የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚሰሩዋቸው ቤቶች በአመት በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ እንደሚከራዩ ሰነዶች አመለከቱ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚሰሩዋቸው ቤቶች በአመት በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ እንደሚከራዩ ሰነዶች አመለከቱ  የኢሳት የምርመራ ክፍል  በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰሩ ህንጻዎችን ባለቤቶች ለማወቅ ባደረገው ጥረት የተወሰኑትን ህንጻዎች ባለቤቶችና የወጣባቸውን ወይም የሚወጣባቸውን የገንዘብ መጠን ባለፈው የካቲት ወር ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።  በተለምዶ ቦሌ መድሀኒአለም እየተባለ በሚጠራው  ወይም ወረዳ አስራ ሰባት ውስጥ በምእረባዊያን የቤት ...

Read More »

የመምህራን ውዝግብ ዛሬም አልበረደም

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ እና የመሠናዶ ትምህርት መምህራን ሰኞ ወደ ማስተማር ተግባራቸው ከመመለሳቸው በፊት በየትምህርት ቤታቸው እንዲሰባሰቡና በግላቸው ተወያይተው የአቋም መግለጫ በማውጣት ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ለየወረዳ፣ ክፍለ ከተማ እና የአዲስ አበባ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲያስገቡ ጥሪ እያስተላለፉ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ከአስተዳደሩ እውቅና ውጪ የሚደረጉ ስብሰባዎች ሁሉ ...

Read More »

ከደቡብ ክልል 22 ሺህ የአማራ ተወላጆች ተፈናቀሉ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከመካከላቸው ሰባ የሚሆኑት በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት  ጽህፈት ቤት ውስጥ የተጠለሉ ሢሆን፤ብዙዎቹ ተፈናቃዮች ግን  ወደ አዲስ አበባ ቢመጡም መጠለያ አጥተው እየተንከራተቱ መሆናቸውን መኢአድ አስታውቋል። የመኢአድ ዋና ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ እንዳሉት፤ ከቤንች ማጅ ዞን ጉራ ፋርድ ወረዳ ቤትና ንብረታቸውን ጥለው የተሰደዱት እነዚህ ወገኖች  አዲስ አበባ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ለመጠለል ቢሞክሩም በጥበቃ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ 21 ኛ ፎቅ ላይ ራሷን መወርወሯ ተዘገበ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሻርጃህ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ታገለግል የነበረች  የ 23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ከ 21 ኛ ፎቅ ላይ ራሷን መወርወሯን ሻርጃህ ታይምስ ዘገበ። በሻርጃህ ፖሊስ የሞራልና  የምክር አገልግሎት ዲፓርትመንት  ዳይሬክተር ማጆር መሀመድ ሰኢድ አልሸሂ እንደገለጹት፤ በአረብ ቤተሰብ ውስጥ ትሠራ የነበረችው  ኢትዮጵያዊት ወጣት ራሷን ከምትሠራበት ፎቅ ቤት ላይ በወርወር  ህይወቷን እንዳጠፋች ለሻርጃህ ፖሊስ መረጃው ...

Read More »

የቦረናና ጉጂ ዞን ነዋሪዎች ድረሱልን ይላሉ

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎቹ ጥሪውን ያሰሙት የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን የወርቅ ኩባንያ የሆነው ሚድሮክ ወርቅ ፣ ለተጨማሪ ወርቅ ፍለጋ አካባቢውን ይፈልገዋል ተብሎ መነገሩን ተከትሎ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ከአመት በፊት በአካባቢው ተነስቶ የነበረው ተቃውሞ የመጨረሻ መፍትሄ ሳያገኝ በእንጥልጥል ላይ ባለበት ወቅት፣ አሁን ደግሞ አካባቢው ለወርቅ አሰሳ እንደሚፈለግ በመነገሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የመፈናቀል አደጋ አጋጥሞአቸዋል። ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያጋልጥ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ተመረቀ

 መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአራት የተለያዩ አገሮች ተሰደው በኔዘርላንድስ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞችን በመጠቀም የተሰራው ፊልም ዛሬ ሄግ በሚገኘው የፊልም አዳራሽ በርካታ እንግዶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ተመርቋል። ኢትዮጵያን በመወከል በፊልሙ ውስጥ የተሳተፈው የኢሳት ጋዜጠኛ የሆነው ፋሲል የኔአለም ነው። ሊዙ ፣ ፋቲ እና ጅግሜ የተባሉ ከቻይና፣ ከሊቢያና ከቡታን የመጡ ስደተኞችም በፊልሙ ውስጥ ተሳትፈዋል። የ90 ደቂቃ እርዝመት ባለው ፊልም ...

Read More »

የፍትህ ዌብሳይት እንዳይታይ መታገዱ ታወቀ

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡኩ ላይ ባሰፈረው መልክት ድረገጻቸው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ታግዷል። ተመስገን ይህን ድርጊት ለፈጸሙት ወጎነች ” መታፈን አማራጭ ቀዳዳዎችን ይፈጥራል፣ ጭቆናም ይበልጥ ያጠነክራል፣ መገፋትም ተከሻን አደንድኖ መልሶ መግፋትን ያስተምራል። ወደድንም ጠላንም አዲሱ ትውልድ ከዚህ በላይ መሸወድም ሆነ ቀጥቅጦ ወይም አባብሎ መግዛት አይቻልም። ለዚህም ነው ...

Read More »

በስዊዘርላንድ ኢትዮጵያዊቷ ራስዋን ከፎቅ ላይ በመወርወር ህይወትዋን አጠፋች

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስዊዘርላንድ ካንቶን ሴንትጋለን ነዋሪ የነበረች ኢትዮጵያዊት ራስዋን ከፎቅ ላይ በመወርወር ህይወትዋን አጠፋች  መዲና ሱሌይማን የተባለች የ28  ዓመት ወጣት ኢትዮጵያዊት ባለፈው እሁድ ማርች 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ህክምና ስትከታተል ከነበረችበት ኡዝናህ ከሚገኘው የአዕምሮ መታከሚያ ሆስፒታል ክፍል ፮ኛ ፎቅ ዘላ በመውረድ ራስዋን ማጥፋትዋን ለማወቅ ተችሏል። ይህች ወጣት ኢትዮጵያዊት ራስዋን ያጠፋችበት ትክክለኝ ምክንያት በውል ባይታወቅም ...

Read More »

የመምህራን የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሎአል

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በቅርቡ ለመምህራን ያደረገውን የደሞዝ ጭማሪ በመቃወም በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች በትናንትናው እለት የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሎአል። በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ ቁጭት እና ስሜት እንዳለ በሚነገርበት በአሁኑ ጊዜ ተቃውሞው ወደ አማራ ክልል ሊሸጋጋር ይችላል በሚል የደህንነት ሀይሎች በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራንን ሲያስፈራሩ እንደነበር መረጃዎች አመልክተዋል። ...

Read More »

የዋጋ ንረት ያልተረጋጋው የግብርና ምርት ባለማደጉ መሆኑን የብሄራዊ ባንኩ ገዢ አመኑ

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብሄራዊ ባንኩ ገዢ የሆኑት አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ለፓርላማ አባላት እንደተናገሩት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ባንኩ የተለያዩ ገንዘብ ነክ እርምጃዎችን ቢወስድም ሊሳካለት አልቻለም። ዋናው ችግር ከግብርና ምርት አቅርቦት ጋር የተያያዘ መሆኑን የገለጡት ገዢው፣ ግብርናው እስካላደገ ድረስ የዋጋ ንረትን መቆጣጠር እንደማይቻል ገልጠዋል። መንግስት በግብርና ምርቶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አህል በብዛት ወደ አገር ውስጥ ...

Read More »