አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት “ፓርላማ” ብሎ በሚጠራው የገዥው ፓርቲ አባላት ስብስብ ውስጥ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ  ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ።

በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ የሚወሰዱ ልጆችን የጤና ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል መመሪያ ለህፃናት ሀኪሞች ተዘጋጀ፡

በጉዲፈቻ የሚወሰዱ አዳዲስ ህፃናትን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ከዕድሜያቸዉና ከአስተዳደጋቸዉ ጋር የተያያዘ አጠቃላይ የጤና ምርመራና ክትትል ለማድረግ በቂ መረጃ ባለመኖሩ ችግር እንዳለ በመግለፅ የአሜሪካ የህፃናት ህክምና አካዳሚ አንድ መመሪያ ማዘጋጀቱን አሜሪካን ሜዲካል ኒዉስ ገለፀ።

ቁጥራቸዉ 22 ሺህ የሚሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚወሰዱትን የጉዲፈቻ ህፃናት ጨምሮ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በየአመቱ ከ100 ሺህ በላይ የሆኑ ህፃናት በጉዲፈቻ የሚገቡ ሲሆን ብዙዎቹ ከባህሪይ እና ከአስተዳደግ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዳሉባቸዉ መመሪያዉ ይተነትናል። 

አብዛኛዎቹ ህፃናት ከድሃ የህብረተሰብ ክፍል ወይንም በጦርነት ከተጎዱ  አካባቢዎችና ከማቆያ ወይንም ከመንከባከቢያ ተቋሞች የሚወሰዱ በመሆናቸዉ የተለያዩ የጤናና የአስተዳደግ ችግሮች፤ ሊኖሯቸዉ እንደሚችሉ የአካዳሚዉ ሪፖርት ያመለክታል። 

በአለምአቀፍ ደረጃ የሚደረግን የጉዲፈቻ የጤና መረጃ ለማግኘት ችግር እንዳለ በመግለፅ በተለይም ከቻይና እና ከኢትዮጵያ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑ ተጠቅሷል።

ለዚህም አይነተኛዉ ምክንያት አብዛኛዎቹ ህፃናት ቤተሰቦቻቸዉን በሞት ያጡ አሊያም ማንነታቸዉ በማይታወቅ ደረጃ የተጣሉ መሆናቸዉን በሲያትል የዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ማእከል የጉዲፈቻ ህክምና ዳይሬክተር  ፕሮፌሰር ጁሊያ ብሌድሶ ገልፀዋል።

ለጉዲፈቻ ህፃናት የሚደረገዉ የህክምና ክትትል እንደየአገሮቹ ሊለያይ እንደሚችል በመግለፅ ህፃናቱ የሳምባ፤ የኤች አይ ቪ እና የጉበት በሽታዎችን በመሳሰሉት ላይ ወደ አሜሪካ ከመግባታቸዉ በፊት ብዙዉን ጊዜ ምርመራ  እንደማይደረግላቸዉ ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት የህፃናት ሃኪሞች ከአጠቃላይ የጤና ምርመራ ባሻገር፤ የቆዳ፤ የአባለዘርና ተያያዥ ተላላፊ በሽታዎችን እንዲሁም የአዕምሮና ከአእምሮ ጋር የተያያዙ የአስተዳደግ የጤና ጉድለቶችን በሰፊዉ እንዲመረምሩ መመሪያዉ የሚያዝ መሆኑን የአሜሪካ ሜዲካል ኒዉስ ገልጿል።