በሳውዲ የሚኖሩ በርካታ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዘወትር  አርብ እየተሰባሰቡ የሚያደርጉትን የአምልኮ መርሀግብር ሲጀምሩ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎች ወደ አምልኮ ስፍራው በመሄድ አፍሰው ወስደዋቸዋል። 43 ሴቶች እና 6 ወንዶች መታሰራቸውን በሳውዲ ነዋሪ የሆኑት የእምነቱ ተከታይ  አቶ በሪሁን አሰፋ ገልጸዋል ፤ ሶስቱ አገልጋዮች ለብቻ ተወስደው =መታሰራቸውን አክለዋል።

የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ሰዎች ወደ አገራቸው ሊመልሱዋቸው እንደሚችሉ የገለጡት አቶ በሪሁን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ግን ታስረው ሊቆዩ እንደሚችሉ ፍርሀታቸውን ገልጸዋል።

ከወራት በፊት 34 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ታስረው፣ የተወሰኑት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።

ሳውዲ አረብያ የሀይማኖት ነጻነት የሌለባት አገር መሆኑዋ ይታወቃል።