በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት ሊያደርጉ ነው

ኢሳት ዜና:- በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት የሻማ  ማብራት ሥነ-ሥርዐት ሊያደርጉ ነው:: ማርች ፎር ፍሪደም ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ኢትዮጵያኑ ኖቪምበር 6 በኋይት ሀውስ ለፊት ከ6ፒኤም ጀምሮ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት በማድረግ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱና የኦባማ አስተዳዳር በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ጫና እንዲያሳርፉ ይጥይቃሉ። በስነስርአቱ ላይ ...

Read More »

በአርባ ምንጭ በተነሳው ውዝግብ የታሰሩ 28 ሰዎች አለመለቀቃቸው ታወቀ

ኢሳት ዜና:-ግለሰቦቹ የታሰሩት አካባቢውን ህዝብ ለአድማ ለማነሳሳት ሙከራ አድርጋችሁዋል ተብለው ነው። ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደም የመንግስት ባለስልጣናት የአካባቢውን ደን በመመንጠር ሰፋፊ ቤቶችን ለግል የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አውለዋል በሚል መታሰራቸው ይታወቃል። እስረኞቹ አቤቱታቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ድረስ ቢያቀርቡም ሰሚ አጥተው ከቆዩ በሁዋላ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ለምን አጋላጣችሁን በሚል ሰብስበው ማሰራቸው ታውቋል። ምንም እንኳ ግለሰቦቹ ያቀረቡት አቤቱታ መንግስት ዘግይቶም ቢሆን ትክክል ነው ቢልም ፣ ...

Read More »

በዋካ ከተማ የፌደራል ፖሊስ አሁንም ከተማውን በመቆጣጠሩ ለአራተኛ ቀን ህዝቡ እንደልቡ አንዳይንቀሳቀስ መደረጉን ዘጋቢያችን ገለጠ

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ማክሰኞ በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ ከመብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አንድም ሰው በመንገድ ላይ እንዳይንቀሳቀስ በመከልከሉ ከተማው ጭር ብሎ መዋሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌላ፣ ተምህርትቤቶች እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መዘጋታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች  ተናግረዋል። በስፍራው ተገኝቶ መረጃዎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው የደቡብ ተወካያችን እንዳለው፣ በፖሊስ ጣቢያ የነበሩት አገር ...

Read More »

በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ ከመብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ያነሳው ተቃውሞ ለሶስተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ማክሰኞ  ከወረዳና ከልማት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ በቀጠለበት ሰአት የፌደራል ፖሊስ ማንኛውም ሰው በከተማው ሲንቀሳቀስ ቢገኝ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በሺ የሚቆጠሩ የፌደራልና የክልሉ ፖሊስ አባላት በከተማው ዋና ዋና መንገዶችና ማህበራዊ አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ላይ ጥበቃ በማድረግ ህብረተሰቡ በነጻነት እንዳይንቀሳቀስና ቤቱ ውስጥ እርፎ እንዲቀመጥ እያስፈራሩ ነው። በስፍራው ተገኝቶ መረጃዎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው የደቡብ ተወካያችን እንዳለው፣ የክልሉና የፌደራል ባለስልጣናት ህዝቡ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አርቲስቶች በቅርቡ ወደ ሕንድ ዴሊ በመጓዝ ያሳዩትን ትርዒት ተከትሎ የቀረበ ዘገባ ውጥረት ማስከተሉን ታወቀ

ለውዝግቡ መነሻ የሆውን  እና የኢትዮጵያውያንን ስሜት የሚጎዳውን ጽሁፍ ያተመው ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንድያ ጋዜጣ ዘገባውን እንዲያርም፣የኢትዮጵያ ኤምባሲም ማስተባበያ እንዲሰጥ በህንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጠይቀዋል። በህንድ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ያስቆጣው ዘገባ፣  በዘ ታይምስ ኦፍ ኢንድያ ኦክቶበር 20/2011 የወጣው እትም ነው። ለዘገባው መነሻ የሆነው ከኦክቶበር 15 እስከ 21/2011 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር የባህል ቡድን በኢንዲያን ኢንተርናሽናል ሴንተር ያሳየው የሙዚቃ  ትርኢት ነው፤ ይህንን የሙዚቃ ...

