ኢፓድ ተመሰረተ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 11/2011) በኢትዮጵያ በመድሃኒት አቅርቦትና ጥራት ላይ እገዛ የሚያደርግ የዲያስፖራ ፋርማሲና የመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዎች ስብስብ ያለበት ተቋም በዋሽንግተን ዲሲ በይፋ ተመሰረተ።

የኢትዮጵያ የፋርማሲስቶችና የመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዎች ማህበር/ኢፓድ/ በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያን ኤምባሲ በተካሄደ ስነስርአት የማህበሩ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት በሃገሪቱ በመድሃኒት ቁጥጥርና ስርጭት እንዲሁም በጥራት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

ይህ ጥረት የመድሃኒት ፋብሪካዎችን በኢትዮጵያ እስከመገንባት እንደሚሄድ የማህበሩ አመራሮች ገልጸዋል።