መንግስት ለሙስሊሙ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ አልሰጠም

የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወሊያ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላቀረቡት የመብት ጥያቄ መንግስት ለህዝቡ ተወካዮች፣  ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2004 ዓም መልስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ምንም እንኳ መንግስት የሰጠው መልስ በይፋ ለህዝብ ባይገለጠም  መልሱ አውንታዊ አይደለም በሚል ህዝበ ሙስሊሙ እየተነጋገረበት ነው። መንግስት መጅሊሱ መጠነኛ ተሀድሶ ተደርጎለት እንዲቀጥልና  የአህባሽ አስተምህሮ በመጂሊሱ የተደገፈ በመሆኑ እምነቱን የማስፋፋቱ እንቅስቃሴ መቆም የለበትም የሚል ...

Read More »

ዶናልድ ፔይን በጠና ታመዋል

የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ እውነተኛ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባ ዘንድ ያለማሳለስ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት አፍሪካዊ አሜሪካዊው ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን፤ በጠና መታመማቸው ተዘገበ። በብዙሀን ኢትዮጵያውያን ዘንድታላቅ ስፍራ ያላቸው የኒው ጀርሲው ተወካይና የዲሞክራቲክ ፓርቲው  አባል ዶናልድ ፔይን የታመሙት በአንጀት ካንሰር  ነው። እንደ “ፖሊቲኮ” ብሎግ ዘገባ፤ የአንጀት ካንሰሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ህመሙ በዶናልድ ፔይን ላይ ያየለባቸው ሲሆን፤ ህይወታቸው ...

Read More »

ስኳርና ዘይት ተመልሰው ከገበያ ጠፉ

የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች ስኳርና ዘይት ተመልሰው የውሀ ሽታ ሆነዋል፡፡ ዘጋቢያችን እንደሚለው መንግስት የዘይት ሀይቅ እንፈጥራን፣ የስኳር ተራራ እንገነባለን እያለ በመገናኛ ብዙሀን ሲናገር ቢቆይም፣ ለእቃዎች ተመን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ስኳርና ዘይት ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር ነበረባቸው። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ሸቀጦች ሙሉ በሙሉ ከገበያ በመጥፋቱ ህዝቡ እየተማረረ ነው። በሌላ በኩል የህወሀት ባለስልጣናት እና ጉናን ...

Read More »

ህይወታችን ሲኦል ሆኖል ይላሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጤፍ ዋጋ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጭማሪ ማሳያቱ ህይወታችንን  ሲኦል አድርጎታል ሲሉ  የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ተናገሩ ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ከሳምንት በፊት አንድ ጣሳ ጤፍ 10 ብር ሲሸጥ የነበረ ቢሆንም፣ በሳምንት ውስጥ የ8 ብር ጭማሪ በማሳየት 18 ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጤፍ ዋጋ መጨመርን ተከትሎም በርካታ እቃዎች እየጨመሩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው እንደተናገሩት በእህልና በሌሎች ...

Read More »

የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ቀጠሮ ሊራዘም ይችላል

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት የሀሰት ክስ ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ፣ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን በመቃወም የመከላከያ መልሶቻቸውን ለማቅረብ ለፊታችን ሰኞ የካቲት 26፣ 2004 ዓም የተቀጠሩ ቢሆንም፣ ዳኞቹ የብይኑን ዝርዝር ለጠበቆች ማስተላለፍ ሲገባቸው እስካሁን ድረስ ለማስተላለፍ ባለመቻላቸው፣ ችሎቱ ለሌላ ጊዜ ሊራዘም እንሚችል ለማወቅ ተችሎአል። ጠበቆቹ እስከ ትናንት ድረስ ብይኑ በጽሁፍ ተገልብጦ እንዳልተሰጣቸው ምንጮች ...

Read More »

የደቡብ ክልል ግምገማ ሌሎች ችግሮችን ጥሎ ማለፉ ተነገረ

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከየካቲት 19 እስከ 23 ቀን በክልሉ በተካሄደው አራተኛው ዙር አስቸኳይ ጉባኤ  የአዋሳ ከንቲባ የነበሩት  አቶ ሽብቁ መገኔ እንዲታሰሩ ሲወሰን እርሳቸውን ከጀርባ ሆነው ሲደግፉዋቸው በነበሩት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ላይ ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። ከወራት በፊት በአዋሳ ከተማ በሺ የሚቆጠሩ ቤቶች እንዲፈርሱ በተደረገበት ጊዜ ከንቲባው  ከሌሎች አካባቢዎች የመጡትን ወይም መጤ እያሉ የሚጠሩዋቸውን ነዋሪዎች ቤታቸው ...

Read More »

ቦሌ መንገድ የንግድ ማእከልነቱ እያከተመ ነው ተባለ

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በቦሌ መስመር የተጀመረው የመንገድ ግንባታ የመኪና ማቆሚያ ወይም ፓርኪንግ የሚተው ባለመሆኑ፣ የቦሌ የንግድ ማእከልነት እያበቃ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኢሳት ዘጋቢ ነዋሪዎቹን አነጋግሮ እንደዘገበው ከአብዮት አደባባይ እስከ ቦሌ አየር ማረፊያ በሚወስደው መንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አልተተወም። በዚህም የተነሳ የቦሌ የንግድ ማእከልነት የሚቀዘቅዝ በመሆኑ፣ በአካባቢው የንግድ ድርጅቶችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች እየለቀቁ ነው። በርካታ ...

Read More »

የኬንያ፣ የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ የጋራ ፕሮጀክት

የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በጣምራ  እጅግ ታላቅ የሆነ ወደብና የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ላማካሄድ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ በ አፍሪካ ደረጃ ታላቅ ነው የሚባለው ፕሮጀክት  23 ቢሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት ወደ 400 ቢሊዮን የሚደርስ የኢትዮጵያ ብር ይፈጃል። ይሁንና ይህ ወጪ በማንና እንዴት እንደሚሸፈን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ፕሮጀክቱ የሚገነባውም ...

Read More »

የአድዋ ድል 116ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓል ተከበረ

የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መላው ኢትዮጵያዊ በነቂስ ወጥቶ የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድል ያደረገበት ቀን በአዲስ አበባ ጀግኖች አርበኞች በተገኙበት ተከብሮአል። የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መላው አፍሪካን ለመቀራመት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1884 እስከ 1885 በፖርቱጋል አስታዋሽነት እና በጀርመን አዘጋጅነት የበርሊን ጉባኤ እየተባለ የሚጠራውን ስምምነት ፈርመዋል። ስምምነቱ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በሚያደርጉት ሩጫ እርስበርሳቸው እንዳይገጩ ዋስትና የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካን ህልውናም በነጮች እጅ ...

Read More »

ዛሬም በጁምዓ ጸሎት ብዙ ህዝብ ተገኘ

የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁምአ ( አርብ) ጸሎት እንደወትሮው ሁሉ በመቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ተገኘ ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው የጁምአ ጸሎት እስከዛሬ ከተገኘው የበለጠ ህዝብ ተገኝቶ  ስነስርአቱን ተካፍሏል። በስነስርአቱ ላይ መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ ገብቶ ለመከፋፈል የሚያደርገውን ሙከራ ለማሳየት ፣ በድምጽ  የተቀነባበረ ማስረጃ ለህዝብ ቀርቧል። በርካታ ሙስሊሞች መንግስት ህገመንግስቱን በመጻረር በእምነት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቱን ሲቃወሙት ተሰምተዋል።በእለቱም መጅሊስ ...

Read More »