ኩፍኝ፣ መንጋጋ ቆልፍ እና ወባ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባወጣዉ ሪፖርት ባለፈዉ ሳምንት በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ዉስጥ እንዲሁም በአጎራባች የጋሞ ጎፋ ዞን እና በአማራ ክልል አዊ ዞን አንካሻ ወረዳ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዲባት ወረዳ በሽታዎቹ በአዲስ መከሰታቸዉን ገልጿል። 

የተጠቀሱት ክልሎች የጤና ቢሮዎች ከአለም የጤና ድርጅት ባለሙያዎች ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ጥናት በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ሪፖርት አመልክቷል።

የሜንኒጃይተስ በሽታን መከሰት ምክንያት በማድረግ ከደቡብ ክልል የጤና ቢሮ፤ ከኢትዮጵያ የጤናና የምግብ ጥናት ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአለም የጤና ድርጅት የተዉጣጡ ባለሙያዎች ከ40 በላይ በበሽታዉ አዲስ የተያዙ በሽተኞች መገኘታቸዉ ወደ ተደረሰባቸዉ ከምባታ ተምባሮ እና ወላይታ ዞኖች መሰማራታቸዉን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለደረሰዉ የጤና ሁኔታ በአካባቢዉ የሚታየዉ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ችግር እንደሆነ የገለፀዉ የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት በክልሉ ዉስጥ ከሚገኙት የእጅ የዉሃ ጉድጓዶች ዉስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ ወይንም የተበላሹ መሆናቸዉን አስታዉቋል።  

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide