ኢሳት ዜና:- የኢሳት ዘጋቢ ያነጋገራቸው ሙስሊሞች እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ መንግስት አንዱን ወገን አህባሽ ሌላውን ወገን ደግሞ ዋህቢ በማለት መከፋፈሉ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታን ፈጥሯል። ክፍፍሉን ተከትሎም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ለእስር ተዳርገዋል። በአዲስ ዘመን ከተማ ደግሞ የወረዳው የእስልምና ሀላፊ የነበሩት በታጣቂዎች መገደላቸው ታውቋል። መንግስት በፖሊሲ ደረጃ ቀርጾና በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መድቦ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አህባሽን ...
Read More »በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ ከመብት ጥያቄዎች ጋር ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ90 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተሰማ ችግሩ ግን አሁንም አልበረደም
ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት በዋካ ከተማ ከወረዳና ከልማት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የሀይል አማራጭ ተጠቅመዋል። በዚህም የተነሳ በየቀበሌው የሚገኙ ወጣቶች መንግስትን ለመገልበጥ አስባችሁዋል እየተባሉ ከእየቤታቸው እየተወሰዱ በመታሰር ላይ ናቸው። በርካታ ወጣቶችም እስሩን በመሸሽ አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው። መመህራን እና ተማሪዎች ባደረጉት ስብሰባ ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት የወሰዱትን እርምጃ አውግዘዋል። ተማሪዎቹና መምህራኑ የመብት ...
Read More »የቀድሞው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ ያረጋል አይሸሹም ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ
ኢሳት ዜና:-በአቶ ያረጋል አይሸሹምና በህወሀት ባለስልጣናት መካከል የተነሳውን የፖለቲካ ውዝግብ ተከትሎ በሙስና የተከሰሱት አቶ ያረጋል የእርሳቸውና የባለቤታቸው ንብረት እንዲታገድ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ፣ አቶ ያረጋል በባለቤታቸው ፣ በልጆቻቸውና በእርሳቸው ስም ተመዝግበው የሚገኙ በአሶሳ በ1200 ስኩየር መሬት ላይ የሰፈረ የግል መኖሪያ ቤት፣ በዚሁ ከተማ የሚገኝ 1000 ካሬ ሜትር ቦታ፣ በቦሌ አካባቢ የሚገኘው 500 ካሬ መሬት፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚገኝ 4132 ...
Read More »በየመን በስደት ላይ የምትገኝ ኢትዮጵያዊት ህጻን በሞት ሽረት ትግል ውስጥ እንደምትገኝ ተገለጠ
ኢሳት ዜና:-ህጻን ሀያት መስከረም 12/2000 ዓ.ም በእቅፍ ነው ስደት የወጣችው። ገና የአንድ አመት ልጅ እያለች ነው በባህር ወደ የመን ከመጡት እናቷ እና አባቷ ጋር አብራ የመጣችው። ድንገት ማንም ሰው በዚህ እድሜው ከሚያየው ስቃይ በላይ ስቃይን አጣጥማለች። እናቷ በሞት የተለየቻት ይህች ህጻን እንዳዛሬው 5 ዓመት ሞልቷት መሳቅ መጫወት ሳትጀምር፣ ርሀብ ጥሟን መናገር ሳትችል፣ ህመሜ እዚህ ጋር ነው በማትልበት ወቅት የ 11 ...
Read More »ኢሳት በሳተላይት የ24 ሰዓት ሬዲዮ ስርጭት ጀመረ (የኢሳት ጋዜጣዊ መግለጫ)
የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓም ኢሳት የ24 ሰዓት የሳተላይት ራዲዮ ስርጭት ማስተላለፍ መጀመሩን በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የሰተላይት ራዲዮ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፍ መጀመሩን ለህዝብ ሲያሳውቅ በታላቅ ደስታ ነው። ኢሳት የሳተላይት ራዲዮ ስርጭት የጀመረበት ዋና ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለዴሞክራሲና ለነጻነት ለሚያደርገው ትግል ህዝብ ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ ትግሉን ለማገዝ የገባውን ቃል አጠናክሮ ...
