የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን (ኢሳት) የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ

ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ተላይት ቴለቪዥን (ኢሳ) ከህዳር እስከ ጥር ወር 2004 . ለሚያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣
http://www.ethsat.com/esat_international_fund_raising_campaign/

በሃገራች በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ጨለማ ውስጥ በማቆየት የግዛት ዘመኑን ለማራዘም የዘረጋውም የአፈና ቀንበር ለመስበርና፣ ነጻነት፣ ፍትህና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን የበኩሉን አስተጽዖ ሲያደርግ ቆይቷል።

በአሁኑ ጊዜ ኢሳት የተቋቋመበትን የነጻ፣ የእውነተኛና ሚዛናዊ የመረጃ ምንጭ የመሆን ራእይ ለመተግበር ወደ አየር ከወጣበት ከሚያዚያ 2002 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ስርጭቱን ቀጥሏል። ኢሳት፣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላልፍ በገዥው ፓርቲ በተደጋጋሚ የተደረገበትን የአፈነ እርምጃ በመቋቋም ወደ አየር እንደተመለሰ ሁሉ፣ በአሁኑ ወቅትም በመጨረሻ የተደረገበትን አፈና ተቋቁሞ ወደ አየር ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። ኢሳት ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ ለማድረስ ተጨማሪ ጥረት በማድረግ የአጭር ሞገድ የሬድዮ ስርጭት ፕሮግራም ሰኞ፣ እሮብና አርብ በ15390 kHz ማክሰኞ፣ ሃሙስ፣ ቅዳሜና እሁድ 15370 kHz ወደ ኢትዮጵያ በማሰተላለፍ ላይ ይገኛል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢሳት፣ እየጠነከረ የመጣውን የገዥው ፓርቲ አፈናን ይበልጥ ለመቋቋም የ24 ሠዓት የሳተላይት ሬድዮ ስርጭት በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ በሳተላይት ቴሌቪዥን ማሰራጨት ጀምሯል። ኢሳት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ (IPTV) በመጠቀም ውጭ ሃገር ለሚገኙ ኢትዮያውያን ስርጭቱን ለማድረስ በቀጥታ በቤታቸው ቴሌቨዥን እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልክ (MOBILE) ማየት የሚችሉበትን አገልግሎት ጀምሯል። ኢሳት፣ በአመስተረዳም፣ በዋሽንግተንና በለንደን የሚገኙትን ስቱዲዮዎች የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሳደግ የሚያስፈልገውን እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ኢሳት፣ በሃገር ውስጥ የሚገኙትን የዜና ወኪሎች ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ኢሳት፣ ድረገጹን ለአገልግሎት አጠቃቀም እንዲያመች (– USER FRIENDLY) ዘመናዊ ይዘት እንዲኖረው ከፍተኛ ጥረት በማድረግ በአገልግሎት ላይ አውሏል።

ኢሳት የሚጠበቅበትን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት እንዲችል ያልተቋረጠ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ይኖርበታል። ከዚህ በፊት የተሰበሰበው ዕርዳታ ኢሳት በየወሩ ከሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጪ አንፃር ሲታይ ላለፉት ተከታታይ ወራት አገልግሎቱን እንዲሰጥ ያስቻለው ቢሆንም፣ በቀጣይ ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው አይደለም። በዚህም መሠረት፣ ኢሳት አገልግሎቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ለማስቻል የሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ቀጣይ ድጋፍና እገዛ ይሻል።

ይህንንም ለማስፈጸም የኢሳት የገንዘብ እርዳታና የአጠቃቀም ልምድ እንዳሳየን ለአሰባሰብም ሆነ ለአጠቃቀም አስተማማኝና አመቺ ሆኖ ያገኘነው፣ በየወሩ ከባንኮ ወደ ኢሳት ባንክ በሚከፈል የቋሚ ትእዛዝ እርዳታ ነው። በየወሩ ከባንኮ ወደ ኢሳት ባንክ የሚተላለፈው የሂሳብ መጠን አሁን ኢሳት ባለበት የገንዘብ ወጪ አኳያ በትንሹ ከሃያ የአሜሪካ ዶላር ($20) ጀምሮ ሊሆን ይገባዋል። አቅሞት የሚፈቅድ ከሆነ በወር ከተቀመጠው ዝቅተኛ ክፍያ ($20)  በላይ በቋሚነት ሊረዱን ይችላሉ።

በተለያዩ ምክንያቶች ከባንካችሁ በቀጥታ በየወሩ ለኢሳት እርዳታ ማድረግ ለማትችሉ ወገኖች በአሁኑ ግዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ላይ ያቀረብናቸውን $100/£100/€100 ልዩ ትኬት የምትችሉትን ያህል ብዛት በመግዛት ወገናዊ ግዴታችሁ መወጣት ትችላላችሁ።  የትኬት አቅርቦት በተመለከተ የአካቢዎን  የኢሳት ተወካይ ለማግኘት እንዲችሉ በኢሳት ድረ ገጽ ላይ የተቀመጠውን የስልክ መረጃ መጠቀም ይችላሉ።

በየወሩ በሚደረግ ክፍያና በገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ከምትገዙት ትኬት በተጨማሪ በማንኛውም ወቅት እርዳታ ለማድረግ የምትፈልጉ ወገኖች በኢሳት ድረገጽ ላይ የተቀመጠውን የፔፓል አገልግሎት መጠቀም ትችላላችሁ።

በመጨረሻም፣ ኢሳት በዚህ አጭር እድሜው ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውታል። እነዚህ ፈተናዎች ቀላላ አልነበሩም። ፈተናዎቹን ለመወጣት ባደረገው ጥረት በቂ ተመክሮ አዳብሯል። ኢሳት ከፈተናዎቹ ያዳበረውን ልምድ በመጠቀምና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን ምንም ዓይነት ፈተና ማለፍ እንደሚቻል ሙሉ እምነት አለው። ለዚህም ነው ኢሳት የእያንዳንዱን ሃገርና ወገን ወዳድ እርዳታና ድጋፍ በመጠየቅ ለዕርሶም ጥሪውን የሚያቀርበው።

የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!!!
ኢሳትን መደገፍ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለችውን ሀገራችንና ወገናችንን መታደግ ነው!!!

የኢሳት አስተዳደር
www.ethsat.com