የመንግስት ሰራተኞች ምርጫ ካርድ መውሰድ አለመውሰዳቸውን እየተጠየቁ ነው

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በሚያዝያ ወር ለሚካሄደው የአካባቢና የአ/አ አስተዳደር ምርጫ ካርድ መውሰድና አለመውሰዳቸውን በቀጥታ እየተጠየቁ መሆኑን እንዲሁም አንዳንድ አባል ያልሆኑ ነዋሪዎች በካድሬዎችና በደህንነት ሰዎች የኢህአዴግ ዕጩ ሆነው በምርጫው እንዲቀርቡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለአንድ ወር ተካሄዶ ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም የመራጮች መደበኛ ምዝገባ ቢጠናቀቅም በተለይ በአዲስ አበባ ...

Read More »

ኢሳት በስዊድንና በኖርዌይ የተሳካ ዝግጅት አደረገ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብርዋሪ 9፣ 2013 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄድው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰባቢያ ዝግጅት ላይ ከጨረታ ከመቶ ሰላሳ ሺህ የስዊድን ክሮነር ወይም ከሃያ ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ የተገኘው በዝግጅቱ ላይ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትሪያክ እና የጸረ ፋሽስት ታጋይ ...

Read More »

እውቁና አንጋፋው ድምፃዊ፤ አርቲስ ታምራት ሞላ አረፈ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እንደ ቅርስ ከሚታወቁት አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ የሆነው አርቲስት ታምራት ሞላ አረፈ። ታምራት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ 50 ዓመታት በላይ ያገለገለ ስመ-ጥር አርቲስት ነው። ከዓመታት በፊት በሉኪሚያ (የደም ካንሰር) የተጠቃው ተወዳጁ የባህል ቅርስ፤ከህመሙ ጋር ግብ ግብ ሲያደርግ ከቆዬ በሁዋላ ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ ህይወቱ አልፏል። በጎንደር ከተማ የተወለደው እና ገና በወጣትነት በሠራዊቱ ...

Read More »

የጸጥታ ሹሙ የኦሮሚያን መሬት ለሶማሊ ክልል አሳልፈን አንሰጥም አሉ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 4 ቀናት በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከፍተኛ   አጀንዳ ሆኖ የቀረበው በክልሉና በሶማሊ ክልል መካከል ያለው የብሄር ግጭት ነው። ከህመማቸው በመጠኑም ቢሆን አገግመው በስብሰባውላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዚዳንት፣ አቶ አለማየሁ አቶምሳ እና የክልሉ የጸጥታ ሹም ፍቃዱ ሰቦቃ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠተ ሞክረዋል። ከምስራቅ ኦሮሚያ እና ከቦረና ዞን የመጡ የምክር ቤት ...

Read More »

በትላንት አርብ የጁማ ጸሎት ተሳትፈዋል የተባሉ ሙስሊሞች ታሰሩ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንዳመለከተው ከፍተኛ ቁጥር ባስተናገደው የትናንት የጁማ ተቃውሞ በአስተባባሪነት የተጠረጠሩ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው። በመርካቶ፣ ፒያሳ ፣ ጉለሌ፣ ሰባተኛ እና በሌሎችም አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ተይዘው ታስረዋል። ከታሰሩት መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ፣ አንዳንዶች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ሌሎች ደግሞ በየአካባቢያቸው ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ተወስደዋል። ...

Read More »

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለስራ የተቀመጡ 18 አምባሳደሮችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጠራ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚኒስቴሩ ይህን እርምጃ የወሰደው ባለፈው ሀሙስ የፓርላማ አባላት ለአዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ጥያቄ ካቀረበ በሁዋላ ነው። የፓርላማ አባላት “በአንድ አገር ውስጥ ሁለት አምባሳደሮችና ሁለት ምክትሎች ይመደባሉ፣ ስራቸው ምንድነው?” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሚኒስትሩም ” ምን እንደሚሰሩ አላውቅም” የሚል መልስ መስጠታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በአጠቃላይ 30 አምባሳደሮችና ምክትሎች ያለምንም ስራ ደሞዝ እየተከፈላቸው ...

Read More »

”የዘንድሮው ምርጫ፤ ምርጫም፣ቅርጫም አይደለም”ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መራጮች ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት ለዘንድሮው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ  ዜጐች ቤታቸው በራፍ እየተንኳኳ አስጨናቂ በሆኑ የማግባባት ሂደቶች፤ ሕጉ እና መመሪያው የሚጠይቀው አንዱም መስፈርት መሟላቱ ሳይረጋገጥ ‹‹ሰው›› መሆኑ ብቻ እየታየ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ሲገደዱ ነበር። በምርጫ 97 ወቅት በመራጭነት ለመመዝገብ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግባቸው የነበሩት መስፈርቶች በዘንድሮው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ በቸልተኝነት መታለፋቸውን የጠቆሙ መራጮችና የፖለቲካ ...

Read More »

በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ዋሉ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-<<ጅሀዳዊ ሀረካት>> የተሰኘውንና በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰሞኑን የተላለፈውን ፊልም በመቃወምና ለታሰሩት የሙስሊም መፍትሔ =  አፈላ ላጊ ኮሚቴዎች አጋርነታቸውን ለመግለጽ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ዛሬ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል። “መሪዎቻችን ይፈቱ! ዓላማችን ኢስላማዊ መንግስት ሳይሆን የሀይማኖት ነፃነታችንን ማግኘት ነው! ድምፃችን ይሰማ ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይቁም>>የሚሉ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን የሚያወግዙ መፈክሮች ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በሳኡዲ አረቢያ-ሪያድ ለ ዓባይ ግድብ ቦንድ ግዥ የጠራው ስብሰባ ወደ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀይሮ በተቃውሞ ተጠናቀቀ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ለ አባይ ግድብ ማሰሪያ የሚውል የቦንድ ግዥ የሚካሄድበትን ፕሮግራም የያዘው ከሳምንታት በፊት ነው። በፕሮግራሙ መሰረት ትናንት ሐሙስ ከወትሮው በተለዬ መልኩ በሪያድና አካባቢው የሞኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት የኮሙኒቲውን አዳራሽ ከ አፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል። የቦንድ ግዥውን ፕሮግራም ለመምራት ወደዚያው ያቀኑት የኢህአዴግ ባለስልጣናትም  በስብሰባው ከተገኘው በርካታ ሰውደጎስ ያለ ገንዘብ ...

Read More »

በሳውዲ የሚኖሩ በርካታ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዘወትር  አርብ እየተሰባሰቡ የሚያደርጉትን የአምልኮ መርሀግብር ሲጀምሩ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎች ወደ አምልኮ ስፍራው በመሄድ አፍሰው ወስደዋቸዋል። 43 ሴቶች እና 6 ወንዶች መታሰራቸውን በሳውዲ ነዋሪ የሆኑት የእምነቱ ተከታይ  አቶ በሪሁን አሰፋ ገልጸዋል ፤ ሶስቱ አገልጋዮች ለብቻ ተወስደው =መታሰራቸውን አክለዋል። የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ሰዎች ወደ አገራቸው ሊመልሱዋቸው እንደሚችሉ የገለጡት አቶ በሪሁን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ...

Read More »