በጄኔራል ከማል ገልጁ የሚመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ፣ የሚደነቅ ነው ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም

ኢሳት ዜና:- የቀድሞው የኦፌዴን ሊቀመንበር እና አሁን የንቅናቄው የክብር ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለኢሳት እንደተናገሩት  በጄኔራል ከማል ገልቹ የተመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ በደስታ ነው የምከታተለው ብለዋል።

“የኦሮሞ ህዝብ የሚሸሽ ወይም የሚገነጠል ህዝብ አይደለም” የሚሉት አቶ ቡልቻ፣ ሁሉም በዚህ ሀሳብ ዙሪያ ቢሰባሰብ ጤነኛ እንሆናለን ሲሉ አክለዋል ።

አቶ ቡልቻ የጄኔራል ከማል ቡድን ከዚህ በፊት ሌላ አይነት ፕሮፓጋንዳ ሲመገብ ያደገውን ወጣት ለመቀየር ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው አልሸሸጉም።