ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና የፍትህ አሳተሚ ጥፋተኞች ተባሉ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና በአሳታሚው ድርጅት በማስተዋል የህትመትና የማስታወቂያ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ በአቶ ማስ  ተዋል ብርሀኑ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል። የችሎቱ ዳኛ አቶ አይሸሹ ሽመልስ ውሳኔያቸውን በንባብ ያሰሙ ሲሆን የፌደራል አቃቢ ህግ ያቀረባቸውን 4 ክሶች በንባብ በማሰማት ፣ ሙሉ ...

Read More »

ከ10 አመታት በላይ ጊዚያቸው ያለፈባቸው መድሀኒቶች በመጋዘን ውስጥ ተገኙ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር እንዳስታወቀው ጊዜያቸው ያለፈባቸው በአማካኝ ከ8 እስከ 14 አመታት የቆዩ መድሀኒቶች በከነማ ፋርማሲዎች ተከማችተው ተገኝተዋል። የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና እንዳስደመጠው መድሀኒቶቹ በህገወጥ መልኩ እየወጡ ለፋርማሲዎች ሳይሸጡ አልቀረም። የአዲስ አበባ የጤና ቢሮ እንዳስታወቀው መድሀኒቶቹ የተጠራቀሙት የኦዲት ምርመራ ስላልተደረገባቸው ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል። በመንግስት ፋርማሲዎች ተከማችተው የሚገኙ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መድሀኒቶች አንዳንድ ...

Read More »

የጅማ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ

ጥር ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ቁጥራቸው ከ500 የማያንስ ሙስሊም የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በስታደየም አካባቢ በመሰባሰብ     ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ጠይቀዋል።  በደህንነት ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ዩኒቨርስቲው  እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎች ጥያቄ አቅርበዋል። የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ዲኑ ለስብሰባ ከአካባቢው በመራቃቸው መልስ ሊሰጡዋቸው እንደማይችሉ ለተማሪዎች ቢነግሩም፣ ተማሪዎቹ ግን በተቃውሞአቸው ገፍተውበታል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ ...

Read More »

የምርጫ ምዝገባ መጠናቀቁ በይፋ ከተገለጠ በሁዋላ ምዝገባው ዛሬም ቀጥሎአል

ጥር ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት የምርጫ ምዝገባው 100 በመቶ የተሳካ በመሆኑ ምርጫውን ከሁለት ቀናት የበለጠ እንደማያርዝም ገልጾ ነበር። ኢሳት ለምርጫው ተገዶም ቢሆን የተመዘገበው ህዝብ ከ30 በመቶ እንደማይበልጥ የምርጫ ቦርድ የውስጥ ምንጮችን በመግልጽ ዘግቧል። ከፍተኛ የኢህአዴግ ካድሬዎች ለወረዳ አመራሮች ቀይ መብራት በርቶባችሁዋል በማለት ማስፈራራታቸውን ተከትሎ ፣ አመራሩ ወደ ህዝቡ በመውረድ በእየቤቱ ሲያስገድዱ ቆይተዋል። ባለፈው ...

Read More »

ግንቦት 7 ጅሐዳዊ ሐረካት ተብሎ የተዘጋጀውን ፊልም አወገዘ

ጥር ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ ጅሃዳዊሐረካት የተባለው ድራማ ሁለቱን ትልልቅና ጥንታዊ የኢትዮጵያ ሐይማኖቶች ለማጣላት ሆን ተብሎ የተሰራ ነው ብሎአል። ኢትዮጵያ እስልምናንም ሆነ ክርስትናን በቅድምያ ከተቀበሉ አገሮች አንዷ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ክርስትናና እስልምና ከአንድ ሺ አመታት በላይ በሠላም ተከባብረዉ ጎን ለጎን የኖሩባት ብቸኛ አገር መሆኑዋን የገለጠው ግንባሩ፣ የአገር አንድነትና የህዝብ ...

Read More »

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች ሞቱ

ጥር ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወረዳ 10 በተለምዶ ሰራተኛ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ47 አባዎራዎች መኖሪያ ቤቶችና አራት ተሽከርካሪዎች በአደጋው ምክንያት የወደሙ ሲሆን ሶስት ሰዎችም በአደጋው ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። እሳቱን ለማጥፋት በስፍራው በነበሩ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ 2 ሰራተኞችና 4 የግቢው ነዋሪዎች ላይ ደግሞ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል። የኤጀንሲው የኮሚዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ ጀሃዳዊ ሀረካትን አጣጣለው

ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ” በ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› ትረካ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም!” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ፣ በገዢው ፓርቲ ድርጊት ማፈሩንና ማዘኑን ገልጿል። ገዥው ፓርቲ  ዜጎች በማንኛውም መንገድ የሚያነሱትን ጥያቄ በግልጽና በውይይት መፍታት ያለመፈለጉ ግልጽ ሀገራዊ አደጋ እየሆነ መምጣቱ እየታየው ነው የሚለው አንድነት፣ “ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሀገር እያስተዳደረ ባለ መንግሥት” ማዘኑንም አልሸሸገም። አንድነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ...

Read More »

መከላከያ ሰራዊት በባድሜ አቅራቢያ ልምምድ አደረገ

ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት እንዳስታወቀው አድዋ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ልምምድ ያደረገው የሰራዊቱን ወቅታዊ ብቃት ለመገምገም ነው።  ባለፈው እሁድ  በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የተካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ግምገማ ይፋ አልሆነም። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተመሳሳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ ነው። የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ወታደራዊ ሀይላቸው እየፈረጠመ መምጣት መንግስትን ስጋት ላይ እንደጣለው ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በየግንባሩ የሚገኙ ...

Read More »

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባላት ማደኛ ወጣባቸው

ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአመራሩ ለመረዳት እንደቻለው፣ የፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ የወጣባቸው በማህበሩ ሊ/መንበር በወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በምክትሉ ሚኬኤል አለማየሁ እና በህዝብ ግንኙነት ሀላፊው በብርሀኑ ተክለያሬድ ላይ ነው። ወጣት ብርሀኑ በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት የገባ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩና ምክትሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልተያዙም። ግለሰቦቹን በግንቦት7 ስም ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።   በቅርቡ የመንግስት ...

Read More »

”የቀድሞውጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶዎችና ፖስተሮች ይነሱ! ” ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ጠየቀ

ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጣው በዛሬው ርዕሰ-አንቀጹ የ አቶ መለስ ፎቶና ፖስተር ያልተሰቀለበትን የ አዲስ አበባ ጎዳና ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻልና ፎቷቸው በሁሉም ስፍራ እንዳለ በመጥቀስ፦<<አሁን ግን ይብቃ! ፎቶዎቹና ፖስተሮቹ ይነሱ!እንላለን>> ሰል በአጽንኦት ጠይቋል። ፖስተሮቹ ሊያስተላልፉ የሚገባቸውን መልእክት በክብር እንደተሰቀሉ በክብር ይነሱ ያለው ጋዜጣው፤ ዝናምና ፀሀይ እስኪያበላሻቸው ዝም ብሎ መጠበቅ  ማቆሸሽና ትርጉም ማሳጣት ነው ብሏል። ፖስተሮቹ ዘላለማዊ ...

Read More »