Read More »

በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን የዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ ከመብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ያነሳው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ዜና:- ማክሰኞ እለት ከወረዳና ከልማት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ ሌሊቱን በሙሉ አድሮ በማግስቱም ተጠናክሮ መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአካባቢው እና የክልሉ ፖሊስ ሁኔታውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በ7 መኪና የተጫኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት በስፍራው ተገኝተዋል። የክልሉና የፌደራል ባለስልጣናትም በአካባቢው ተገኝተዋል። እስካሁን ድረስ ከ26 አላነሱ ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውንና 4 ግለሰቦችም ተደብድበው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ከተሳሩት መካከል አቶ አድነው ማሞ፣ ተፈራ ታደሰ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ከሀላፊነታቸው የተነሱት፦”ብቃት ስለሌላቸው” ነው ሲሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ

ኢሳት ዜና፡- ብአዴኖች በህወሀት ክፍፍል ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ታማኝነታቸውን በማሳየታቸው ምክንያት በሹመት በተንበሸበሹበት ወቅት ነው- የብአዴኑ አቶ ከፍያለው አዘዘ- ከመንግስት ጋዜጠኝነት ተነስተው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት። ለረዥም ጊዜ  የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የቆዩት አቶ ከፍያለው አዘዘ በአቶ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው ካቤኔ አዲስ አበባን ማስተዳደር ሲጀምር  የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተመደቡ። ይሁንና አቶ አዲሱ ለገሰን፣ ...

Read More »

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በመድረክ ላይ የሚያደርገውን ወከባ አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ

ኢሳት ዜና፡- ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመልከተው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመድረክ አባላት ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። የአረና ትግራይ አባል የሖነው አማረ ተወልደ በሁመራ አካባቢ የድርጅቱን ወረቀት ሲበትን ተገኝቷል በሚል ሰበብ ለበርካታ ቀናት በቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ በመጨረሻም ንብረቱንና እቃዎቹን ተቀምቶ በሳምንቱ መጨረሳ ተለቋል። በተመሳሳይ ዜናም የዚሁ የአረና ትግራይ አባል የሆኑት አቶ አያሌው በዬነ በሽሬ ከተማ የፓርቲውን ወረቀት ...

Read More »

የሜድሮክ ኮንስትራክሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

ኢሳት ዜና:- ከ 500 በላይ የሚሆኑት የሚድሮክ ጉርድ ሾላ፣ የረር በርና አያት ሳይት መንገድ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ የመቱት፤  ባለፈው ሐሙስ ነው። ኑሮ ሰማይ በነካበት በአሁኑ ሰዓት የአብዛኞቻችን ደመወዝ ከ 500  ብር ብዙም አይበልጥም የሚሉት እነዚሁ ሠራተኞች፤”‹ከዚህች ኪስ ከማትገባ ደመወዝ ላይ ለታክስና ለዓባይ ግድብ ተቆርጦላት  በእጃችን የምትደርሰን ከቤት ኪራይ እንኳ የማታልፍ ሆናለች>›ሲሉ ምሬታቸውን አሰምተዋል። “የዓመታት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያችን ምላሽ ሊያገኝ ...

Read More »

የምክር ቤት አባልነቴ፤ በቴሌቪዥን ቢሆንልኝ ይሻል ነበር” ሲሉ በፓርላማው ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪል ተናገሩ

ኢሳት ዜና:- አቶ ግርማ ሰይፉ ከአውራምባ ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፤ ሰሞኑን አቶ መለስ በፓርላማ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከወትሮው በተለየ መልኩ በ አቶ መለስ አስተያዬት ዙሪያ ሀሳባቸውን ለመስጠት እንዳልተፈቀደላቸው ጠቅሰዋል።   “ይህ ነገር መታረም ካልቻለ  ምናልባትም ለምክር ቤቱ ጥያቄዎቻችንን አስገብተን እሳቸው መልስ እንዲሰጡና እኛ በቴሌቪዥን ብንከታተል የሚሻል ይመስለኛል”ያሉት አቶ ግርማ፤ “የምክር ቤት አባል መሆኔ ትርጉም የሚኖረው፤በተሰጡት አስተያዬቶች ላይ ሀሳቤን በማንጸባረቅ ስችል ይመስለኛል”ብለዋል። ...

Read More »