አብቁተ የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2011)የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) በአማራ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

አብቁተ ከማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታወቋል ።

ጥረት ኮርፖሬት በበኩሉ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታወቋል

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም /አብቁተ/ ድጋፉን ያደረገው የክልሉ መንግሥት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ለሚገኙ ወገኖች የድጋፍ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነው ተብሏል ።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ90 ሺህ በላይ መድረሱን የክልሉ መንግሥት ማስታወቁ ይታወሳል።

ከእነዚህ ዜጎች ውስጥም 45 ሺህ የሚሆኑት በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች መሆናቸው ነው የተገለፀው።

በክልሉ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን ካሉበት ችግር በማውጣት መልሶ ለማቋቋምም የክልሉ መንግስት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል ።

ጥረት ኮርፖሬት በበኩሉ የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታወቋል

በሌላ በኩል ሰሞኑን በጎንደር፣ ሁመራ፣ መተማ መስመር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የሚከለክለው ገደብ በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተሳካ ሁኔታ ለማስከበር የታቀደ እንጂ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር የማይገናኝ መሆኑን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተናግረዋል።

አቶ ሰማህኝ ይሕን ይበሉ እንጂ በጎንደር ተለይተው በተወሰኑ አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት የክልሉ ሚሊሻና ልዮ ሀይል እንዲሁም አማራ ፖሊስ ኮሚሽን የተካተቱብት ጥምር ሀይል ተዋቅሮ ጸጥታ የማስከበር ሽራ እየተከናወነ ነው።

በአማራ ክልል ጎንደር አካባቢ አስቸዃይ ጊዜ አዋጅ ከማለት ይልቅ ኮማንድ ፖስት የተቋቋመው የቱሪዝም ፍሰቱን ይጎዳል በሚል እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።