ኢትዮጵያውያን በኦስሎ ኖርዌይ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው የተደረገው የኖርዌይ መንግሥት የፖለቲካ ከለላ የጠየቁ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ከመለስ መንግስት ጋር ስምምነት መፈራራሙን በመቃወም ነው። ስምምነቱ የመኖሪያ ህጋዊ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውያን እስከ ማርች 15-2012 ድረስ አገር ለቀው ይወጣሉ። 

ማርች ሁለት እና  5  በኦስሎ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሥርአቱን በመቃውም   አገራቸውን ለቀው የወጡ እንዲሁም ስደተኞች እንዲሁም በጋብቻ ትስስር ከኢትዮጵያውያን ጋር ቁርኝት ያላቸው ኖርዌጅያኖች ጭምር ተሳትፈዋል።

በዕለቱ የህወሀት ነባር ታጋይና መስራች ከነበሩት ከአቶ ግደይ ዘርአጺዮን በተጨማሪ የስደተኛውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ፣ ከ-አንቲ ራሲስቲስክ ድርጅት ፣ኖአስ ተብሎ ከሚጠራው ለስደተኞች ከቆመው ድርጅት ፥ ከ-ማርች ፎር ፥ከ-ፔን  እና ረኧድት ተብሎ ከሚጠራው ፓርቲ ጭምር ተወካዮች ተገኝተው ፣ የስደተኛውን ጥያቄ በመደገፍ ተራ በተራ ንግግር አድርገዋል፡፡

ማርች 5 ቀን 2012 በተካሄደው ሰልፍ ቁጥሩ ወደ ሁለት መቶ የሚጠጋ ከተለያየ ካምፕ የመጡ ስደተኞች ተካፍለዋል።

የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያንን በሀይል ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት እያስተቸው እንደሚገኝ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide