በማላዊ 70 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ማላዊን ከታንዛኒያ በሚያዋስነዉ አካባቢ በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰዉ ገብተዋል የተባሉ 70 ኢትዮጵያዊያንና አንድ የሶማሊያ ዜጋ በፖሊስ ተይዘዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ኦል አፍሪካን ኒዉስ ገለፀ።

ህገወጥ ስደተኞቹን ረድታችሁዋል ተብለዉ 3 የማላዊ ዜጎችም በእስር ላይ ይገኛሉ። በጢሻ ዉስጥ ተደብቀዉ የነበሩት ስደተኞች የተያዙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት መሆኑን የገለፁት የአካባቢዉ የፖሊስ አዛዥ ስደተኞቹ በተሸሸጉበት ስፍራ በመፈራረስ ላይ ያለ የአንድ ሰዉ አስከሬን መገኘቱን በተጨማሪ ገልፀዋል።

አስከሬኑ በረሃብ ወይንም በበሽታ የሞተ የህገወጥ ስደተኛ ሊሆን እንደሚችልና እዚያዉ እንዲቀበር መደረጉን የገለፁት የፖሊስ አዛዥ እስረኞቹ ያለህጋዊ ፈቃድ ስለመግባታቸዉ ክስ የሚመሰረትባቸዉ መሆኑን አመልክተዋል።  

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide