያሳይዋት ሲሆን ፣ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ ለሱዳን የተሰጠው ሰፊ መሬት ለወደፊቱ የግጭት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቀ

ኢሳት ዜና:-ኮሚቴው ኖቬምበር 3፣ 2011 ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ የመለስ መንግስት ከኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ከራሱ የፓርላማ አባላትም ሳይቀር በመደበቅ ለሱዳን የሰጠው ሰፊ የኢትዮጵያ መሬት ህጋዊ ተቀባይነት የለውም። የድንበር ኮሚቴው  የመለስ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ከመሬቱ አልተፈናቀለም እያለ ቢናገርም፣ ሚስጢራዊ ሰነዶችን በማውጣት ታወቀው ዊኪሊኪስ የመለስ መንግስት ሰፊ የሆነ ለም መሬት ለሱዳን መስጠቱን ከበቂ በላይ ማረጋገጡን ጠቅሶአል። የሱዳኑ መሪ የአፍሪካ ህብረት ...

Read More »

በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የታሰሩት 20 የሚጠጉ የአገር ሽማግሌዎች መፈታታቸው ታወቀ

ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት ከወረዳና ከሌሎች ማህበራዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ በከተማው የተነሳው ግጭት ያሳሰበው የፌደራሉ መንግስት፣ የታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች ተለቀው ችግራቸው እንዲታይላቸው የሚል ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል። በዚህም መሰረት የአገር ሽማግሌዎቹ አርብ ማምሻውን መለቀቃቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ ስርአቱን ሲያወግዙ የነበሩ ወጣቶች ግን በብዛት እየታሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢው ህዝብ ባስነሳው ተቃውሞ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ተዘግተው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ...

Read More »

የኦሮሞ ተዋጊዎችን ፍለጋ ድንበር ያቋረጠው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ወጣ

የኦሮሞ ተዋጊዎችን በማሳደድ ቄዳር እና ማራ-ዲሌ ወደ ተባሉ የሶማሊያ አካባቢዎች ድንበር አቋርጦ የገባዉ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን፤ ኦል አፍሪካን የዜና አገልግሎት ዘግቧል። ሰራዊቱ በአካባቢዉ የሚያደርገዉን አሰሳ አጠናቆ ከአንድ ቀን በሁዋላ ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን የገለፁት፤ የአካባቢዉ የአይን ምስክሮች እንደሆኑ የዜና አግልግሎቱ ገልጿል። የማእከላዊ ሶማሊያ ከተሞችን ይዞ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ድንበር አቋርጦ የገባዉ፤ ለዘብተኛ የሆነዉ የአህሉ ሱና ...

Read More »

በከፍተኛ ድጎማ ከውጪ የተገዛ ስንዴ ለህዝቡ መከፋፈል መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ

ኢሳት ዜና:- አቶ መለስ ዜናዊ ባለፉት 20  አመታት የእርሻ ምርት በ40 በመቶ ማደጉን በገለፁበት ማግስት በከፍተኛ ድጎማ ከውጪ የተገዛ ስንዴ ለህዝቡ መከፋፈል መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። በስንዴ እጥረት ምክንያት፡በርካታ ዳቦ ቤቶች ሥራቸውን ባቆሙበት ባሁኑ ጊዜ መንግስት ለአንድ ኩንታል እስከ ሁለት መቶ ብር ድጎማ በማድረግ  ከውጪ የገዛው ስንዴ በዐዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች እየተከፋፈለ ነው። ስንዴው እታደለ  ያለውበ ሸማቾች ማህበር አማካይነት ...

Read More »

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በእስር ላይ የሚገኙት የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን በአምነስቲ ኢንተርናሽናል አማካኝነት ደብዳቤ እንዲጽፉ ጠየቁ

ኢሳት ዜና:- የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን በአምነስቲ ድረ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “በፌስቡክና በቲዊተር ዘመን ደብዳቤ መጻፍ አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች የእኔን የእስር ዘመን እንዲያስታውሱ እመክራቸዋለሁ” ብለዋል። “እኔ  ነጻ እሆናለሁ የሚል ተስፋ አልነበረኝም። እኔ ምንም ወንጀል ሳልፈጽም ሀሳቤን በነጻነት በመግለጼ ብቻ ነበር የታሰርኩት ።  የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኞችን ለእስር በመዳረግ ተቃውሞን ለማፈን የሚችል ይመስለዋል” ያሉት ወ/ት ብርቱካን  አምነስቲ ኢንተርናሽናል በ2009 ...

Read More »

በትምህርት ቤት ውስጥ የመንግስትን ፖሊሲዎች በማንሳት ጥያቄዎችን በመጠየቁና ተማሪዎችን ለማነሳሳት ሙከራ አድርጓል በማለት ለአንድ አመት የታሰረው አስቻለው ቢራቱ ተፈታ

ኢሳት ዜና:- ተማሪ አስቻለው በቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚማርበት ጊዜ ገዢው ፓርቲ ተማሪዎችን ለአባልነት ለመመልመል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም፣ እንዲሁም በመሬትና በተዛማጅ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዙሪያ ጥያቄዎችን በማቅረቡ ተከሶ ለአንድ አመት በእስር እንዲቀጣ ተፈርዶበት ነበር። ተማሪ አስቻለው ለኢሳት እንደገለጠው የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ርእሰ መምህርና መምህራን አስቻለው የሚያቀርባቸውን ጥአቄዎችም ሆነ ከተማሪዎች ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት አይወዱለትም ነበር። በ2002 ዓም ደግሞ ተማሪ አስቻለው ...

Read More »

ኢትዮጵያን ለቀው የሚወጡ ዜጎች ቁጥር በታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ

ኢሳት ዜና:- የኢሳት የባህርዳር ዘጋቢ እንዳለው በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ የመንና ሱዳን የሚሰደደው ህዝብ በእጅጉ አስደንጋጭ ሆኗል። የአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ባለስልጣናት ያቀረቡትን ሪፖርት ተንተርሶ በላከው ዘገባ ተሰዳጆቹ የከተማ ነዋረዎች ብቻ ሳይሆኑ ገበሬዎች ጭምር ናቸው። በደቡብ ጎንደር በየሳምንቱ ከ250 እስከ 300፣ በሰሜን ወሎ ከ300 እስከ 450 ፣ በደቡብ ወሎ ከ200 እስከ 300፣ በጎጃም ከ400 እስከ 550 የሚደርሱ ገበሬዎችና የከተማ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች፤ ዐቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የመጀመሪያ ምስክር ቃል መሳቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ

ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ ዐቃቤ ህግ በጋዜጠኞቹ ላይ የመጀመሪያው የአቃቤ ህግ ምስክር ኢንስፔክተር መሀመድ አህመድ የተባለ የፖሊስ አባል ነው። ኢንስፔክተር መሀመድ፤ ጆሀን ፐርሰን እና ማርቲን ሽብዬ የተባሉት ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች የኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ተዋጊዎችን የሚያሰለጥኑ ናቸው  በማለት ነው የመሰከረው። የኢንስፔክተሩ ምስክርነት ከተሰማ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኞቹን ፦የኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ተዋጊዎችን ስለመርዳትና ስለማሰልጠን በተሰማው ምስክር ላይ ያላቸውን አስተያዬት ...

Read More »