በተያያዘ ዜና በጉምሩክ ባለሥልጣኖችና ባለሃብቶች ላይ የተጀመረው የምርመራ ሥራና ዘመቻ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትዕዛዝና መመሪያ መሆኑ ተገለጠ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑትን አቶ ዓሊ ሱሌይማንን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ወቅት በሰጡት የሥራ መመሪያ መሰረት ጥናትተደርጎ የተከናወነ መሆኑን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመት ከአሥር ወር በፊት የሥራ መመሪያ መስጠታቸውን ለተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት ኮሚሽነሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ አቶ መለስ በመታመማቸው ውሳኔ አግኝቶ ወደሥራ ሳይገባ ቆይቷል ብለዋል።በኢትዮጵያ ባለው አሰራር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮ፣ የሬዲዮ አድማጮቹን ቁጥር ለመጨመር በሚያደርገው ጥረት በአራት ተጨማሪ ሃገሮች በስልክ ሬዲዮውን የማሰራጨት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮ ማኔጅመንት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም፣ በጀርመን፣ በደቡብ አፍሪካና በኖርዌይ አድማጮች የኢሳት ሬዲዮን ፕሮግራሞች በስልክ እንዲያዳምጡ የሚያስችል አገልግሎት ዘርግቷል። በዚህ መሠረት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የኢሳት ሬዲዮ አድማጮች በስልክ ቁጥር 44-203-519-7144፣ የጀርመን አድማጮች 49-230-218-590-0200፣ የደቡብ አፍሪካ አድማጮች 27-105-918-884፣ የኖርዌይ አድማጮች ደግሞ በስልክ ቁጥር 47-219-532-14 ደውለው ፕሮግራሞችን ማድመጥ የሚችሉ መሆኑን ...

Read More »

በባህርዳር 17 ሰዎችን በጥይት አርከፍክፎ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ከዘር ጋር የተያያዘ ምክንያት የለውም ሲሉ የአማራ ክልል የፖሊስ አዛዥ ተናገሩ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን  በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት መለየቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አስታውቋል። ኢሳት ትናንት  ፖሊሱ የሌላ ብሄር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን በመንተራስ ...

Read More »

በቻግኒ ከተማ የህዝብን ተቃውሞ ተከትሎ አንድ መስጊድ ታሸገ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ መስጊድ አረህማን እየተባለ የሚጠራው ነባር መስጊድ የታሸገው ህዝቡ መንግስት የወከለውን አሰጋጅ አንቀበልም በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። በመስጊዱ መግቢያ ላይ  የተለጠፈው ወረቀት ፣ ” ከዛሬ ጀምሮ በዚህ መስጊድ መስገድ በህግ ያስቀጣል” የሚል ይዘት እንዳለው የአይን እማኞች ተናግረዋል። ነባሩ መስጊድ እንዲታሸግ መደረጉን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ መንገድ ላይ መስገድ መጀመሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ...

Read More »

የኩል ዉሀ ፋብሪካ መርዛማ ዝቃጭ አሳስቦናል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ ንብረትነቱ የሼህ ሙሀመድ አላሙዲን የሆነው የቡሬ ኩል ውሀና ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ መርዛማ ዝቃጭ በጤና ላይ እያደረሰው ያለ ችግር አሳስቦናል ሲሉ የወረዳው ኗሪዎች ተናገሩ፡፡ ህዝቡ ለመጠጥና ለመስኖ ስራ በሚገለገልባቸው ይስርና ኩል ወንዞች የሚለቀቀው መርዛማ ዝቃጭ ወንዙን ተከትሎ በሰፈረው ህዝብ ላይ ከሚያደርስው የጤና ችግር ባለፈ በንብረት ላይ አሉታዊ ተፅንኦ ፈጥሯል ...

Read More »

በመኪና አደጋ የ 17 ሰዎች ህይዎት አለፈ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባህር ዳር ከተማ በመሸንቲ ሳተላይት ቀበሌ ቆጥቆጥማ ተብሎ  በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 1/2005 ዓ/ም ሁለት መኪናዎች ተጋጭተው የ16 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ አደጋው የተከሰተው ከእንጅባራ ወደ ባህር ዳር ከተማ 19 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-08862  አማ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከባህር ዳር ከተማ ወደ  ዳንግላ ከተማ በመጎዝ ላይ ...

Read More »

17 ሰዎችን የገደለው የፌደራል ፖሊስ ማንነት በውል አልታወቀም

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን  በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት እና የገደለበት ምክንያት በውል አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው። ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው አንድ ያፈቀራት ወጣት ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ...

Read More »

በጭልጋ ወረዳ በተነሳ ተቃውሞ 60 ሰዎች ታሰሩ በርካቶችም በረሀ ገብተዋል

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከጎንደር ከተማ 55 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በጭልጋ ወረዳ  አለምጸሀይ ቀበሌ አመክሊን እየተባለ በሚጠራ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደሮች “ ለ አገር ውስጥ ባለሀብት ሊሰጥ ነው”ከተባለው ይዞታቸው እንዲነሱ  የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቃወማቸው በታጠቁ  የክልል እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት መንደራቸው ተከብቦ ተኩስ እንደተከፈተባቸው የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። ይዞታችንን አንለቅም ያሉት ሁሉ  ሚያዚያ 29 ቀን ...

Read More »

ሉሲ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየት እንዳልነበረባት ሳይንቲስቶች ተናገሩ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሉሲ መውጣት የለባትም”የሚል አቋም ይዘው የነበሩ ወገኖች፤ በአቶ መለስ ደብዳቤ ተረትተው ሉሲ እንድትወጣ መደረጉም ተጠቁሟል። ላለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ከርማ የተመለሰችው ሉሲ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየት እንዳልነበረባት ኢትዮጵያዊው የቅሬተ አካል ሳይንቲስት ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ  መናገራቸውን ሪፖርተር ዘገበ።   ዶክተር ዘረሰናይ ይህን ያሉት፤የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም ...

Read More »

መንግስት በዜጎች መፈናቀል ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲል መድረክ አስታወቀ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጠው መግለጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለደረሱትና እየደረሱ ላሉት የዜጎች በህገወጥ መንገድ መፈናቀል ተጠያቂነቱን በበታች የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አስተዳደር አካላት ላይ በማላከክ መንግስትን ከተጠያቂነት ለማዳን መሞከር ” ተጨፈኑ ላታላችሁ” አይነት እርምጃ ነው ብሎአል። በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በሁዋላ መንግስትን ከሃላፊነት ለማሸሽ የበታች አካላትን የመስዋት በግ በማድረግ የተኬደበት አቋራጭ ...

Read More »