በኦሮሚያ ዳኞች በብዛት እየለቀቁ ነው

ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ነው ስራቸውን የሚለቁት። አምና ከ100 በላይ ዳኞች ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን በያዝነው አመት ደግሞ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል። ከአንድ ወር በፊት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታደለ ነጊሾና አቶ ሰይድ ጁንዲን   ስልጣናቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲለቁ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ...

Read More »

በሎሚ ዲሳ ወረዳ የፖሊስ አባላት ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ስብሰባ እንዳይካፈሉ ታገዱ

ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን በገሳ ከተማ በተጠራው የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ የሎማ ዲሳ ህዝብን አዲስ የወረዳ ጥያቄን በመደገፍ ንግግር የዳረጉት የሀምሳ አለቃ ሽታየ ከታሰሩ በሁዋላ፣ ሌሎች የወረዳው ፖሊሶች ዛሬ በተጠራው ስብሰባ ላይ እንዳይካፈሉ ታግደዋል። የዞኑ ባለስልጣናት ለዲሳ ህዝብ ወረዳ አያስፈልገውም በማለት መናገራቸውን ተከትሎ አምሳ አለቃው ” ወረዳ ለህዝብ ባያስፈልግ ኖሮ ያኔ ለሲዳማ ...

Read More »

የስነምግባርና የስነዜጋ ትምህርት አስተማሪዎች የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ጫና እየደረሰባቸው ነው

ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መምህራኑ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ መምህራን ከታህሳስ12 እስከ 15 ” የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት የበለፀገች ዴሞከራሲያዊት አገር ለመገንባት ያለው ፋይዳና ሕገ-መንግሥቱን ለትውልድ የማስረፅ አስፈላጊነት” በሚል ርዕስ በአዳማ፣ በሃዋሳ፣ በባህር ዳርና በጅማ ከተሞች ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረው፣ ስልጠናው በዋናነት በአገሪቱ ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የህግ የበላይነት ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በስልጠናው ላይ ...

Read More »

አዲስ አበባ በሞቱ ውሾች ሳቢያ በሽታ እንዳይነሳ ተሰግቷል፤ ቢሮዎቹ እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነው

ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ  አበባ  የተለያዩ ቦታዎች  ተገድለው  ያልተነሱ ውሻዎች  በህብረተሰቡ ዘንድ የጤና ስጋት መፍጠራቸውን ፋና ዘገበ። ራዲዮ ጣቢያው የመዲናዋን  ነዋሪዎች በመጥቀስ እንደዘገበው  ሰሞኑን ባልተለመደ መልኩ በተለያዩ የመዲናይቱ አካባቢዎች  የሞቱ ውሾች ይታያሉ። የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት  በማድረግ የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኞች በከተማዋ ባደረጉት ቅኝት በስታድየም ፣ በጨርቆስ ፣ በፒያሳና በገርጂ መብራት ሃይል አከባቢዎች  የተገደሉ ውሻዎች ባልተለመደ መልኩ ...

Read More »

ለእርቅ ጉባኤ አሜሪክ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አባቶች በሽምግልና ኮሚቴ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጡ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚገኙ አባታቶችን በሶስት ዙር ሲያደራድር የቆየውና ለአረተኛ ዙር ቀጠሮ ይዞ የተነሳው የሽምግልና ቡድን ባለፈው አርብ ያወጣው መግለጫ እንዳስቆጣቸው የገለጹት አባቶች ይቅርታ ካልተጠየቁ በተያዘው የእርቅ ንግግር እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል:: በቤተክርስትያኒቱ መካከል እርቅ ለማውረድና ሰላምን ለማውረድ ሲንቀሳቀስ የቆየው አስታራቂ ቡድን አዲስ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወም ባለፈው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል:: ...

Read More »

ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ብቻ ነው ሲሉ አንጋፋው የሕውሀት ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ ገለጹ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሐት ነጋ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንደማይመስላቸውና ያለው የጋራ ራዕይ መሆኑን ገልጠዋል:: ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ያወሱት አቶ ስብሐት ነጋ: መደረግ የነበረበት ነገር መከናወኑን አስረድተዋል:: ይህ እርምጃ ሕገ-መንግስቱን ይጥሳል በሚል የሚነሳውን ተቃውሞ ...

Read More »

በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች  ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ  አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቶል:: የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ...

Read More »

መንግስት አቡነ መርቆርዮስ ቢመለሱ አልቃወምም ማለቱ ተዘገበ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሳምንታዊ ሰንደቅ  እንደዘገበው መንግስት በህገ-መንግስቱ መሠረት በሃይማኖቶች የውስጥ ተግባር ጣልቃ መግባት ስለማይችል አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የማለት ህገ-መንግስታዊ መሰረት የለውም። በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ፤ <<4ኛው ፓትርያሪክ የነበሩት አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ብሎ ካመነ  መንግስት ተቃውሞ የለውም>>ብሏል-ሚኒስቴሩ። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ...

Read More »

መምህራን ተማሪዎችን ፈርመው እንዲረከቡ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች መጨመራቸውን ተከትሎ ፣ በአማራ ክልል የሚያስተምሩ መምህራን ተማሪዎችን በሰሚስተሩ መጀመሪያ ላይ ቆጥረው ተረክበው፣ በሰሚስተሩ መጨረሻ ላይ ቆጥረው እንዲያስረክቡ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ለውይይት ቢቀርብም፣ መምህራን ግን አጥብቀው ተቃውመውታል። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ መምህሩ ቆጥሮ ከተረከባቸው ተማሪዎች መካከል ከ2 ተኩል በመቶ በላይ ተማሪዎች ቢያቋርጡ፣ መምህሩ በጥፋተኝነት የሚመዘገብ ሲሆን፣ አስፈላጊውን እድገትም አያገኝም። ...

Read More »

በ ኢትዮጵያውያ ከ11 ሚሊዮን በላይ ተረጅዎች አሉ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና በአለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በምግብ ለስራ ታቅፈው የሚረዱ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ታውቋል። መንግስት ሴፍቲኔት እያለ በሚጠራው መርሀግብር የታቀፉ ኢትዮጵያውያን ምእራባዊያን ለጋሾች እርዳታቸውን ቢያዘገዩ ወይም ቢያቋርጡ ወደ አስቸኳይ ተረጅነት የሚወርዱ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው የምግብ እጥረት የተነሳ በሴፍቲኔት የሚታቀፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ታውቋል። ...

Read More »