Read More »አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር፣ ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ እና ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የፍትህ ስርዓቱንና አቶ መለስ በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር ተቹ
ኢሳት ዜና:- ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር፤አንድ ዳኛ ህገ-መንግስቱ ውስጥ በተቀመጠው መሰረት የዳኝነት ነፃነቱን እንዴት ያለ ተፅዕኖ ሊገብር ይችላል?” የሚለውን ጉዳይ ለማየት፤ “ዻኛው ማነው?”፣ዳኛ ለመሆን የሚያስችሉት መስፈርቶችስ ምንድናቸው? የሚለውን የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማየት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። የዴሞክራሲ ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች የዳኝነት አካል ሲዋቀር ዜጐች በተለያየ መንገድ እንደሚሳተፉ፤ በዳኝነት የሚሾሙት ሰዎችም ዕድሜያቸው በሰል ያለና ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን የሚናገሩት እኚሁ ምሁር፣ ኢትዮጵያ ...
Read More »መንግስት በአዲስ አበባ የታየውን ከፍተኛ የስንድ እጥረት ለመቅረፍ ከውጭ አገር የገዛውን ስንዴ ለህብረተሰቡ ማከፋፈል ሊጀምር መሆኑ ታወቀ
ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በአዲስ አበባ የታየውን ከፍተኛ የስንዴ እጥረት ተከትሎ የዳቦ መጠን መቀነሱን እንዲሁም ህብረተሰቡ ዳቦ ለማግኘት ረጅም ሰአት ተስለፎ መጠበቅ ግድ ብሎት እንደነበር መዘገባችን ይታወቃል። ይህን ተከትሎ መንግስት ከዚህ ቀደም ዘይት ለማከፋፈል እንደሞከረው ሁሉ ስንዴም ለነዋሪው በዚህ ሳምንት ውስጥ ማከፋፈል እንደሚጀመር ታውቋል። አንድ ቤተሰብ በነፍስ ወከፍ የሚገዛው የስንዴ መጠን ባይታወቅም፣ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን ከ25 እስከ 50 ኪሎ ሊደርስ ይችላል። ግብርናው ...
Read More »ኢሳት በሳተላይት የሬዲዮ ስርጭት ጀመረ
ኢሳት ዜና:- ኢሳት በቅርቡ የከፈተው የአጭር ሞገድ ስርጭት በኢትዮጵያ መንግስት መታፈን መጀመሩን ተከትሎ የሳተላይት የሬዲዮ ስርጭት በመጀመር የመንግስትን አፈና ለመቋቋም ወሳኝ እርምጃ ወስዷል። የአጭር ሞገድ ስርጭቱ እየታፈነም ቢሆን እንደሚቀጥል የገለጠው ማኔጅመንቱ፣ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያውያን በሳተላይት ኢሳትን የሚስቡበት አማራጭ ቀርቦላቸዋል። አዲሱ የሳተላይት ስርጭት በ ኤቢ 2 ሳተላይት፣ በስምንት ዲግሪ ዌስት በ11 ሺ 5 መቶ 95 ሞገድ ቨርቲካል በ27 ሺ 5 መቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ
ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) ከህዳር እስከ ጥር ወር 2004 ዓ.ም ለሚያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣ http://www.ethsat.com/esat_international_fund_raising_campaign/ በሃገራች በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ጨለማ ውስጥ በማቆየት የግዛት ዘመኑን ለማራዘም የዘረጋውም የአፈና ቀንበር ለመስበርና፣ ነጻነት፣ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን የበኩሉን አስተጽዖ ሲያደርግ ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ ኢሳት የተቋቋመበትን ...
Read More »“የኢህአዴግ ስርዓተ-መንግስት ሳይውል ሳይድር በዲሞክራሲያዊ ስርዓት መተካት አለበት” ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዶሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ገለፀ
ኢሳት ዜና:- መድረክ ይህን ያለው፦ “በኢትዮጵያ ድርቅ አለ፤ ረሀብም አለ፤ ኢኮኖሚውም መንግስት እንደሚለው እያደገ አይደለም። የፖለቲካ ምህዳሩም ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠቧል” በሚል ርዕስ ትናንት ባወጣው ባለ ስምንት ገፅ መግለጫ ላይ ነው። ፕሬዚዳንት ግርማና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለፓርላማ ባቀረቡት የአዲስ አመት ንግግር ሰፋፊ ዲስኩሮችን አስደምጠውናል ያለው መድረክ፤በንግራቸው የነካኳቸው ጉዳዮች ብዙ ቢሆኑም በሁሉም ዘርፎች ያሏቸው ነገሮች ስህተት እንደሆኑ መረጃዎችን በመጥቀስ አብራርቷል። በአለም ...
Read More »