ግሎባል አሊያንስ ከጎንደር ለተፈናቀሉ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ረዳ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 11/2011)ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር መለገሱን ግሎባል አልያንስ አስታወቀ።

አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን ግሎባል አሊያንስ የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት የቦርድ አመራር አባላት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ከ3 ሺ በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል።

ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉትም የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ።

እናም በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ለተፈናቀሉት ወገኖች የጎ ፈንድ ሚ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በይፋ መጀመሩን ግሎባል አሊያንስ አስታውቋል።