(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2019) ሕወሃት 7 ሺ የልዩ ሃይል አባላቱን በራያ ኮረም አካባቢ ማስፈሩ ተነገረ። ይህንኑ ተከትሎም የራያ ማንነት አስመላሽ አብይ ኮሚቴ እልቂት ከመፈጠሩ በፊት የፌደራል መንግስቱ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ37 ሺ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ልዩ ሃይል በአካባቢው መስፈሩን ኮሚቴው አስታወቋል። ይህ በእንዲህም ሕወሐት ሚሊሻዎቹን እያሰፈረ የሚገኘው ከክልል ሶስት ጋር ጦርነት ለማካሄድ እንደሆነ ...
Read More »በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን ፎቶ ሲያነሱ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2011) በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥረው በቀረቡ ግለሰቦች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከፌደራል ፖሊስ ያገኘውን መረጃ ጠቀሶ ፋና እንደዘገበው ሁለቱ ግለሰቦች ወደ ፍርድ ቤቱ በድብቅ በመግባት ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሲያሰራጩ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹ ...
Read More »ኢፓድ ተመሰረተ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 11/2011) በኢትዮጵያ በመድሃኒት አቅርቦትና ጥራት ላይ እገዛ የሚያደርግ የዲያስፖራ ፋርማሲና የመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዎች ስብስብ ያለበት ተቋም በዋሽንግተን ዲሲ በይፋ ተመሰረተ። የኢትዮጵያ የፋርማሲስቶችና የመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዎች ማህበር/ኢፓድ/ በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያን ኤምባሲ በተካሄደ ስነስርአት የማህበሩ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት በሃገሪቱ በመድሃኒት ቁጥጥርና ስርጭት እንዲሁም በጥራት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ይህ ጥረት የመድሃኒት ፋብሪካዎችን በኢትዮጵያ እስከመገንባት እንደሚሄድ የማህበሩ አመራሮች ገልጸዋል። ...
Read More »አብቁተ የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2011)የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) በአማራ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ። አብቁተ ከማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታወቋል ። ጥረት ኮርፖሬት በበኩሉ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታወቋል የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም /አብቁተ/ ድጋፉን ያደረገው የክልሉ መንግሥት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ...
Read More »ኦዴፓ በብሔሮች ራስን የማስተዳደር መብት ላይ አልደራደርም አለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት/2011)በፌደራል ስርዓቱ በብሄሮች ራስን የማስተዳደር መብት ላይ ከማንም ጋር እንደማይደራደር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ገለጸ። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ብሏል። የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እና የአፋን ኦሮሞ ሁለተኛ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆንም እየተሰራበት መሆኑን ኦዲፒ ገልጿል። ኦዴፓ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች መካከል ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ለፌደራል ...
Read More »በለውጥ ስም ሃገርን የሚበታትን ተግባር ሊቆም ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011)የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ በለውጥ ስም ሀገርን የሚበታትን ተግባር ሊቆም ይገባል ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጠ። የህወሓት 44ኛው የምስረታ በአልን ምክንያት በማድረግ የማዕከላዊ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ የሀገሪቱን ህገመንግስትና ፌደራላዊ ስርዓቱን ለማፍረስ የውስጥ ትምክህት ሀይልና ጸረ ልማት የሆኑ የውጭ ሀይሎች አንድ ላይ በመቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡ እናም የትግራይ ሕዝብና ብሄር ብሄረሰቦች እንዲሁም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ህይሎችና አጋር ድርጅቶች በትምክህትና በጥገኝነት ላይ ...
Read More »በጎንደርና ባህርዳር ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በሶስት አመት ይጠናቀቃል
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት11/2011)በአማራ ክልል ጎንደርና ባህርዳር ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በ1መቶ ሚሊየን ብር ለመገንባት የሚንቀሳቀሰው ወንፈል ተራድኦ ተቋማቱን በሶስት አመታት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል ገባ። በአሜሪካን ሃገር የተቋቋመውና በክልሉ ተወላጆች ኢትዮጵያውይን የተመሰረተው ድርጅት ግንባታውን የሚያከናውነው ከአማራ ልማት ማህበር ከዩኒቨርስቲዎች ጥምረት ፎረምና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ነው። የወንፈል ተራድኦ ስራ አስፈጻሚ አባላት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ለግንባታው ከሚውለው ...
Read More »ግሎባል አሊያንስ ከጎንደር ለተፈናቀሉ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ረዳ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 11/2011)ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር መለገሱን ግሎባል አልያንስ አስታወቀ። አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን ግሎባል አሊያንስ የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ከ3 ሺ በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉትም የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ። እናም በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ...
Read More »በጎንደር የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የሚከልከል መመሪያ ወጣ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2011)በጎንደር በተወሰኑ አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የሚከልከል መመሪያ በአማራ ክልል ይፋ ተደረገ። መመሪያውን ለማስፈጸም ከመከላከያ ሰራዊት ፥ከክልሉ ፖሊስና የጸጥታ ሐይሎች የተወጣጣ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጅአለም ከኢሳት ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ አስታወቋል። ይህ ጸጥታን በጥምር ወታደራዊ እዝ የማስከበሩ ስራ በመመሪያ መልክ የወጣ እንጂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመሆኑንም አቶ ዘላለም ገልጸዋል። በምዕራብ እና ...
Read More »አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተፈቀደ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011)የኢትዮ ቴሌኮም የኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ የነበሩትና በሌብነት የተጠረጠሩት አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤት ፈቀደ። ፍርድ ቤቱ አቶ ኢሳያስ ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ፈቅዶላቸዋል። ፖሊስ በወሳኔው ላይ ይግባኝ ስለመጠየቁ የተገለጸ ነገር የለም። አቶ ኢሳያስ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ይፈቱ አይፈቱ የታወቀ ነገር የለም። መርማሪ ፖሊስ በኢትዮ-ቴሌኮም ኃላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ...
Read More »